Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 26:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ብዙ የበግና የከብት መንጋ፥ እንዲሁም ብዙ አገልጋዮች ስለ ነበሩት ፍልስጥኤማውያን ቀኑበት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ብዙ የበግና የፍየል መንጋ፣ ብዙ ከብት፣ ብዙ አገልጋዮችም ስለ ነበሩት፣ ፍልስጥኤማውያን ተመቀኙት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 በግና ላም ከብትም ሎሌዎችም እጅግ በዙለት፥ የፍልስጥኤም ሰዎች ቀኑበት።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ወን​ዶ​ችና ሴቶች አገ​ል​ጋ​ዮ​ችን፥ ብዙ በጎ​ች​ንና ላሞ​ችን፥ የእ​ርሻ መሬ​ት​ንም ገዛ፤ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤም ሰዎ​ችም ቀኑ​በት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 የበግና የላም ከብትም ሎሌዎችም እጅግ በዙለት የፍልስጥኤም ሰዎች ቀኑበት።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 26:14
16 交叉引用  

በእርስዋ ምክንያት ንጉሡ አብራምን በደኅና ዐይን ተመለከተው፤ በጎች፥ ከብቶች፥ አህዮች፥ ግመሎች፥ ወንዶችና ሴቶች አገልጋዮችን ሰጠው።


አብራም ብዙ እንስሶች፥ ብዙ ብርና ወርቅ ያለው ሀብታም ሰው ነበረ።


እግዚአብሔር ጌታዬን እጅግ ባርኮታል፤ ባለጸጋም አድርጎታል፤ ብዙ የበግ፥ የፍየልና የከብት መንጋ፥ ብርና ወርቅ፥ ወንዶችና ሴቶች አገልጋዮች ግመሎችና አህዮች ሰጥቶታል።


አብርሃም ያለውን ሀብት ሁሉ ለይስሐቅ አወረሰው፤


በዚህ አኳኋን ያዕቆብ እጅግ ባለ ጸጋ ሆነ፤ ብዙ መንጋዎች፤ ሴቶችና ወንዶች አገልጋዮች፥ ብዙ ግመሎችና አህዮችም ነበሩት።


የዮሴፍ ወንድሞች እጅግ ቀኑበት፤ አባቱ ግን ይህን ነገር በልቡ እያሰላሰለ ይጠብቀው ነበር።


በሀብትም በኩል ሰባት ሺህ በጎች፥ ሦስት ሺህ ግመሎች፥ አምስት መቶ ጥማድ በሬዎችና አምስት መቶ አህዮች ነበሩት፤ እንዲሁም እጅግ ብዙ አገልጋዮች ነበሩት፤ በምሥራቅ አገር ካሉት ሰዎች ሁሉ እርሱን የሚያኽል ሀብታምና ታላቅ ሰው አልነበረም።


እግዚአብሔር የኢዮብን የመጨረሻ ሕይወት ከመጀመሪያው አስበልጦ ባረከው፤ ስለዚህ ኢዮብ ዐሥራ አራት ሺህ በጎች፤ ስድስት ሺህ ግመሎች፤ አንድ ሺህ ጥማድ በሬዎች፤ አንድ ሺህ እንስት አህዮች ነበሩት።


ቊጣ ሞኝን ይገድለዋል፤ ቅናትም ሰውን ያጠፋል።


ክፉዎች ይህን አይተው ይቈጣሉ፤ ተስፋ በመቊረጥም ጥርሳቸውን ያፋጫሉ፤ የክፉዎችም ምኞት ከንቱ ይሆናል።


ቤተሰቦቹ ሀብታሞችና ባለጸጎች ይሆናሉ፤ ጽድቅም ለዘለዓለም የእርሱ ይሆናል።


የእግዚአብሔር በረከት ሐዘንን የማይጨምር ብልጽግና ይሰጣል።


ቊጣ ጭካኔና ንዴትን ያስከትላል፤ ቅናት ግን ከቊጣ የባሰ ነው።


ደግሞም ሰዎች የተመኙትን ለማግኘት ተግተው በመሥራት ምን ያኽል እንደሚደክሙ ተመለከትኩ፤ ይህንንም የሚያደርጉት በባልንጀሮቻቸው ላይ በመቅናት መሆኑን ተረዳሁ፤ ይህም ሁሉ ከንቱ ስለ ሆነ ነፋስን ለመጨበጥ እንደ መሞከር ነው።


ከዚህም የተነሣ ከዚያን ቀን ጀምሮ በዳዊት ላይ ቅናትና ጥርጣሬ አደረበት።


跟着我们:

广告


广告