Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 25:30 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 ስለዚህም ያዕቆብን “ከዚህ ከቀይ ወጥ ስጠኝ” አለው። ኤዶም የተባለውም በዚህ ምክንያት ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 ዔሳውም ያዕቆብን፣ “ቶሎ በል፤ በጣም ርቦኛልና ከዚህ ቀይ ወጥ አብላኝ” አለው። ስለዚህም ስሙ ኤዶም ተባለ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 ዔሳውም ያዕቆብን፥ “ከዚህ ከቀዩ ወጥ አብላኝ፥ እኔ እጅግ እርቦኛልና!” አለው፤ (ኤዶም የተባለውም በዚህ ምክንያት ነበር።)

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 ዔሳ​ውም ያዕ​ቆ​ብን፥ “ከም​ስር ንፍ​ሮህ አብ​ላኝ፤ እኔ እጅግ ደክ​ሜ​አ​ለ​ሁና” አለው፤ ስለ​ዚ​ህም ስሙ ኤዶም ተባለ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 ዔሳውም ያዕቆብን፦ ከዚህ ከቀዩ ወጥ አብላኝ እኔ እጅግ ደክሜአለሁና አለው ስለዚህ ስሙ ኤዶም ተባለ።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 25:30
15 交叉引用  

ከዕለታት አንድ ቀን ያዕቆብ ቀይ የምስር ወጥ በመሥራት ላይ እንዳለ ዔሳው ከአደን መጣ፤ በጣም እርቦት ነበር፤


ያዕቆብም “መጀመሪያ ብኲርናህን ሽጥልኝ” አለው።


ከዚህ በኋላ ያዕቆብ በኤዶም አገር ሤዒር ተብላ በምትጠራው ምድር ወደሚኖረው ወደ ወንድሙ ወደ ዔሳው መልእክተኞች አስቀድሞ ላከ።


እንዲህም በማለት አዘዛቸው፥ “ለጌታዬ ለዔሳው እንዲህ ብላችሁ ንገሩት፤ ‘ታማኝ አገልጋይህ እኔ ያዕቆብ እስከ አሁን የቈየሁት ከላባ ጋር እንደ ነበር ልነግርህ እወዳለሁ፤


ኤዶም የተባለው የዔሳው የትውልድ ታሪክ የሚከተለው ነው፤


እነዚህ ሁሉ ኤዶም የተባለው የዔሳው ልጆችና የነገድ አለቆች ናቸው።


ማግዲኤልና ዒራም። በየመኖሪያ ስፍራቸው ስም የሚጠሩት የኤዶም አለቆች እነዚህ ናቸው። ይህም ዔሳው የኤዶማውያን አባት ነው።


ስለዚህ ኤዶም የተባለው ዔሳው በተራራማው አገር በኤዶም ተቀመጠ።


በተራራማው አገር በኤዶም ይኖሩ የነበሩት ኤዶማውያን ቅድመ አያት የነበረው የዔሳው ዘሮች የሚከተሉት ናቸው፤


በኢዮራም ዘመነ መንግሥት ኤዶም በይሁዳ ላይ ዐመፀ፤ የራሱንም ነጻ መንግሥት ዐወጀ፤


የኤዶም መሪዎች ተስፋ ቈረጡ፤ የሞአብም ኀያላን ተንቀጠቀጡ፤ የከነዓንም ሕዝብ ወኔ ከዳቸው።


የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ስለ ኤዶም የተናገረው ይህ ነው፦ “የቴማን ከተማ ሕዝብ ከዚህ በፊት የነበራቸውን ጥበብ አጥተዋልን? አማካሪዎቻቸውስ ምክር መስጠት አቅቷቸዋልን? የነበራቸውስ ጥበብ የት ደረሰ?


አብድዩ ያየው ራእይ፦ እግዚአብሔር አምላክ ኤዶምን በተመለከተ አብድዩን ልኮአል፤ የሰማነውም የእግዚአብሔር መልእክት፦ “እኔ እግዚአብሔር በኤዶም ላይ አደጋ እንዲጥሉ በማዘዝ ወደ ሕዝቦች መልእክተኛ ልኬአለሁ!” የሚል ነው።


“ኤዶማውያን ዘመዶችህ ስለ ሆኑ አትጸየፋቸው፤ በግብጽ ምድር ስደተኛ ሆነህ ስለ ኖርክ ግብጻውያንን አትጸየፋቸው።


跟着我们:

广告


广告