ዘፍጥረት 24:45 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም45 የኅሊና ጸሎቴን ገና ሳልጨርስ ርብቃ እንስራ ተሸክማ ብቅ አለች፤ ወደ ጒድጓዱም ሄዳ ውሃ ቀዳች፤ እኔም ‘እባክሽ ጥቂት ውሃ አጠጪኝ’ አልኳት። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም45 “በልቤ የምጸልየውን ጸሎት ገና ሳልጨርስ፣ ርብቃ እንስራዋን በትከሻዋ ላይ አድርጋ ብቅ አለች፤ ወደ ምንጩም ወርዳ ውሃ ቀዳች። እኔም፣ ‘እባክሽ፤ ውሃ አጠጪኝ’ አልኋት። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)45 “እኔም የልቤን መናገር ገና ሳልፈጽም፥ እነሆ፥ ርብቃ እንስራዋን በትከሻዋ ተሸክማ ወጣች፥ ወደ ምንጭም ወርዳ ውኃ ቀዳች እኔም፦ ‘እስኪ አጠጪኝ’ አልኋት። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)45 እኔም በልቤ ያሰብሁትን ሳልፈጽም እንዲህ ሆነ፤ ያን ጊዜ ርብቃ እንስራዋን በትከሻዋ ተሸክማ ወጣች፥ ወደ ምንጭም ወርዳ ውኃ ቀዳች፤ እኔም “እስቲ ውኃ አጠጪኝ” አልኋት። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)45 እኔም የልቤን መናገር ገና ሳልፈጽም እነሆ፥ ርብቃ እንስራዋን በትከሻዋ ተሸክማ ወጣች ወደ ምንጭም ወርዳ ውኃ ቀዳች እኔም፦ እስኪ አጠጭኝ አልኍት። 参见章节 |