ዘፍጥረት 24:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም15 ገና ጸሎቱን ሳይጨርስ ርብቃ እንስራ ተሸክማ መጣች፤ የዚህችም ልጅ አባት በቱኤል ይባል ነበር፤ እርሱም የአብርሃም ወንድም ናኮር ከሚስቱ ከሚልካ የወለደው ነው። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም15 እርሱም ገና ጸሎቱን ሳይጨርስ፣ እነሆ፤ ከአብርሃም ወንድም ከናኮርና ከሚስቱ ከሚልካ የተወለደው የባቱኤል ልጅ ርብቃ እንስራዋን በትከሻዋ ላይ አድርጋ ብቅ አለች። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)15 ይህን መናገሩንም ሳይፈጽም እነሆ፥ ሚልካ የወለደችው የባቱኤል ልጅ ርብቃ እንስራዋን በጫንቃዋ ተሸክማ ወጣች፥ ሚልካም የአብርሃም ወንድም የናኮር ሚስት ናት። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)15 እንደዚህ በልቡ ያሰበውን መናገሩን ሳይፈጽም እንዲህ ሆነ፦ የአብርሃም ወንድም የናኮር ሚስት የሚልካ ልጅ የባቱኤል ሴት ልጅ ርብቃ እነሆ፥ መጣች፥ እንስራዋንም በጫንቃዋ ተሸክማ ነበር። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)15 ይህን መናገሩንም ሳይፈጽም እነሆ ሚልካ የወለደችው የባቱኤል ልጅ ርብቃ እንስራዋን በጫንቃዋ ተሸክማ ወጣች፤ ሚልካም የአብርሃም ወንድም የናኮር ሚስት ናት 参见章节 |