ዘፍጥረት 18:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም19 ቅንና ትክክል የሆነውን ነገር በማድረግ የእግዚአብሔርን መንገድ እንዲጠብቁ ልጆቹንና ቤተሰቡን በመምከር ይመራቸው ዘንድ እኔ እርሱን መርጬዋለሁ፤ ልጆቹ ይህን ካደረጉ እኔም ለአብርሃም የሰጠሁትን ተስፋ ሁሉ እፈጽማለሁ።” 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም19 ትክክለኛና ጽድቅ የሆነውን በማድረግ የእግዚአብሔርን መንገድ ይጠብቁ ዘንድ ልጆቹንና ከርሱ በኋላ ቤተ ሰቦቹን እንዲያዝዝ መርጬዋለሁ፤ ይኸውም እግዚአብሔር ለአብርሃም የሰጠው ተስፋ ሁሉ እንዲፈጸም ነው።” 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)19 ጽድቅንና ፍርድን በማድረግ የእግዚአብሔርን መንገድ ይጠብቁ ዘንድ ልጆቹንና ከእርሱ በኋላ ቤቱን እንዲያዝዝ አውቃለሁና፥” ይህም እግዚአብሔር በአብርሃም ላይ የተናገረውን ነገር ሁሉ ያመጣ ዘንድ ነው። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)19 ጽድቅንና ፍርድን በማድረግ የእግዚአብሔርን መንገድ ይጠብቁ ዘንድ፥ ልጆቹንና ቤቱን ያዝዛቸው ዘንድ እንዳለው አውቃለሁና፤ ይህም እግዚአብሔር ለአብርሃም የተናገረውን ሁሉ ያደርግላቸው ዘንድ ነው።” 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)19 ጽድቅንና ፍርድን በማድረግ የእግዚአብሔርን መንገድ ይጠብቁ ዘንድ ልጆቹንና ከእርሱ በኍላ ቤቱን እንዲያዝዝ አውቃለሁና፤ ይህም እግዚአብሔር በአብርሃም ላይ የተናገረውን ነገር ሁሉ ያመጣ ዘንድ ነው። 参见章节 |