Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 16:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ስለዚህ ሰዎች በቃዴስና በባሬድ መካከል የሚገኘውን የውሃ ጒድጓድ “ብኤር ላሐይ ሮኢ” ብለው ይጠሩታል፤ ትርጒሙም “ሕያው የሆነውና የሚያየኝ አምላኬ ጒድጓድ” ማለት ነው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ከዚህ የተነሣ የዚያ ምንጭ ስም፣ “ብኤርላሃይሮኢ” ተብሎ ተጠራ፤ እስካሁንም በቃዴስና በባሬድ መካከል ይገኛል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ስለዚህም የዚያ ጉድጓድ ስም ብኤርለሃይሮኢ ተብሎ ተጠራ፥ እርሱም በቃዴስና በባሬድ መካከል ነው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ስለ​ዚ​ህም የዚ​ያን ጕድ​ጓድ ስም “በፊቴ የተ​ገ​ለ​ጠ​ልኝ የእ​ርሱ ጕድ​ጓድ” ብላ ጠራ​ችው፤ እር​ሱም በቃ​ዴ​ስና በባ​ሬድ መካ​ከል ነው። አጋ​ርም ተመ​ለ​ሰች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ስለዚህም የዚያ ጕድጓድ ስም ብኤርለሃይሮኢ ተብሎ ተጠራ፤ እርሱም በቃዴስና በባሬድ መካከል ነው።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 16:14
7 交叉引用  

ከዚያም ተመልሰው ወደ ቃዴስ መጡ፤ በዚያን ጊዜ የዚህ ቦታ ስም ዔይንሚሽፖጥ ይባል ነበር። የዐማሌቃውያንንም ምድር ሁሉ ያዙ፤ በሐጸጾን ታማር ይኖሩ የነበሩትን አሞራውያንንም አሸነፉ።


አጋር ለአብራም ወንድ ልጅ ወለደችለት፤ እርስዋ የወለደችለትንም ልጅ “እስማኤል” ብሎ ስም አወጣለት፤


በዚህም ጊዜ እግዚአብሔር ዐይኖችዋን ከፈተላትና አንድ የውሃ ጒድጓድ አየች፤ ሄዳም በአቁማዳው ውሃ ሞላች፤ ለልጅዋም አጠጣችው።


ሁለቱ ተማምለው የተስማሙበት ስፍራ በመሆኑ የዚያ ቦታ ስም ቤርሳቤህ ተባለ።


በዚህ ጊዜ ይስሐቅ “ብኤር ላሐይ ሮኢ ወይም የሚያየኝ ሕያው አምላክ” የተባለው ኲሬ ወዳለበት በረሓ መጥቶ በኔጌብ ተቀምጦ ነበር።


አብርሃም ከሞተ በኋላ ልጁን ይስሐቅን እግዚአብሔር ባረከው፤ ይስሐቅም “ብኤርላሐይ ሮኢ ወይም የሚያየኝ ሕያው አምላክ” ተብሎ በሚጠራው ኲሬ አጠገብ ይኖር ነበር።


በፋራን ምድረ በዳ በቃዴስ ወደነበሩት ወደ ሙሴና አሮን ወደ መላውም የእስራኤል ማኅበር መጡ፤ እነርሱም ያዩትን ነገር ሁሉ አስረዱ፤ ያመጡትንም ፍሬ አሳዩአቸው፤


跟着我们:

广告


广告