Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 14:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 እነዚህ ነገሥታት አንድ ግንባር ፈጥረው አሁን ሙት ባሕር ተብሎ በሚጠራው በሲዲም ሸለቆ ጦርነት ገጠሙ፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 እነዚህ የኋለኞቹ ዐምስቱ ነገሥታት በሲዲም ሸለቆ፣ በጨው ባሕር ተሰበሰቡ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 እነዚህ ሁሉ በሲዲም ሸለቆ ተሰብስበው ተባበሩ፥ ይኸውም የጨው ባሕር ነው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 እነ​ዚህ ሁሉ በኤ​ሌ​ቄን ሸለቆ ተሰ​ብ​ስ​በው ተባ​በሩ፤ ይኸ​ውም የጨው ባሕር ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 እነዚህ ሁሉ በሲዲም ሸለቆ ተሰብስበው ተባበሩ፤ ይኸውም የጨው ባሕር ነው።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 14:3
9 交叉引用  

በዚህ ዐይነት የከነዓናውያን ድንበር ከሲዶና አንሥቶ በስተደቡብ በገራር አጠገብ እስካለው እስከ ጋዛ ድረስ፥ በስተ ምሥራቅ እስከ ሰዶም፥ ገሞራ፥ አዳማና በላሻዕ አጠገብ እስካለው እስከ ጸቦይም ድረስ ሆነ።


በሲዲም ሸለቆ ብዙ የቅጥራን ጒድጓዶች ነበሩ፤ ስለዚህ የሰዶምና የገሞራ ነገሥታት ከጦርነቱ ሸሽተው ለማምለጥ በሞከሩ ጊዜ በጒድጓዶቹ ውስጥ ወደቁ፤ የቀሩት ሦስት ነገሥታት ግን ወደ ተራራዎቹ ሸሹ።


እነዚህ ነገሥታት ለዐሥራ ሁለት ዓመት በከዶርላዖሜር ቊጥጥር ውስጥ ነበሩ፤ በዐሥራ ሦስተኛው ዓመት ግን በእርሱ ላይ ዐመፁ።


ከዚህ በኋላ የሰዶም፥ የገሞራ፥ የአዳማ፥ የጸቦይምና የቤላዕ ነገሥታት ሠራዊታቸውን በሲዲም ሸለቆ አሰልፈው ተዋጉ፤


እግዚአብሔር በሰዶምና በገሞራ ከተሞች ላይ እሳትና ዲን ከራሱ (ከእግዚአብሔር ዘንድ) ከሰማይ አዘነበ።


እዚያ ከሚኖሩት ሰዎች ክፋት የተነሣ ፍሬያማዋን አገር እንደ ጨው ምድር የማታፈራ አደረጋት።


ወሰኑም ወደ ዮርዳኖስ ይወርዳል፤ መጨረሻውም የሙት ባሕር ይሆናል። እነዚህም የምድራችሁ ዙሪያ አዋሳኞች ይሆናሉ።”


በስተ ምዕራብ በኩል ያለው ግዛታቸው አራባን ዮርዳኖስንና በአካባቢው ያለውን ምድር ያጠቃልላል፤ በስተምሥራቅ በኩል ከገሊላ ባሕር በፒስጋ ተራራ ግርጌ እስካለው እስከ ጨው ባሕር ድረስ ይደርሳል።


ውሃው መውረዱን አቆመ፤ በጻርታን አጠገብ አዳም ተብላ እስከምትጠራው ከተማ ድረስ ተከመረ፤ ወደ ሙት ባሕር ይፈስ የነበረውም ጐርፍ በፍጹም ተቋረጠ፤ ስለዚህም ሕዝቡ ወደ ማዶ ወደ ኢያሪኮ ተሻገሩ።


跟着我们:

广告


广告