Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 1:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር “ምድር ሕይወት ያላቸው ፍጥረቶችን፥ እንደየዐይነታቸው እንስሶችን፥ በደረታቸው እየተሳቡ የሚንቀሳቀሱ ፍጥረቶችንና አራዊትን እንደየዐይነታቸው ታስገኝ” አለ፤ እንዲሁም ሆነ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 እግዚአብሔር፣ “ምድር ሕያዋን ፍጥረታትን እንደየወገናቸው፣ ከብቶችን፣ በምድር ላይ የሚሳቡ ፍጥረታትንና የዱር እንስሳትን እያንዳንዱን እንደ ወገኑ ታስገኝ” አለ፤ እንዳለውም ሆነ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 እግዚአብሔርም አለ፦ “ምድር ሕያዋን ፍጥረታትን እንደ ወገኑ፥ እንስሳትንና ተንቀሳቃሾችን የምድር አራዊትንም እንደ ወገኑ፥ ታውጣ፥” እንዲሁም ሆነ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለ፥ “ምድር ሕያ​ዋን ፍጥ​ረ​ታ​ትን እንደ ወገኑ፥ እን​ስ​ሳ​ት​ንና ተን​ቀ​ሳ​ቃ​ሾ​ችን፥ የም​ድር አራ​ዊ​ት​ንም እን​ደ​የ​ወ​ገኑ ታውጣ፥” እን​ዲ​ሁም ሆነ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 እግዚአብሔርም አለ ምድር ሕያዋን ፍጥረታትን እንደ ወገኑ እንስሳትንና ተንቀሳቃሾችን የምድር አራዊትንም እንደ ወገኑ ታዉጣ እንዲሁም ሆነ።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 1:24
15 交叉引用  

ቀኑ መሸ፤ ሌሊቱም ነጋ፤ አምስተኛ ቀን ሆነ።


እግዚአብሔር አምላክ ከምድር ዐፈር ወስዶ እንስሶችንና ወፎችን ሁሉ ፈጠረ፤ ምን ዐይነት ስም እንደሚያወጣላቸው ለማየት ወደ አዳም አመጣቸው፤ አዳም ለእያንዳንዱ ሕያው ፍጡር ያወጣለት ስም መጠሪያው ሆነ።


በሕይወት እንዲኖሩ ከየዐይነቱ ወፎች፥ ከየዐይነቱ እንስሶች፥ በደረታቸው እየተሳቡ ከሚንቀሳቀሱ ከልዩ ልዩ ተንቀሳቃሽ ፍጥረቶች በየዐይነቱ ሁለት ሁለት ወደ አንተ ይምጡ።


ከአራዊት፥ ከእንስሶች፥ በደረታቸው እየተሳቡ ከሚንቀሳቀሱ ፍጥረቶችና በሰማይ ከሚበርሩ ወፎች ከእያንዳንዱ ዐይነት አብረዋቸው ገቡ።


አራዊትና እንስሶች፥ ወፎችም በደረታቸው እየተሳቡ የሚንቀሳቀሱ ፍጥረቶችም በየወገናቸው ሆነው ከመርከቡ ወጡ።


“የበረሓ ፍየሎች የሚወልዱበትን ጊዜ ታውቃለህን? ዋልያ አምጣ ስትወልድ አይተህ ታውቃለህን?


“ኢዮብ ሆይ! ለፈረሶች ኀይልን የሰጠህ፥ በረጃጅምም ጋማ ያስጌጥካቸው አንተ ነህን?


“ለሜዳ አህዮች ነጻነት የሰጣቸው ማን ነው? ከእስራት የፈታቸውስ ማን ነው?


“ጎሽ የተባለው የዱር እንስሳ አንተን ለማገልገል ፈቃደኛ ይሆናልን? በበረትህስ ውስጥ ሊያድር ይችላልን?


“እኔ አንተንና ጒማሬን ፈጥሬአለሁ፤ ጉማሬውም እንደ በሬ ሣር ይበላል።


ዋልያዎች በከፍተኛ ተራራዎች ላይ ይገኛሉ፤ ሽኮኮዎችም በተሰነጠቁ አለቶች ውስጥ ይኖራሉ።


ከዚህ በኋላ ሰዎች ለሥራ ይሰማራሉ፤ እስከሚመሽም ድረስ ሲሠሩ ይውላሉ።


አራዊትና ለማዳ እንስሶች፥ በምድር የምትሳቡና በክንፍ የምትበርሩ ፍጥረቶች ሁሉ እግዚአብሔርን አመስግኑት።


跟着我们:

广告


广告