Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ገላትያ 3:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ይሁን እንጂ በመካከል ሆኖ የሚያስታርቅ ሰው ለሁለት ወገን ነው እንጂ ለአንድ ወገን ብቻ አይሠራም፤ እግዚአብሔር ግን አንድ ነው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ሆኖም መካከለኛው አንድን ወገን ብቻ የሚወክል አይደለም፤ እግዚአብሔር ግን አንድ ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 መካከለኛው አንድን ወገን ብቻ የሚወክል አይደለም፤ እግዚአብሔር ግን አንድ ነው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 መካ​ከ​ለ​ኛው ግን ማንም አይ​ደ​ለም፤ አንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው እንጂ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 መካከለኛውም ለአንድ ብቻ አይደለም እግዚአብሔር ግን አንድ ነው።

参见章节 复制




ገላትያ 3:20
11 交叉引用  

በዚያን ዕለት እግዚአብሔር ለአብራም እንዲህ በማለት ቃል ኪዳን ገባለት፦ “ከግብጽ ወንዝ ጀምሮ እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ያለውን ምድር ሁሉ ለዘሮችህ እሰጣለሁ፤


ከጀርባዬ እግዚአብሔር በትሩን እንዲያነሣና ግርማውም እንዳያስፈራኝ እጁን በሁለታችን ላይ የሚያኖር ዳኛ በመካከላችን ምነው በተገኘ!


ሄሮድስ በጢሮስና በሲዶና ሰዎች ላይ በጣም ተቈጥቶ ነበር፤ እነርሱም በአንድነት መጡና፤ የንጉሥ ባለሟል ብላስጦስ እንዲተባበራቸው ለምነው እሺ ካሰኙትም በኋላ ንጉሡን ዕርቅ ጠየቁ፤ ይህንንም ያደረጉት አገራቸው ምግብ የምታገኘው ከንጉሡ ግዛት ስለ ነበረ ነው።


እንግዲህ እኔ የምለው ይህን ነው፤ ከአራት መቶ ሠላሳ ዓመት በኋላ የተሰጠው ሕግ ቀደም ብሎ በእግዚአብሔር ተረጋግጦ የተሰጠውን ቃል ኪዳን በመሻር የተስፋውን ቃል ሊያጠፋው አይችልም።


“እስራኤል ሆይ! ይህን አስታውስ! እግዚአብሔር አምላካችን አንድ እግዚአብሔር ብቻ ነው፤


እግዚአብሔር አንድ ነው፤ በመካከል ሆኖ እግዚአብሔርንና ሰውን የሚያስታርቀውም አንድ ነው፤ እርሱም ሰው የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።


የአዲስ ኪዳን ማእከላዊ አስማሚ ወደ ሆነው ወደ ኢየሱስ፥ ከአቤል ደም ይልቅ የሚሻለውን ወደሚናገረውና ወደተረጨው ደሙም ቀርባችኋል።


አሁን ግን ኢየሱስ አማካይ አስማሚ የሆነበት ቃል ኪዳን ከአሮጌው ቃል ኪዳን የበለጠና በተሻለ ተስፋ ላይ የተመሠረተ እንደ መሆኑ ለእርሱ የተሰጠው አገልግሎት የበለጠ ነው።


እነዚያ የተጠሩት እግዚአብሔር በተስፋ የሰጠውን ዘለዓለማዊ ርስት እንዲቀበሉ ክርስቶስ የአዲስ ኪዳን ማእከላዊ አስማሚ ሆኖአል፤ ይህም የሆነው ሰዎችን በመጀመሪያው ቃል ኪዳን ሥር ሆነው ከሠሩት ኃጢአት ለማዳን እርሱ በመሞቱ ነው።


跟着我们:

广告


广告