Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ገላትያ 3:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 “በሕግ መጽሐፍ በተጻፉት ትእዛዞች ሁሉ ጸንቶ የማይኖርና የማይፈጽማቸው ሁሉ የተረገመ ነው” ተብሎ ስለ ተጻፈ “ሕግን በመፈጸም እንጸድቃለን” የሚሉ ሁሉ የተረገሙ ናቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ሕግን በመጠበቅ የሚተማመኑ ሁሉ ከርግማን በታች ናቸው፤ “በሕግ መጽሐፍ የተጻፈውን ሁሉ የማያደርግ የተረገመ ነው” ተብሎ ተጽፏልና።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ከሕግ ሥራ የሆኑት ሁሉ ከርግማን በታች ናቸው፤ “በሕግ መጽሐፍ በተጻፉት ሁሉ የማይኖርና የማይፈጽማቸው ሁሉ የተረገመ ይሁን፤” ተብሎ ተጽፎአልና።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 በኦ​ሪት ሕግ ያሉ ሁሉ በእ​ር​ግ​ማን ውስጥ ይኖ​ራሉ፤ መጽ​ሐፍ እን​ዲህ ብሎ​አ​ልና፥ “በዚህ በኦ​ሪት መጽ​ሐፍ ውስጥ የተ​ጻ​ፈ​ውን ሁሉ የማ​ይ​ፈ​ጽ​ምና የማ​ይ​ጠ​ብቅ ርጉም ይሁን።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ከሕግ ሥራ የሆኑት ሁሉ በእርግማን በታች ናቸውና፤ በሕግ መጽሐፍ በተጻፉት ሁሉ ጸንቶ የማይኖር የማያደርግም ሁሉ የተረገመ ነው ተብሎ ተጽፎአልና።

参见章节 复制




ገላትያ 3:10
18 交叉引用  

የወንድምህን ደም ከአንተ ለመቀበል አፍዋን በከፈተችው ምድር ላይ የተረገምክ ነህ።


ስለዚህ የቤተ መቅደስን ሹማምንት ርኲሰት ገለጥኩ፤ የያዕቆብም ልጆች እስራኤላውያን እንዲዋረዱና ፈጽመውም እንዲጠፉ አደረግሁ።”


ይህን ቃል ኪዳን የማይታዘዝ ሁሉ የተረገመ ይሁን።


ነገር ግን ወደዚህች ምድር መጥተው ከወረሱአት በኋላ ለቃልህ መታዘዝንና በአስተማርካቸው ሕግ ጸንተው መኖርን እምቢ አሉ፤ ያዘዝካቸውንም ነገር ሁሉ አልፈጸሙም፤ ከዚህም የተነሣ ይህን ሁሉ ጥፋት አመጣህባቸው።


የእያንዳንዱ ሰው ሕይወት የእኔ ነው፤ የወላጅም ሆነ የልጅ ሕይወት የእኔ መሆኑን ዕወቁ፤ ኃጢአት የሚሠራ ሰው ራሱ ይሞታል።


ከዚህ በኋላ በግራው በኩል ያሉትንም እንዲህ ይላቸዋል፤ ‘እናንተ የተረገማችሁ! ከእኔ ወዲያ ራቁ! ለዲያብሎስና ለተከታዮቹ መላእክት ወደ ተዘጋጀው ወደ ዘለዓለም እሳት ሂዱ!


ሕግ የሚያመጣው የእግዚአብሔርን ቊጣ ነው፤ ሕግ ከሌለ ግን ሕግን የመተላለፍ በደል አይኖርም።


ከኃጢአት የሚገኘው ዋጋ ሞት ነው፤ ከእግዚአብሔር የሚሰጠው ስጦታ ግን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት የሚገኘው የዘለዓለም ሕይወት ነው።


ሥጋዊ ነገርን የሚያስብ ሰው ለእግዚአብሔር ሕግ ስለማይታዘዝና መታዘዝም ስለማይችል የእግዚአብሔር ጠላት ነው።


ሕግ የተቀረጸው በድንጋይ ጽላት በፊደል ነበር፤ ሕግ በተሰጠበትም ጊዜ የነበረው ብርሃን እየተወገደ የሚሄድ ቢሆንም እስራኤላውያን የሙሴን ፊት ትኲር ብለው ሊመለከቱት አልቻሉም፤ እንግዲህ ሞትን ያመጣ ሕግ በእንዲህ ዐይነት ክብር ከተገለጠ


ነገር ግን ሰው የሚጸድቀው በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን እንጂ ሕግን በመፈጸም እንዳልሆነ እናውቃለን፤ እኛም ሕግን በመፈጸም ሳይሆን በክርስቶስ በማመን እንድንጸድቅ በኢየሱስ ክርስቶስ አምነናል፤ ማንም ሰው የኦሪትን ሕግ በመፈጸም አይጸድቅም።


“ ‘እነዚህን የእግዚአብሔርን ሕግ ቃላት ሁሉ የማይፈጽም ሁሉ የተረገመ ይሁን።’ “ሕዝቡም ሁሉ ‘አሜን’ ይበሉ።


እግዚአብሔር ለእንደዚህ ያለው ሰው ይቅርታ አያደርግም፤ ይልቁንም የእግዚአብሔር ቊጣና ቅናት በእርሱ ላይ እንደ እሳት ይነዳል፤ እግዚአብሔርም እንደዚህ ያለውን ሰው ፈጽሞ እስኪደመስሰው ድረስ በዚህ መጽሐፍ የተጻፉት መቅሠፍቶች ሁሉ ይወርዱበታል።


跟着我们:

广告


广告