Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ገላትያ 2:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 በክርስቶስ በማመን ለመጽደቅ ስንፈልግ እኛ ራሳችን ኃጢአተኞች ሆነን ብንገኝ ታዲያ፥ ኃጢአት እንድንሠራ የሚያደርገን ክርስቶስ ነው ማለት ነውን? ከቶ አይደለም!

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 “በክርስቶስ ለመጽደቅ ስንፈልግ፣ እኛ ራሳችን ኀጢአተኞች መሆናችን ግልጽ ነው፤ ታዲያ ክርስቶስ ኀጢአት እንዲስፋፋ ያደርጋልን? ከቶ አይሆንም!

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ነገር ግን በክርስቶስ ልንጸድቅ የምንፈልግ፥ እኛ ራሳችን ደግሞ ኃጢአተኞች ሆነን ብንገኝ፥ ታዲያ ክርስቶስ የኃጢአት አገልጋይ ነውን? በጭራሽ አይደለም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 በክ​ር​ስ​ቶስ ልን​ጸ​ድቅ የም​ንሻ እኛ እንደ ኀጢ​አ​ተ​ኞች ከሆን እን​ግ​ዲህ ክር​ስ​ቶስ የኀ​ጢ​አት አገ​ል​ጋይ መሆኑ ነውን? አይ​ደ​ለም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ነገር ግን በክርስቶስ ልንጸድቅ የምንፈልግ ስንሆን ራሳችን ደግሞ ኃጢአተኞች ሆነን ከተገኘን፥ እንግዲያስ ክርስቶስ የኃጢአት አገልጋይ ነዋ? አይደለም።

参见章节 复制




ገላትያ 2:17
17 交叉引用  

እርስዋ ወንድ ልጅ ትወልዳለች፤ እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ስለሚያድን ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ።”


የወይኑ ተክል ባለቤት ራሱ ይመጣል፤ ገበሬዎቹንም ይገድላል፤ የወይኑንም አትክልት ለሌሎች ገበሬዎች ይሰጣል።” ሰዎቹም ይህን በሰሙ ጊዜ “ይህስ ከቶ አይሁን!” አሉ።


ታዲያ፥ ውጤቱ ምን ሆነ? እስራኤላውያን የፈለጉትን አላገኙም፤ የተመረጡት ግን የፈለጉትን አገኙ፤ የቀሩት ልባቸውን አደነደኑ።


ይህንንም ስናገር እግዚአብሔር ለቀደሙት አባቶች የሰጠው ተስፋ እንዲፈጸምና የእግዚአብሔርም እውነተኛነት እንዲታወቅ ክርስቶስ የአይሁድ አገልጋይ ሆነ ማለቴ ነው።


ከቶ አያስቀርም! “ከቃልህ የተነሣ እውነተኛ ትሆናለህ፤ ባላጋራህንም በፍርድ ትረታለህ” ተብሎ እንደ ተጻፈው ሰው ሁሉ ሐሰተኛ ቢሆንም እግዚአብሔር እውነተኛ ነው።


ፈጽሞ አይደለም! እንዲህ ከሆነማ እግዚአብሔር በዓለም ላይ እንዴት ይፈርዳል?


ጴጥሮስ ወደ አንጾኪያ በመጣ ጊዜ በግልጥ ተሳስቶ ስለ ነበር ፊት ለፊት ተቃወምኩት፤


በእርግጥ እኛ በትውልዳችን አይሁድ ነን፤ እንደ ኃጢአተኞች አሕዛብም አይደለንም።


እንግዲህ ሕግ የእግዚአብሔርን የተስፋ ቃል ይቃወማልን? ከቶ አይቃወምም! ሕይወት የሚገኝበት ሕግ ተሰጥቶ ቢሆን ኖሮ ጽድቅ በሕግ አማካይነት በተገኘ ነበር።


ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር በሌላ መመካት ከእኔ ይራቅ፤ በዚህም መስቀል ዓለም ከእኔ ተለይቶአል፤ እኔም ከዓለም ተለይቼአለሁ።


እርሱ የሚያገለግለው እውነተኛ ድንኳን በሆነችው መቅደስ ነው፤ ይህች ድንኳን የተተከለችው በሰው እጅ ሳይሆን በጌታ ነው።


ክርስቶስ የሰዎችን ኃጢአት ለመደምሰስ እንደ ተገለጠና እርሱም ኃጢአት እንደሌለበት ታውቃላችሁ።


跟着我们:

广告


广告