Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ገላትያ 2:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 አንዳንድ ከአይሁድ ወገን የሆኑ ክርስቲያኖችም የጴጥሮስን ግብዝነት ተከተሉ፤ በርናባስ እንኳ ሳይቀር በግብዝነታቸው ተስቦ ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 በርናባስም እንኳ በእነርሱ ግብዝነት እስኪወሰድ ድረስ፣ ሌሎቹም አይሁድ በግብዝነቱ ተባበሩት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 የቀሩት አይሁድ ግብዝነቱን ተከተሉ፥ በርናባስ ስንኳ ሳይቀር በግብዝነታቸው ተሳበ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ከአ​ይ​ሁድ ወገ​ንም ወደ​ዚህ ግብር የተ​መ​ለሱ ብዙ​ዎች ነበሩ፤ በር​ና​ባ​ስም እንኳ በግ​ብ​ዝ​ነ​ታ​ቸው ተባ​በረ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 የቀሩትም አይሁድ ደግሞ በርናባስ ስንኳ በግብዝነታቸው እስከ ተሳበ ድረስ፥ ከእርሱ ጋር አብረው ግብዞች ሆኑ።

参见章节 复制




ገላትያ 2:13
17 交叉引用  

“በእርግጥ አንተ ልጄ ዔሳው ነህን?” ሲል እንደገና ጠየቀው፤ እርሱም “አዎ፥ ነኝ” አለ።


ለመሆኑ የጌታዬን ልጅ ካላገለገልኩ ማንን ላገለግል ነው? ስለዚህ አባትህን እንዳገለገልኩ አሁንም ደግሞ አንተን አገለግላለሁ።”


ልብህ ለምን ወደ ሌላ ይወስድሃል? ስለምንስ በቊጣ ዐይኖችህን ታፈጣለህ?


የሞቱ ዝንቦች ተቀምሞ የተሠራውን የዘይት ሽቶ ሊያገሙት ይችላሉ፤ እንዲሁም ትንሽ ሞኝነት ታላቅ ጥበብን ያጠፋል።


ምንም ስሕተት ሳይፈጽም ሁልጊዜ መልካም ነገርን የሚሠራ ደግ ሰው በምድር ላይ አይገኝም።


እንዲሁም እናንተ፥ በውጪ ለሰው ጻድቃን መስላችሁ ትታያላችሁ፤ በውስጣችሁ ግን ግብዝነትና ክፋት ሞልቶባችኋል።


የቆጵሮስ ተወላጅ የሆነ፥ ዮሴፍ የሚባል አንድ ሌዋዊ ነበረ፤ ሐዋርያት “በርናባስ” እያሉ ይጠሩት ነበር፤ ትርጓሜው “የመጽናናት ልጅ” ማለት ነው።


አሕዛብ በነበራችሁበት ጊዜ በማታውቁት ነገር ተመርታችሁ መናገር ወደማይችሉ ጣዖቶች ትወሰዱ እንደ ነበር ታውቃላችሁ።


አትታለሉ፤ “መጥፎ ጓደኛ ጥሩውን ጠባይ ያበላሻል።”


እንግዲህ መመካታችሁ መልካም አይደለም፤ ትንሽ እርሾ ሊጡን ሁሉ እንደሚያቦካው ታውቁ የለምን?


ይሁን እንጂ ይህ ነጻነታችሁ በእምነት ላልጠነከሩ ሰዎች መሰናከያ እንዳይሆንባቸው ተጠንቀቁ።


ከዐሥራ አራት ዓመት በኋላ ከበርናባስ ጋር ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሼ ሄድኩ፤ ቲቶንም ከእኔ ጋር ይዤው ሄጄ ነበር።


እንደ ምሰሶ መስለው የሚታዩት መሪዎች ያዕቆብና ጴጥሮስ ዮሐንስም እግዚአብሔር በጸጋ ይህን ልዩ የአገልግሎት ዕድል እንደ ሰጠኝ በተረዱ ጊዜ ለእኔና ለበርናባስ የመተባበራቸው ምልክት የሆነውን ቀኝ እጃቸውን ሰጡን፤ እኛ ወደ አሕዛብ እንድንሄድ እነርሱም ወደ አይሁድ እንዲሄዱ ተስማሙ።


ከእንግዲህ ወዲህ በሰዎች የተንኰል ሽንገላና አታላይነት በተዘጋጀ በአሳሳች የትምህርት ነፋስና ሞገድ ወዲያና ወዲህ ተገፍትረው እንደሚወሰዱ ሕፃናት አንሆንም።


ባልተለመደ በልዩ ልዩ ዐይነት ትምህርት አትማረኩ፤ ልባችን የመብል ሥነ ሥርዓቶችን በመጠበቅ ሳይሆን በጸጋ ቢጸና መልካም ነው፤ ይህን የምግብ ሥነ ሥርዓት የተከተሉ ሰዎች ምንም አልተጠቀሙም።


跟着我们:

广告


广告