Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዕዝራ 8:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2-14 ከፊንሐስ ጐሣ ጌርሾም፥ ከኢታማር ጐሣ ዳንኤል፥ ከዳዊት ጐሣ የሸካንያ ልጅ ሐጡሽ፥ ከፓርዖሽ ጐሣ ዘካርያስ ሲሆን፥ ከእርሱ ቤተሰብ ወገን የሆኑ አንድ መቶ ኀምሳ ወንዶች ተመዝግበዋል፤ ከፓሐትሞአብ ጐሣ የዘራሕያ ልጅ ኤልየሆዔናይ ከሁለት መቶ ወንዶች ጋር፥ ከዛቱ ጐሣ የያሐዚኤል ልጅ ሸካንያ ከሦስት መቶ ወንዶች ጋር፥ ከዓዲን ጐሣ የዮናታን ልጅ ዔቤድ ከኀምሳ ወንዶች ጋር፥ ከዔላም ጐሣ የዐታልያ ልጅ የሻዕያ ከሰባ ወንዶች ጋር፥ ከሸፋጥያ ጐሣ የሚካኤል ልጅ ዘባድያ ከሰማንያ ወንዶች ጋር፥ ከኢዮአብ ጐሣ የየሒኤል ልጅ አብድዩ ከሁለት መቶ ዐሥራ ስምንት ወንዶች ጋር፥ ከባኒ ጐሣ የዮሲፍያ ልጅ ሸሎሚት ከአንድ መቶ ሥልሳ ወንዶች ጋር፥ ከቤባይ ጐሣ የቤባይ ልጅ ዘካርያስ ከኻያ ስምንት ወንዶች ጋር፥ ከዓዝጋድ ጐሣ የሃቃጣን ልጅ ዮሐናን ከአንድ መቶ ዐሥር ወንዶች ጋር፥ ከአዶኒቃም ጐሣ ኤሊፌሌጥ፥ ይዒኤልና ሸማዕያ ከስድሳ ወንዶች ጋር፥ እነርሱም ዘግየት ብለው ተመልሰዋል፤ ከቢግዋይ ጐሣ ዑታይና ዛኩር ከሰባ ወንዶች ጋር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ከፊንሐስ ዘሮች ጌርሶን፤ ከኢታምር ዘሮች ዳንኤል፤ ከዳዊት ዘሮች ሐጡስ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ከፊንሐስ ልጆች ጌርሶን፥ ከኢታማር ልጆች ዳንኤል፥ ከዳዊት ልጆች ሐጡሽ፥

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ከፊ​ን​ሐስ ልጆች ጌር​ሶም፥ ከኢ​ታ​ምር ልጆች ዳን​ኤል፥ ከዳ​ዊት ልጆች ሐጡስ፥

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ከፊንሐስ ልጆች ጌርሶን፥ ከኢታምር ልጆች ዳንኤል፥ ከዳዊት ልጆች ሐጡስ፥ ከሴኬንያ ልጆች፥

参见章节 复制




ዕዝራ 8:2
6 交叉引用  

ዳዊት በኬብሮን ሳለ የወለዳቸው ወንዶች ልጆች ስም እንደ ዕድሜአቸው ቅደም ተከተል እንደሚከተለው ነው፦ በኲሩ የኢይዝራኤል ተወላጅ ከሆነችው ከአሒኖዓም የተወለደው አምኖን፥ ሁለተኛው የቀርሜሎስ ተወላጅ ከሆነችው ከአቢጌል የተወለደው ዳንኤል፥ ሦስተኛው የገሹር ንጉሥ የታልማይ ልጅ ከሆነችው ከማዕካ የተወለደው አቤሴሎም፥ አራተኛው ከሐጊት የተወለደው አዶንያስ፥ አምስተኛው ከአቢጣል የተወለደው ሸፋጥያ፥ ስድስተኛው ከዔግላ የተወለደው ዩትረዓም፤


ሸካንያም ሸማዕያን ወለደ፤ ሸማዕያም ሐጡሽ፥ ዩጋል፥ ባሪያሕ፥ ነዓርያና ሻፋጥ ተብለው የሚጠሩትን አምስት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ የሸካያ ትውልድ በድምሩ ስድስት ነበር፤


በንጉሡ በአርጤክስስ ዘመነ መንግሥት ከእኔ ጋር ከባቢሎን የተመለሱት የቤተሰብ አለቆች በየትውልዳቸው እንደሚከተለው ነው፦


እኔ ዕዝራ ወደ አሀዋ በሚፈሰው ወንዝ አጠገብ መላውን ጉባኤ ሰበሰብኩ፤ በዚያም ሰፍረን ለሦስት ቀኖች ቈየን፤ በዚያም ጉባኤ ውስጥ ከካህናት በቀር ሌዋውያን አለመኖራቸውን ተገነዘብኩ፤


跟着我们:

广告


广告