Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዕዝራ 6:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ቅጽሮቹም ከድንጋይ በተሠሩት በሦስቱም ዙር ግንቦች አናት ላይ አንዳንድ ዙር ከእንጨት የተሠራ ድምድማት ይኑራቸው፤ ለዚህም ሁሉ ሥራ የሚያስፈልገው ገንዘብ ከቤተ መንግሥቱ ግምጃ ቤት ወጪ ሆኖ ይሰጥ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 በሦስት ዙር ታላላቅ ድንጋዮችና በአንድ ዙር ዕንጨት ይሠራ፤ ወጪውም ከቤተ መንግሥቱ ግምጃ ቤት ይከፈል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 በሦስት መደዳ ታላላቅ ድንጋይ፥ አንድ መደዳ እንጨት ይደረግ፤ ወጪውም ከንጉሡ ቤት ይሰጥ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 በሦ​ስት ተራ ታላ​ላቅ ድን​ጋይ፥ በአ​ንድ ተራ እን​ጨት ይደ​ረግ፤ ወጭ​ውም ከን​ጉሡ ቤት ይሰጥ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 በሦስት ተራ ታላላቅ ድንጋይ፥ በአንድ ተራ እንጨት ይደረግ፤ ወጪውም ከንጉሡ ቤት ይሰጥ።

参见章节 复制




ዕዝራ 6:4
10 交叉引用  

በቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት አንድ የውስጥ አደባባይ ሠራ፤ በዚህም አደባባይ ዙሪያ በየሦስቱ ዙር የድንጋይ ረድፍ አንድ የሊባኖስ ዛፍ ሠረገላ ሳንቃ የተጋደመበት ግንብ አደረገ።


እንዲሁም ሕዝቡ ለግንበኞችና ለአናጢዎች የሚከፈለውን ገንዘብ ሰጡ፤ ከሊባኖስ ዛፍ ቈርጠው በኢዮጴ የባሕር ጠረፍ በኩል እንዲልኩላቸው ለጢሮስና ለሲዶና ከተሞች ነዋሪዎች ምግብን፥ መጠጥንና የወይራ ዘይትን ላኩ፤ ይህም ሁሉ የሆነው የፋርስ ንጉሠ ነገሥት ቂሮስ በሰጣቸው ፈቃድ መሠረት ነበር።


ወደ ይሁዳ ምድር ሄደን የታላቁ አምላክ ቤተ መቅደስ በድንጋይና በጠርብ እንጨት ሲሠራ ማየታችን ለግርማዊነትዎ የታወቀ ይሁን፤ ሥራውም በሽማግሌዎቹ መሪነት በጥንቃቄና በፍጥነት እየተሠራ ነው።


በዚሁ አጋጣሚ ይልቁንም የቤተ መቅደሱን ሥራ እንድታግዙአቸው አዝዣችኋለሁ። ስለዚህም አስፈላጊው የማሠሪያ ገንዘብ ሁሉ ከኤፍራጥስ ምዕራባዊ ክፍል ከተሰበሰበው የመንግሥት ግብር ሳይዘገይ ወጪ እየሆነ ይሰጣቸው፤ ሥራውም መሰናከል አይገባውም።


በዚህ ዐይነት በኢየሩሳሌም ስላለው መቅደስህ ነገሥታት መባን ያመጡልሃል።


የተርሴስ ደሴቶች ነገሥታት ስጦታ ያቅርቡለት፤ የሳባና የዐረብ ነገሥታት እጅ መንሻ ያምጡለት።


ነገሥታት አሳዳጊ አባቶችሽ ይሆናሉ፤ እቴጌዎቻቸውም ሞግዚቶችሽ ይሆናሉ፤ ግንባራቸውንም ወደ ምድር ዝቅ አድርገው ይሰግዱልሻል። የእግርሽንም ትቢያ ይልሳሉ፤ ከዚህም የተነሣ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቂአለሽ፤ የእኔን ርዳታ ለማግኘት የሚጠባበቁ ከቶ አያፍሩም።”


ነገር ግን ምድር ሴቲቱን ረዳቻት፤ አፍዋንም ከፈተችና ዘንዶው ከአፉ ተፍቶ ያፈሰሰውን ውሃ መጠጠች።


跟着我们:

广告


广告