Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዕዝራ 5:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 “ንጉሥ ሆይ! እንግዲህ በእርግጥ ይህ ቤተ መቅደስ በኢየሩሳሌም ይሠራ ዘንድ ንጉሥ ቂሮስ የሰጠው ትእዛዝ መኖር አለመኖሩን ለማረጋገጥ በባቢሎን ቤተ መንግሥት የጽሑፍ ማስረጃዎችን አስመርምረህ በዚህ ጉዳይ ላይ ምን ዐይነት ውሳኔ ቢሰጥ እንደምትፈቅድ ታስታውቀን ዘንድ እንለምናለን።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 አሁንም ንጉሡን ደስ የሚያሠኘው ቢሆን፣ ይህ የእግዚአብሔር ቤት በኢየሩሳሌም እንዲሠራ ንጉሥ ቂሮስ በርግጥ ትእዛዝ ሰጥቶ እንደ ሆነ በባቢሎን ቤተ መንግሥት ግምጃ ቤት የተቀመጡት መዛግብት እንዲመረመሩ ያድርግ፤ ከዚያም ንጉሡ ስለዚህ ጕዳይ የወሰነውን ይላክልን።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 “አሁንም ይህ ነገር በንጉሡ ዐይን መልካም ቢሆን ይህ የእግዚአብሔር ቤት በኢየሩሳሌም እንዲሠራ ከንጉሡ ከቂሮስ ታዝዞ እንደሆነ በባቢሎን ባለው በንጉሡ ቤተ መዛግብት ይመርመር፥ ስለዚህም ነገር ንጉሡ ፈቃዱን ይላክልን።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 አሁ​ንም ይህ ነገር በን​ጉሡ ዐይን መል​ካም ቢሆን ይህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ይሠራ ዘንድ ከን​ጉሡ ከቂ​ሮስ ታዝዞ እንደ ሆነ በባ​ቢ​ሎን ባለው በን​ጉሡ ቤተ መዛ​ግ​ብት ይመ​ር​መር፤ ስለ​ዚ​ህም ነገር ንጉሡ ፈቃ​ዱን ይላ​ክ​ልን።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 አሁንም ይህ ነገር በንጉሡ ዓይን መልካም ቢሆን ይህ የእግዚአብሔር ቤት በኢየሩሳሌም ይሠራ ዘንድ ከንጉሡ ከቂሮስ ታዝዞ እንደ ሆነ በባቢሎን ባለው በንጉሡ ቤተ መዛግብት ይመርመር፤ ስለዚህም ነገር ንጉሡ ፈቃዱን ይላክልን።”

参见章节 复制




ዕዝራ 5:17
4 交叉引用  

ስለዚህ የቀድሞ አባቶችዎ ታሪክ ያለባቸው መዛግብት እንዲመረመሩ ትእዛዝ ይሰጡ ዘንድ እናሳስባለን፤ ይህ በሚደረግበት ጊዜ ይህች ከተማ ዘወትር ዐመፀኛ እንደ ነበረችና ከጥንት ጀምሮ ለነገሥታትና በየክፍላተ ሀገሩ ለሚገኙ አገረ ገዢዎች ምን ያኽል አስቸጋሪ እንደ ነበረች ማስረጃ ያገኛሉ፤ ከጥንት ጀምሮ ሕዝቦችዋ ዐመፀኞች ነበሩ፤ ከዚህ በፊት ከተማይቱ እንድትደመሰስ የተደረገበትም ምክንያት ይኸው ነበር።


በእርሱም መነሻነት ጥብቅ ምርምርና ጥናት እንዲደረግ ትእዛዝ ሰጥቻለሁ፤ ከጥናቱም የተገኘው ውጤት ኢየሩሳሌም ከጥንት ጀምሮ በመንግሥት ሥልጣን ላይ ስታምፅ የኖረች ዐመፀኞችና አስቸጋሪዎች ሰዎች የሞሉባት ከተማ እንደ ነበረች ያስረዳል፤


እግዚአብሔር የምሥጢር አምላክ ስለ ሆነ እናከብረዋለን፤ ነገሥታትን የምናከብራቸው ነገሮችን መርምረው በመግለጣቸው ነው።


跟着我们:

广告


广告