Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 9:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ግድያውም በሚፈጸምበት ጊዜ እኔ ብቻዬን ቀርቼ ሳለሁ በግንባሬም ወደ መሬት ተደፍቼ በመጮኽ “ልዑል እግዚአብሔር ሆይ! ወዮ! በእስራኤል የተረፉትን ሁሉ እስክትፈጅ ድረስ በኢየሩሳሌም ላይ ይህን ያህል ትቈጣለህን?” አልኩ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 እነርሱ እየገደሉ እኔም ብቻዬን ሳለሁ፣ በግንባሬ ተደፍቼ፣ “ወዮ! ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ በኢየሩሳሌም ላይ መዓትህን አውርደህ የእስራኤልን ቅሬታዎች ሁሉ ልታጠፋ ነውን?” በማለት ጮኽሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 እነርሱ ሲገድሉ እኔ ብቻዬን ቀርቼ ሳለሁ በግምባሬ ተደፍቼ ጮኽሁ፥ እንዲህም አልሁ፦ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ ወዮ! መዓትህን በኢየሩሳሌም ላይ ስታፈስስ የእስራኤልን ትሩፍ ሁሉ ታጠፋለህን?

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ሲገ​ድ​ሉም እኔ ብቻ​ዬን ቀርቼ ሳለሁ በግ​ን​ባሬ ተደ​ፍቼ፥ “ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ! ወዮ! መዓ​ት​ህን በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ላይ ስታ​ፈ​ስስ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ቅሬታ ሁሉ ታጠ​ፋ​ለ​ህን?” ብዬ ጮኽሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ሲገድሉም እኔ ብቻዬን ቀርቼ ሳለሁ በግምባሬ ተደፍቼ፦ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ ወዮ! መዓትህን በኢየሩሳሌም ላይ ስታፈስስ የእስራኤልን ቅሬታ ሁሉ ታጠፋለህን? ብዬ ጮኽሁ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 9:8
16 交叉引用  

ወደ እርሱ ቀረብ ብሎ እንዲህ አለ፤ “በእርግጥ በደል የሌለባቸውን ደጋግ ሰዎች ከኃጢአተኞች ጋር ታጠፋለህን?


ዳዊትም መልአኩ ኢየሩሳሌምን ለመደምሰስ ሰይፉን በእጁ እንደ ያዘ በምድርና በሰማይ መካከል ቆሞ አየው፤ በዚህ ጊዜ ዳዊትና ማቅ ለብሰው የነበሩት የሕዝቡ አለቆች በሙሉ በግንባራቸው በመሬት ላይ ተደፉ።


የምሽትም መሥዋዕት የሚቀርብበት ሰዓት በደረሰ ጊዜ በሐዘን ከተቀመጥኩበት ስፍራ ተነሣሁ፤ የቀደድኩትን ልብስ እንደ ለበስኩ፥ በጒልበቴም በመንበርከክ ወደ አምላኬ ወደ እግዚአብሔር እጆቼን ዘርግቼ እንዲህ ስል ጸለይኩ፦


እኔም እንዲህ አልኩ፦ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! ነቢያቱ ‘ጦርነት ሆነ ራብ አይኖርም’ እያሉ ለሕዝቡ ይናገራሉ፤ ‘በምድራችን ዘላቂ ሰላም ብቻ እንደሚሰፍን እግዚአብሔር ተናግሮአል’ ይላሉ።”


እግዚአብሔር ሆይ! ይሁዳን ፈጽመህ ልትጥላት ነውን? የጽዮንንስ ሕዝብ እንደ ጠላህ መቅረትህ ነውን? ለመፈወስ እስከማንችል ድረስ፥ ይህን ያኽል እንድንጐዳ ማድረግህስ ስለምንድን ነው? ሰላም እናገኛለን ብለን ተስፋ አደረግን፥ ነገር ግን ምንም መልካም ነገር አልገጠመንም፤ ፈውስ እናገኛለን ብለን ተስፋ አደረግን፤ ነገር ግን ሽብር እየበዛ ሄደ።


እኔም፥ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! የኢየሩሳሌምን ሕዝብ ማታለል አይሆንብህምን? ‘ሰላም ይሆንላችኋል’ ብለሃቸው ነበር፤ እነሆ አሁን ሰይፍ በአንገታቸው ላይ ተቃጥቶአል” አልኩ።


እኔም ትንቢት በምናገርበት ጊዜ የበናያ ልጅ ፈላጥያ ወድቆ ሞተ፤ እኔም በግንባሬ ወደ መሬት ተደፍቼ በመጮኽ “ልዑል እግዚአብሔር ሆይ! በእስራኤል የተረፉትን ሁሉ ልትፈጅ ነውን?” አልኩ።


እኔም እንዲህ ስል መለስኩ፦ “ልዑል እግዚአብሔር ሆይ! ይህስ ከቶ አይሁን! እኔ ከቶ ረክሼ አላውቅም፤ ከሕፃንነቴ ጀምሮ የበከተ ወይም አውሬ የገደለው ከብትን ሥጋ የበላሁበት ጊዜ የለም፤ ጸያፍ ምግብም አልበላሁም።”


“አሁን እኔ በቅርቡ ቊጣዬንና መዓቴን አወርድባችኋለሁ፤ እንዳካሄዳችሁም እፈርድባችኋለሁ፤ በአጸያፊ ድርጊታችሁም ምክንያት እቀጣችኋለሁ።


በዚያን ጊዜ ሙሴና አሮን በሕዝቡ ሁሉ ፊት ወደ መሬት ተደፉ፤


ሙሴም ይህን በሰማ ጊዜ በግንባሩ ወድቆ ጸለየ፤


“ከእነዚህ ሰዎች ርቃችሁ ቁሙ፤ እኔ እነርሱን በአንድ ጊዜ እደመስሳቸዋለሁ!” ሁለቱም በግንባራቸው ወደ መሬት ተደፉ፤


ከዚህም በኋላ እንደገና አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ምንም ነገር ሳልበላና ሳልጠጣ በእግዚአብሔር ፊት በግንባሬ ተደፍቼ ቈየሁ። ይህንንም ያደረግኹት እግዚአብሔርን የሚያሳዝን ኃጢአት ሠርታችሁ እርሱን በማስቈጣታችሁ ምክንያት ነበር።


ኢያሱና የእስራኤል መሪዎች በሐዘን ልብሳቸውን ቀደዱ፤ በእግዚአብሔርም ታቦት ፊት እስከ ማታ ድረስ በግንባራቸው ተደፉ፤ ሐዘናቸውን ለመግለጥ በራሳቸው ላይ ትቢያ ነሰነሱ።


跟着我们:

广告


广告