Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 9:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ከዚህ በኋላ የእስራኤልን አምላክ ክብር የሚገልጥ ነጸብራቅ ቀድሞ ካረፈበት ከኪሩብ ላይ ተነሥቶ ወደ ቤተ መቅደሱ መግቢያ በር ሄደ፤ እግዚአብሔርም በፍታ የለበሰውንና የጽሕፈት ዕቃ ማኅደር የያዘውን ሰው፥ ጠራው፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 በዚህ ጊዜ የእስራኤል አምላክ ክብር ከነበረበት ከኪሩብ በላይ ተነሥቶ ወደ ቤተ መቅደሱ መድረክ ሄደ። እግዚአብሔርም በፍታ የለበሰውን በጐኑም የጽሕፈት ዕቃ ማኅደር ያነገበውን ሰው ጠራ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 የእስራኤልም አምላክ ክብር በላዩ ላይ አርፎ ከነበረበት ኪሩብ ተነሥቶ ወደ ቤቱ መግቢያ ሄዶ ነበር፥ በፍታ የለበሰውን በወገቡም የጸሐፊ ቀለም ቀንድ የያዘውን ሰው ጠራ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ ክብር በበ​ላዩ ከነ​በ​ረ​በት ኪሩብ ተነ​ሥቶ ወደ ቤቱ መድ​ረክ ሄዶ ነበር፤ በፍ​ታም የለ​በ​ሰ​ውን፥ የሰ​ን​ፔር መታ​ጠ​ቂ​ያም በወ​ገቡ የታ​ጠ​ቀ​ውን ሰው ጠራ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 የእስራኤልም አምላክ ክብር በበላዩ ከነበረበት ኪሩብ ተነሥቶ ወደ ቤቱ መድረክ ሄዶ ነበር፥ በፍታ የለበሰውን የጸሐፊውንም ቀለም ቀንድ በወገቡ የያዘውን ሰው ጠራ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 9:3
6 交叉引用  

የእግዚአብሔር ክብር ከኪሩብ ተነሥቶ ወደ ቤተ መቅደሱ መድረክ ሄደ፤ ደመና ቤቱን ሞላው፤ አደባባዩም በእግዚአብሔር ክብር ነጸብራቅ ተሞላ።


ስለዚህ ተነሥቼ ወደ ሸለቆው ወረድኩ፤ እዚያም በኬባር ወንዝ አጠገብ ባየሁት ሁኔታ የእግዚአብሔር ክብር ተገለጠልኝ፤ በግንባሬም ወደ መሬት ተደፋሁ፤


በዚያም የእስራኤል አምላክ ክብር ነበር፤ ይህም በኬባር ወንዝ ያየሁት ዐይነት ራእይ ነበር።


ስድስት ሰዎችም የመግደያ መሣሪያዎቻቸውን ይዘው ወደ ሰሜን ከሚመለከተው ከላይኛው በር መጡ፤ ከእነርሱም መካከል በፍታ የለበሰና የጽሕፈት ዕቃ ማኅደር በጐኑ የያዘ አንድ ሰው ነበር። ስድስቱም ሰዎች ገብተው በነሐሱ መሠዊያ አጠገብ ቆሙ።


跟着我们:

广告


广告