Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 8:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 እርሱም የሰው እጅ የሚመስል ነገር ወደ እኔ ዘርግቶ የራስ ጠጒሬን ያዘ፤ በዚሁ ራእይ የእግዚአብሔር መንፈስ ከምድር ወደ ሰማይ አነሣኝና ወደ ኢየሩሳሌም አደረሰኝ። በሰሜን በኩል ወደ ውስጠኛው አደባባይ በሚያስገባው ቅጽር በር አሳልፎ የእግዚአብሔርን ቅናት የሚቀሰቅስን የጣዖት ምስል ወዳለበት ስፍራ አደረሰኝ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 እርሱም እጅ መሳይ ዘርግቶ የራስ ጠጕሬን ያዘ፤ መንፈስም በምድርና በሰማይ መካከል አነሣኝ፤ እርሱም ቅናት የሚያነሣው ጣዖት ወደ ቆመበት፣ ወደ ውስጠኛው አደባባይ መግቢያ ወደ ሰሜን በር ወደ ኢየሩሳሌም በእግዚአብሔር ራእይ ወሰደኝ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 እጅ የሚመስል ዘረጋና በራስ ጠጉሬ ወሰደኝ፥ መንፈስም በምድርና በሰማይ መካከል አነሣኝ፥ በእግዚአብሔርም ራእዮች ወደ ኢየሩሳሌም፥ ቅናትን የሚያነሣሣ የቅናት ጣዖት ወደሚገኝበት፥ ወደ ሰሜን ወደሚመለከተው፥ ወደ ውስጠኛው አደባባይ በር መግቢያ አመጣኝ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 እጅ መሳ​ይ​ንም ዘረጋ፤ በራስ ጠጕ​ሬም ያዘኝ፤ መን​ፈ​ስም በም​ድ​ርና በሰ​ማይ መካ​ከል አነ​ሣኝ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ራእይ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ ሰሜን ወደ​ሚ​መ​ለ​ከ​ተው ወደ ውስ​ጠ​ኛው አደ​ባ​ባይ በር መግ​ቢያ ቅን​አት የተ​ባ​ለው ምስል ወደ አለ​በት አመ​ጣኝ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 እጅ መሳይንም ዘረጋ በራስ ጠጕሬም ያዘኝ መንፈስም በምድርና በሰማይ መካከል አነሣኝ፥ በእግዚአብሔርም ራእይ ወደ ኢየሩሳሌም ወደ ሰሜን ወደሚመለከተው ወደ ውስጠኛው አደባባይ በር መግቢያ አመጣኝ፥ በዚያም ቅንዓት የሚያነሣሣ የቅንዓት ጣዖት ተተክሎ ነበር።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 8:3
39 交叉引用  

እኔ ከዚህ እንደ ሄድኩ ወዲያውኑ የእግዚአብሔር መንፈስ አንተን ወዳልታወቀ ቦታ ቢወስድህ እኔ ምን ይበጀኛል? አንተ በዚህ ቦታ መኖርኽን ለአክዓብ ነግሬው ሳያገኝህ ቢቀር እርሱ እኔን በሞት ይቀጣኛል፤ ከልጅነቴ ጀምሬ እግዚአብሔርን የምፈራ ሰው መሆኔን አስታውስ።


ከነሐስ ተሠርቶ ለእግዚአብሔር የተለየውም መሠዊያ በዚያ አዲስ መሠዊያና በቤተ መቅደሱ መካከል ነበር፤ አካዝም ያንን መሠዊያ አስነሥቶ እርሱ ባሠራው በአዲሱ መሠዊያ በስተ ሰሜን በኩል አኖረው፤


“እነሆ! በዚህ ጠንካሮች የሆንን ኀምሳ ሰዎች አለን፤ እንሂድና ጌታህን እንፈልገው፤ ምናልባት የእግዚአብሔር መንፈስ አንሥቶ ወስዶ በአንድ ተራራ ላይ ወይም ሸለቆ ውስጥ አሳርፎት ይሆናል።” ኤልሳዕም “አትላኩአቸው” ሲል መለሰ።


በቤተ መቅደሱም ውስጥ የአሼራን ምስል አኖረ፤ ይህም ቤተ መቅደስ እግዚአብሔር ለዳዊትና ለልጁ ለሰሎሞን “ይህ በኢየሩሳሌም የሚገኘው ቤተ መቅደስ እኔ ለዘለዓለም እመለክበት ዘንድ ከዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች ግዛት ሁሉ የመረጥኩት ስፍራ ነው፤


የአሕዛብ አምልኮ በሚፈጽሙባቸው ስፍራዎቻቸው እግዚአብሔርን አስቈጡት፤ በጣዖቶቻቸውም አስቀኑት።


“በሰማይም ሆነ በምድር ወይም ከምድር በታች ባለው ውሃ ውስጥ ከሚኖሩት ነገሮች የማንኛውንም ዐይነት ምስል ጣዖት አድርገህ አትሥራ፤


እኔ እግዚአብሔር አምላክህ እጅግ ቀናተኛ ስለ ሆንኩ ተቀርጾ የተሠራውን ማንኛውም ጣዖት አታምልክ፤ አትስገድለትም፤ እኔ የሚጠሉኝን ሁሉ እቀጣለሁ፤ ዘራቸውንም ሁሉ እስከ ሦስትና አራት ትውልድ ድረስ እበቀላለሁ።


“እኔ እግዚአብሔር ቀናተኛ አምላክ ስለ ሆንኩ ከእኔ በቀር ለሌሎች አማልክት አትስገዱ፤


ይልቁንም የስሜ መጠሪያ እንዲሆን በተሠራው መቅደሴ አጸያፊ የሆኑ ጣዖቶቻቸውን በማቆም አርክሰውታል።


“የይሁዳ ሕዝብ ክፉ ነገር አድርገዋል፤ ይኸውም እኔ የምጠላቸውን ጣዖቶቻቸውን አስገብተው በውስጡ በማኖር ቤተ መቅደሴን አርክሰዋል።


በሠላሳኛው ዓመት፥ በአራተኛው ወር፥ ከወሩም በአምስተኛው ቀን በኬባር ወንዝ አጠገብ በአይሁድ ምርኮኞች መካከል ሳለሁ ሰማያት ተከፍተው የእግዚአብሔርን ራእይ አየሁ።


ወደ ውስጥ በሚገባበትም ጊዜ ኪሩቤል ከቤተ መቅደሱ በስተ ደቡብ በኩል ቆመው ነበር፤ በውስጥ በኩል ያለውንም አደባባይ ደመና ሞላው፤


የእግዚአብሔር መንፈስ ከምድር ወደ ላይ አንሥቶ በምሥራቅ ትይዩ ወደ ሆነው በእግዚአብሔር ቤት ወደ አለው ወደ ምሥራቁ በር አመጣኝ፤ እዚያም በቅጽር በሩ አጠገብ ኻያ አምስት ሰዎችን አየሁ፤ በእነርሱም መካከል የሕዝብ መሪዎች የሆኑት የዐዙር ልጅ አዛንያና የበናያ ልጅ ፈላጥያ ይገኙባቸዋል።


በራእይም የእግዚአብሔር መንፈስ ከምድር ወደ ላይ አንሥቶ በባቢሎን ወዳሉት ስደተኞች አመጣኝ፤ ከዚህ በኋላ ራእዩ ከእኔ ተለየ።


ከዚህ በኋላ የብራና ጥቅል የያዘ እጅ ወደ እኔ ተዘርግቶ አየሁ።


ከዚህ በኋላ የእግዚአብሔር መንፈስ ወደ ላይ ከፍ አደረገኝ፤ ከበስተኋላዬም “በሰማይ ለሚኖር እግዚአብሔር ምስጋናና ክብር ይሁን!” የሚል ታላቅ ድምፅ ሰማሁ።


መንፈስ አንሥቶ በወሰደኝ ጊዜ ስሜቴ በምሬትና በቊጣ ተሞልቶ ነበር፤ የእግዚአብሔርም ኀይል በእኔ ላይ በርትቶ ነበር።


የእግዚአብሔር ኀይል በእኔ ላይ መጣ፤ የእርሱም መንፈስ እኔን ወስዶ ብዙ አጥንቶች በተከማቸበት ሸለቆ ውስጥ አኖረኝ፤


በእግዚአብሔርም ራእይ ወስዶ በእስራኤል ምድር በአንድ ከፍተኛ ተራራ ላይ አኖረኝ፤ እዚያም አንድ ብዙ ቤቶች የተሠሩበትን ከተማ የሚመስል ከተራራው በስተደቡብ በኩል አየሁ።


የእግዚአብሔር መንፈስ ወደ ላይ አነሣኝ፤ ወስዶም ወደ ውስጠኛው አደባባይ አስገባኝ፤ ቤተ መቅደሱም በእግዚአብሔር ክብር ተሞልቶ ነበር፤


ነገሥታቱ የቤተ መንግሥታቸውን መድረኮችና መቃኖች ወደ ቤተ መቅደሴ መድረኮችና መቃኖች አስጠግተው ስለ ሠሩ፥ የእኔን ቤትና የእነርሱን ቤት የሚለይ አንድ ግንብ ብቻ ሆኖአል፤ በፈጸሙትም አጸያፊ ድርጊት ሁሉ ቅዱስ ስሜን አሰድበዋል፤ ከዚህም የተነሣ በቊጣዬ አጠፋኋቸው።


“ስለዚህ ሕያው አምላክ እንደ መሆኔ እኔ እግዚአብሔር የምለው ይህ ነው፤ ክፋትና ርኲሰት የተሞላበት ነገር ሁሉ በመፈጸም ቤተ መቅደሴን በማርከሳችሁ ምክንያት እኔም ያለ ምሕረት እንድትዋረዱ አደርጋለሁ።


መመኪያቸው ከሆኑት ውብ ጌጦቻቸው አስጠሊና አጸያፊ ጣዖቶቻቸውን ሠሩባቸው፤ ስለዚህ እነዚህን ጌጦቻቸውን በእነርሱ ዘንድ አረክሳቸዋለሁ።


እግዚአብሔርም፦ “የሰው ልጅ ሆይ! በስተ ሰሜን በኩል ተመልከት!” አለኝ፤ በተመለከትኩም ጊዜ በቅጽር በሩ ፊት ለፊት ባለው መሠዊያ አጠገብ የእግዚአብሔርን ቅናት የሚቀሰቅስ ምስል ነበር።


ስድስት ሰዎችም የመግደያ መሣሪያዎቻቸውን ይዘው ወደ ሰሜን ከሚመለከተው ከላይኛው በር መጡ፤ ከእነርሱም መካከል በፍታ የለበሰና የጽሕፈት ዕቃ ማኅደር በጐኑ የያዘ አንድ ሰው ነበር። ስድስቱም ሰዎች ገብተው በነሐሱ መሠዊያ አጠገብ ቆሙ።


ከዚያ በኋላ አንዳች እጅ ዳሰሰኝ፤ ገና እየተንቀጠቀጥኩ ስለ ነበር ደግፎ በእጄና በጒልበቴ እንድቆም አደረገኝ።


ያ ሰው የሚመስለው መልአክ እንደገና በዳሰሰኝ ጊዜ ብርታት አገኘሁ።


የሰው እጅ ጣቶች በድንገት ታይተው በቤተ መቅደሱ መቅረዝ ፊት ለፊት ባለው በተለሰነው የቤተ መንግሥቱ ግድግዳ ላይ መጻፍ ጀመሩ፤ እነዚያም ጣቶች በሚጽፉበት ጊዜ ንጉሡ አየ።


ከውሃው ከወጡ በኋላ የጌታ መንፈስ ፊልጶስን ወሰደው፤ ጃንደረባውም ዳግመኛ አላየውም፤ ይሁን እንጂ ደስ እያለው ጒዞውን ቀጠለ።


እግዚአብሔርን በጣዖት አምልኮ አስቀኑት፤ በሚያደርጉትም ክፉ ነገር ሁሉ አስቈጡት።


እውነተኛ ባልሆኑ አማልክት አስቀንተውኛል፤ ዋጋቢስ በሆኑ ጣዖቶቻቸው አስቈጥተውኛል፤ በተናቀ ሕዝብ አስቀናቸዋለሁ፤ በማያስተውል ሕዝብ አስቈጣቸዋለሁ።


አምላካችሁ እግዚአብሔር የሚባላ እሳት ነው፤ ቀናተኛ አምላክ ነው።


እኔ አምላክህ እግዚአብሔር፥ እኔን ትተው ሌሎች አማልክትን የሚያመልኩትን ሰዎች፥ የአባቶችን ኃጢአት በልጆች፥ እስከ ሦስት ትውልድ ድረስ የምበቀል ቀናተኛ አምላክ ስለ ሆንኩ እነዚያን የተቀረጹ ምስሎች አትስገድላቸው፤ አታምልካቸውም።


ባዕዳን አማልክትን ብታመልኩ በመካከላችሁ የሚገኘውን የአምላካችሁን ቊጣ ታስነሣላችሁ፤ አምላካችሁ እግዚአብሔር ቀናተኛ አምላክ ስለ ሆነ ከምድር ገጽ ጠራርጎ ያጠፋችኋል፤


ኢያሱም ለሕዝቡ እንዲህ አለ፤ “እግዚአብሔር ቅዱስና ቀናተኛ አምላክ ስለ ሆነ፥ እናንተ እርሱን ማገልገል አትችሉም፤ የምትሠሩትን ዐመፅና ኃጢአት ሁሉ ይቅር አይልም፤


跟着我们:

广告


广告