Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 7:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ከቶ አልራራላችሁም፤ ምሕረትም አላደርግላችሁም። በርኲሰት ላይ እስካላችሁ ድረስ እንደ አካሄዳችሁ እቀጣችኋለሁ፤ በዚያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 በርኅራኄ ዐይን አልመለከትሽም፤ ምሕረትም አላደርግልሽም፤ ስለ አካሄድሽና በመካከልሽ ስላለው ጸያፍ ተግባር፣ ተገቢውን ቅጣት እከፍልሻለሁ፤ በዚያ ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።’

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ዓይኔ አይራራልሽም እኔም አላዝንም፤ መንገድሽን በአንቺ ላይ እመልስብሻለሁ፥ ርኩሰቶችሽም በመካከልሽ ይሆናሉ፥ በዚያን ጊዜ እኔ ጌታ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ዐይ​ኔም አይ​ራ​ራ​ል​ሽም፤ እኔም ይቅር አል​ል​ሽም፤ መን​ገ​ድ​ሽ​ንም አመ​ጣ​ብ​ሻ​ለሁ፤ ርኵ​ሰ​ት​ሽም በመ​ካ​ከ​ልሽ ነው፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ዓይኔም አይራራልሽም እኔም አላዝንም፥ መንገድሽንም አመጣብሻለሁ ርኵሰትሽም በመካከልሽ ይሆናል፥ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 7:4
24 交叉引用  

ያን ጊዜ አባቶችንና ልጆቻቸውን ሁሉንም እንደ ማድጋ እርስ በርሳቸው አጋጫቸዋለሁ፤ ምንም ዐይነት ሐዘኔታ፥ ርኅራኄ ወይም ምሕረት እነርሱን ከማጥፋት ሊያግደኝ አይችልም።”


እንደ በድን ሕይወት በሌላቸው ጣዖቶች ርስቴን ስላረከሱና በሐሰተኞች አማልክታቸው ስለ ሞሉአት ስለ ኃጢአታቸውና ስለ ክፋታቸው በእጥፍ እቀጣቸዋለሁ።”


ባቢሎናውያን ስላደረጉትም ክፋት ሁሉ ቅጣታቸውን እንዲያገኙ አደርጋለሁ፤ ብዙ ሕዝቦችና ታላላቅ ነገሥታት ባሪያ አድርገው ይገዙአቸዋል።’ ”


ልባቸው ርኩስና አጸያፊ የሆኑ ጣዖቶችን የሚከተሉትን ግን እንደ ሥራቸው እከፍላቸዋለሁ፤” ይህን የተናገረ ልዑል እግዚአብሔር ነው።


አሁን በሕዝብ ተሞልተው የሚታዩ ከተሞች ይጠፋሉ፤ አገሪቱም ምድረ በዳ ትሆናለች፤ በዚያን ጊዜ እነርሱ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ያውቃሉ።’ ”


በልጅነትሽ ወራት ያደረግኹልሽን ሁሉ ረሳሽ፤ በፈጸምሽውም ክፉ ሥራ አስቈጣሽኝ፤ ስለዚህ እኔም በሠራሽው ኃጢአት መጠን ዋጋሽን እንድትቀበይ አደረግሁ፤ በፈጸምሽው አጸያፊ ሥራ ሁሉ ላይ የዝሙትን ርኲሰት መጨመርሽ ለምን ይሆን?” ይህን የተናገረ ልዑል እግዚአብሔር ነው።


ስለዚህ ቊጣዬን በእነርሱ ላይ አወርዳለሁ፤ በኀይለኛ ቊጣዬም አጠፋቸዋለሁ፤ በደላቸውንም በራሳቸው ላይ እመልሳለሁ።” ይህን የተናገረ ልዑል እግዚአብሔር ነው።


የእኅትሽን አካሄድ ስለ ተከተልሽ እርስዋ የጠጣችውን የቅጣት ጽዋ እንድትጠጪ አደርግሻለሁ።”


እናንተም ሁለት እኅትማማቾች ስለ ስድነታችሁና ለጣዖቶች በመስገድ ስለ ፈጸማችሁት ኃጢአት እቀጣችኋለሁ፤ በዚያን ጊዜ እኔ ልዑል እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ።”


እኔ ልዑል እግዚአብሔር ‘አንድ ነገር የማደርግበት ጊዜ ቀርቦአል፤ አልገታም፤ አልምርም፤ ሐሳቤን አለውጥም፤ እንደ አካሄድሽና እንደ ሥራሽ እፈርድብሻለሁ’ ” ብዬ ተናግሬአለሁ።


እነርሱ በፈጸሙአቸው አጸያፊ ነገሮች ሁሉ ምክንያት ምድሪቱን ባድማና ወና በማደርግበት ጊዜ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ያውቃሉ።”


“ስለዚህ ሕያው አምላክ እንደ መሆኔ እኔ እግዚአብሔር የምለው ይህ ነው፤ ክፋትና ርኲሰት የተሞላበት ነገር ሁሉ በመፈጸም ቤተ መቅደሴን በማርከሳችሁ ምክንያት እኔም ያለ ምሕረት እንድትዋረዱ አደርጋለሁ።


በእርግጥም እጄን ዘርግቼ አገራቸውን አጠፋታለሁ፤ ከደቡባዊው በረሓ አንሥቶ በሰሜን በኩል እስከምትገኘው እስከ ሪብላ ከተማ ድረስ ባድማ አደርጋታለሁ፤ እስራኤላውያን የሚኖሩበትን ስፍራ ሁሉ አንድም ሳይቀር አጠፋለሁ፤ በዚያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንድ አሆንኩ ሰዎች ሁሉ ያውቃሉ።”


የተገደሉት በአካባቢያችሁ ይጣላሉ፤ ከዚያ በኋላ እናንተ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ።


ንጉሡ ያለቅሳል፤ መስፍኑም ሙሉ በሙሉ ተስፋ ይቈርጣል፤ ሕዝቡም ከፍርሃት የተነሣ ይርበደበዳሉ፤ እንደ አካሄዳችሁ እቀጣችኋለሁ፤ በሌሎች ላይ በፈረዳችሁት ዐይነት እፈርድባችኋለሁ፤ በዚህም እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ።”


“የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! አሁን መጥፊያችሁ ደርሶአል። ቊጣዬን አወርድባችኋለሁ፤ እንደ አካሄዳችሁም እፈርድባችኋለሁ ስለ ርኲሰታችሁም ሁሉ እቀጣችኋለሁ።


ከቶ አልራራላችሁም፤ ምሕረትም አላደርግላችሁም፤ በርኲሰት ላይ እስካላችሁ ድረስ እንደ አካሄዳችሁ እቀጣችኋለሁ፤ በዚያን ጊዜ የምቀጣችሁ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ።”


ስለዚህ ቊጣዬን አወርድባቸዋለሁ፤ ራርቼም አልተዋቸውም፤ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ወደ እኔ ቢጮኹም አላደምጣቸውም።”


ስለዚህ አልራራላቸውም፤ ምሕረትም አላደርግላቸውም፤ እነርሱ በሌሎች ላይ ያደረጉትን ሁሉ በእነርሱ ላይ መልሼ አደርግባቸዋለሁ።”


እግዚአብሔር በይሁዳ ሕዝብ ላይ የሚያቀርበው ወቀሳ አለው፤ የያዕቆብንም ልጆች እንደ አካሄዳቸው ይቀጣቸዋል፤ ባደረጉትም ክፉ ሥራ መጠን ዋጋቸውን ይከፍላቸዋል።


የቅጣት ቀን ደርሶአል፤ እስራኤላውያንም የበቀል ቀን መቃረቡን ይወቁ፤ በእናንተ በደልና ጥላቻ ምክንያት ነቢይን እንደ ሞኝ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያደረበትን ሰው እንደ ዕብድ ትቈጥሩታላችሁ።


እርሱም “አሞጽ ሆይ! የምታየው ነገር ምንድን ነው?” ብሎ ጠየቀኝ። እኔም “ቱምቢ ነው” አልኩ። ጌታም እንዲህ አለኝ፦ “በቱምቢ ተስተካክሎ እንዳልተሠራ ቅጽር ሕዝቤ እስራኤል ጠማሞች ሆነው ስለ ተገኙ ይህ ቱምቢ የእስራኤልን ጠማማነት ማሳያ ምሳሌ ነው፤ ሳልቀጣቸውም አላልፍም።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እኔም ከእንግዲህ ወዲህ በምድር ላይ ለሚኖር ለማንም ሰው ርኅራኄ አላደርግም፤ እኔ ራሴ እያንዳንዱን ሰው ለጐረቤቱና ለንጉሡ አሳልፌ እሰጣለሁ፤ እነርሱ ምድሪቱን ያጠፋሉ፤ እኔም ከእነርሱ እጅ አልታደጋቸውም።”


“በቀል የእኔ ነው፤ እኔ ተገቢ ዋጋን እከፍላለሁ” ያለው ማን መሆኑን እናውቃለን፤ እንዲሁም “እግዚአብሔር በሕዝቡ ላይ ይፈርዳል” ይላል ጌታ።


跟着我们:

广告


广告