Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 5:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 በዚህም ምክንያት እኔ ልዑል እግዚአብሔር በአንቺ በኢየሩሳሌም ላይ በቊጣ የተነሣሁብሽ መሆኔን እገልጥልሻለሁ፤ ሕዝቦች ሁሉ እያዩ በፍርድ እቀጣሻለሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 “ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘እነሆ፤ እኔ ራሴ በአንቺ ላይ ተነሥቻለሁ፤ በአሕዛብም ፊት ፍርድ አመጣብሻለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ እኔ ራሴ በአንቺ ላይ ነኝ፥ አገሮችም እያዩ በመካከልሽ ፍርድን አመጣብሻለሁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ እኔ ራሴ በአ​ንቺ ላይ ነኝ፤ በአ​ሕ​ዛ​ብም ፊት ፍር​ድን በመ​ካ​ከ​ልሽ አደ​ር​ጋ​ለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ እኔ ራሴ በአንቺ ላይ ነኝ፥ አሕዛብም እያዩ ፍርድን በመካከልሽ አደርጋለሁ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 5:8
30 交叉引用  

አንቺም ኢየሩሳሌም ሆይ፥ በሜዳ ላይ እንደሚገኝ ቋጥኝ ከሸለቆዎች በላይ ከፍ ብለሽ ትታዪአለሽ፤ ነገር ግን እኔ እዋጋሻለሁ፤ አንቺ ግን ማንም የሚደፍርሽና ምሽጎችሽን ጥሶ የሚገባ ያለ አይመስልሽም፤


እኔ ራሴ በሚነድ ቊጣ፥ በታላቅ ተግሣጽ በኀይሌና በሥልጣኔ አንተን እዋጋለሁ።


በስደት እንዲበታተኑ ባደረግሁባቸው በምድር መንግሥታት ሁሉ ዘንድ የተጠሉ፥ የተሰደቡ፥ የመነጋገሪያ ርእስ የሆኑ፥ መሳለቂያና የተወገዙ እንዲሆኑ አደርጋቸዋለሁ።


በጎች የአውሬ ሰለባ እንደሚሆኑ እነርሱንም ያገኛቸው ሁሉ አደጋ ጣለባቸው፤ ጠላቶቻቸውም ‘እኛ እኮ ምንም አልበደልንም፤ ይህ ሁሉ ጥፋት በእነርሱ ላይ የደረሰባቸው የቀድሞ አባቶቻቸው ተስፋ አድርገውበት በኖሩት አምላክ ላይ በማመፃቸው ምክንያት ነው፤ እነርሱም እንደ አባቶቻቸው ለእርሱ ታማኞች ሆነው መኖር ይገባቸው ነበርና ነው።’


እግዚአብሔር እንደ ጠላት እስራኤልን አጠፋ፤ ቤተ መንግሥቶችዋን አወደመ፤ ምሽጎችዋን አፈራረሰ፤ በይሁዳ ሕዝብም ለቅሶና ዋይታን አበዛ።


ቀኑን ሙሉ እኔን ብቻ መላልሶ ቀጣኝ።


እናንተን ከከተማይቱ አስወጥቼ ለባዕዳን ሕዝቦች አሳልፌ በመስጠት እፈርድባችኋለሁ።


ስለዚህ ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላቸዋል፦ “ሐሰትን ስለ ተናገራችሁና ራእያችሁም ውሸት ስለ ሆነ እኔ በእናንተ ላይ እነሣለሁ። ይህንን የተናገርኩ እኔ ጌታ እግዚአብሔር ነኝ።


እቈጣቸዋለሁ፤ ምንም እንኳ ለጊዜው ከእሳቱ ቢያመልጡ እሳቱ ግን ይበላቸዋል፤ እነርሱንም በምትቈጣበት ጊዜ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ።


ቤቶችሽን በእሳት ያቃጥላሉ፤ በብዙ ሴቶች ፊት ፍርድን ተግባራዊ ያደርጉብሻል፤ በዚህ ዐይነት አመንዝራነትሽንና ለወዳጆችሽ የዝሙት ዋጋ መክፈልሽን እንድትተዪ አደርግሻለሁ።


እንዲህም በላት! ‘እኔ በአንቺ ላይ ተነሥቼአለሁ፤ ሰይፉን ከሰገባው አውጥቼ ኃጢአተኛውንና ጻድቁን ከመካከልሽ አጠፋለሁ።


ለሕዝብዋም ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል በላቸው፦ እኔ በእናንተ ላይ ተነሥቼአለሁ፤ በእናንተ ላይ በማደርገው ድርጊት ሕዝቦች ያመሰግኑኛል፤ ፍርዴን ተግባራዊ በማደርግበትና ቅድስናዬን በምገልጥበት ጊዜ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ያውቃሉ።


ግብጽን በዚህ ዐይነት በምቀጣበት ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንኩ ያውቃሉ።”


እኔ ልዑል እግዚአብሔር የበጎቹን እረኞች እቃወማለሁ፤ በጎቹን ከእረኞች እጅ ወስጄ እንዳያሰማሩአቸው አደርጋለሁ፤ ከእንግዲህ ወዲህ እረኞቹ ራሳቸውን አይመግቡም፤ ለእነርሱም ምግብ እንዳይሆኑ በጎቼን ከእነርሱ አፍ አስጥላለሁ።


እኔ ልዑል እግዚአብሔር የምለውንም ሁሉ እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘የኤዶም ሕዝብ ሆይ! እነሆ እኔ እናንተን እቃወማለሁ፤ ምድራችሁንም ባድማና ወና ላደርግ በእናንተ ላይ ተነሥቼአለሁ።


ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ “የሰው ልጅ ሆይ! የሜሼክና የቱባል ሕዝብ ገዢ በሆነው በጎግ ላይ ትንቢት ተናገርበት፤ በእርሱም ላይ የተነሣሁ መሆኔን ንገረው።


“በኀይለኛ ቊጣዬ በእናንተ ላይ ፍርዴን ተግባራዊ አድርጌ በምቀጣችሁ ጊዜ በአካባቢአችሁ ለሚኖሩ ሕዝቦች የመሳለቂያ፥ የሽሙጥ፥ የማስጠንቀቂያ የድንጋጤ ምክንያት ትሆናላችሁ፤ ይህን የተናገርኩ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።


ነነዌ ሆይ! በአንቺ ላይ ተነሥቼአለሁ ይላል የሠራዊት አምላክ፤ ሠረገሎችሽንም አቃጥላለሁ፤ ደቦሎችሽንም ሰይፍ ይበላቸዋል፤ በምድር ላይ በአንቺ ተጠቂ የሚሆን እንዳይኖር አደርጋለሁ፤ የመልእክተኞችሽም ድምፅ ከእንግዲህ ወዲያ አይሰማም።


በዚህ ጊዜ ንጉሡ ተቈጣና ወታደሮቹን ልኮ እነዚያን ገዳዮች አስገደለ፤ ከተማቸውንም በእሳት እንዲያቃጥሉ አደረገ፤


እግዚአብሔር ለእንደዚህ ያለው ሰው ይቅርታ አያደርግም፤ ይልቁንም የእግዚአብሔር ቊጣና ቅናት በእርሱ ላይ እንደ እሳት ይነዳል፤ እግዚአብሔርም እንደዚህ ያለውን ሰው ፈጽሞ እስኪደመስሰው ድረስ በዚህ መጽሐፍ የተጻፉት መቅሠፍቶች ሁሉ ይወርዱበታል።


跟着我们:

广告


广告