Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 5:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ከበባው ከተፈጸመ በኋላ ከሦስቱ አንዱን እጅ የከተማውን ንድፍ በሠራህበት ጡብ መካከል አቃጥለው፤ ሁለተኛውን አንድ ሦስተኛ እጅ ቈራርጠህ የከተማው ንድፍ በተሠራበት ጡብ ዙሪያ አኑረው። ሦስተኛውን አንድ ሦስተኛ እጅ ደግሞ ለነፋስ በትነው፤ እኔም በሰይፍ አሳድደዋለሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 የከበባው ጊዜ ሲፈጸም የጠጕሩን ሢሶ በከተማው ውስጥ አቃጥለው፤ ሌላውን ሢሶ ጠጕር በከተማዪቱ ዙሪያ ሁሉ በሰይፍ ቈራርጠው፤ የቀረውንም ሢሶ ደግሞ ለነፋስ በትነው፤ እኔም በተመዘዘ ሰይፍ አሳድዳቸዋለሁና።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 የመከበብም ወራት ሲፈጸም አንድ ሦስተኛውን በከተማይቱ መካከል በእሳት ታቃጥለዋለህ፥ አንድ ሦስተኛውን ወስደህ ዙሪያውን በሰይፍ ትመታዋለህ፥ አንድ ሦስተኛውን ወደ ነፋስ ትበትነዋለህ፥ እኔም ከኋላቸው ሰይፍ እመዝዛለሁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 የእ​ስ​ራ​ት​ህም ወራት በተ​ፈ​ጸመ ጊዜ በከ​ተ​ማ​ዪቱ መካ​ከል ሢሶ​ውን በእ​ሳት ታቃ​ጥ​ላ​ለህ፤ ሢሶ​ው​ንም ወስ​ደህ ዙሪ​ያ​ውን በጎ​ራዴ ትመ​ታ​ለህ፤ ሢሶ​ው​ንም ወደ ነፋስ ትበ​ት​ና​ለህ፤ እኔም በኋ​ላ​ቸው ጎራዴ እመ​ዝ​ዛ​ለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 የመከበብም ወራት በተፈጸመ ጊዜ በከተማይቱ መካከል ሢሶውን በእሳት ታቃጥላለህ፥ ሢሶውንም ወስደህ ዙሪያውን በጐራዴ ትመታለህ፥ ሢሶውንም ወደ ነፋስ ትበትናለህ እኔም በኋላቸው ጐራዴ እመዝዛለሁ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 5:2
19 交叉引用  

አሁን ግን እግዚአብሔር የበረሓ ነፋስ ጠራርጎ እንደሚወስደው ገለባ ይበታትናችኋል።


‘ታዲያ ወዴት እንሂድ?’ ብለው ቢጠይቁህ፥ ከዚህ በፊት እንዲህ ብዬ የነገርኳቸውን አስታውሳቸው፤ ‘በመቅሠፍት እንዲሞቱ የተፈረደባቸው በመቅሠፍት ይሞታሉ! በጦርነት እንዲሞቱ የተፈረደባቸው በጦርነት ይሞታሉ! በራብ እንዲሞቱ የተፈረደባቸውም በራብ ይሞታሉ። ተማርከው እንዲታሰሩ የተፈረደባቸው ወደ ምርኮ ይሂዱ።’


ለእነርሱና ለቀድሞ አባቶቻቸው ከሰጠኋት ከዚህች ምድር እስኪጠፉ ድረስ በጦርነት፥ በራብና በቸነፈር እንዲያልቁ አደርጋለሁ።”


የተናገርኩትም ቃል ይህ ነበር፦ “በከተማይቱ የሚቀሩ ሁሉ በጦርነት፥ በረሀብ ወይም በወረርሽኝ ይሞታሉ፤ ወደ ባቢሎናውያን ሄዶ እጁን የሚሰጥ ግን አይገደልም፤ እርሱ ሕይወቱን ለማትረፍ ያመልጣል።”


ሴዴቅያስ በይሁዳ በነገሠ በዘጠነኛው ዓመት በዐሥረኛው ወር የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ከሠራዊቱ ሁሉ ጋር መጥቶ በኢየሩሳሌም ላይ ከበባ አደረገ።


ሴዴቅያስ በነገሠ በዐሥራ አንደኛው ዓመት፥ በአራተኛው ወር፥ በዘጠነኛው ቀን የከተማይቱ ቅጽሮች ተጣሱ።


ስለዚህ የእስራኤል አምላክ እኔ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የማደርገውን ነገር ልንገራችሁ፤ ይህ ሕዝብ ምግቡ መራራ መጠጡም የተመረዘ ውሃ እንዲሆንበት አደርጋለሁ።


እነርሱም ሆኑ የቀድሞ አባቶቻቸው በማያውቁአቸው አሕዛብ መካከል እበትናቸዋለሁ፤ እስከማጠፋቸውም ድረስ በሰይፍ አሳድዳቸዋለሁ።”


የቅርብ አማካሪዎቹንና የክብር ዘብ ጠባቂዎቹን ሁሉ በየአቅጣጫው እበትናቸዋለሁ፤ ከኋላቸውም ሆኜ በሰይፍ አሳድዳቸዋለሁ።


ምርጥ የሆኑ ወታደሮቹ በጦር ሜዳ ይገደላሉ፤ ከሞት የሚያመልጡትም በየአቅጣጫው ይበተናሉ፤ በዚያን ጊዜ ይህን የተናገርኩት እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ።”


በዚህም ምክንያት በኢየሩሳሌም ያሉ ወላጆች በእርግጥ ልጆቻቸውን ይበላሉ፤ ልጆችም ወላጆቻቸውን ይበላሉ፤ በዚህ ዐይነት ሁላችሁንም እቀጣለሁ፤ የተረፉትንም በአራቱ ማእዘን እበትናቸዋለሁ።


ከሕዝባችሁ አንድ ሦስተኛው እጅ በራብና በበሽታ ያልቃል፤ አንድ ሦስተኛው ከከተማው ውጪ በሰይፍ ይገደላል፤ ሌላው ሦስተኛ እጅ በአራቱ ማእዘን በነፋስ እንዲበተን አድርጌ በኋላ በሰይፍ አሳድደዋለሁ።


በከተማው ዙሪያ በሰይፍ ቈራርጠው፤ ደግሞም ከዚሁ ጥቂት ጠጒር ወስደህ በመጐናጸፊያህ ጫፍ ላይ ቋጥረው።


በእናንተም ላይ ጦርነት አምጥቼ በባዕዳን አገሮች ሁሉ እበትናችኋለሁ፤ ሰይፍንም አስመዝዝባችኋለሁ፤ ምድራችሁ ሰው አልባ፥ ከተሞቻችሁም ውድማ ይሆናሉ፤


በጠላቶቻቸው እጅ ተማርከው ቢወሰዱም እዚያ እንዲገደሉ አደርጋለሁ፤ በዚህ ዐይነት እኔ በእነርሱ ላይ የማደርገው ትኲረት ይጐዳቸዋል እንጂ አይጠቅማቸውም።”


በአገሪቱ ላይ ካሉት ሕዝቦች ከሦስቱ ሁለቱ እጅ ተመተው ይሞታሉ፤ ሆኖም ከሦስቱ አንዱ እጅ ይቀራል።


跟着我们:

广告


广告