Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 5:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 “ስለዚህ ሕያው አምላክ እንደ መሆኔ እኔ እግዚአብሔር የምለው ይህ ነው፤ ክፋትና ርኲሰት የተሞላበት ነገር ሁሉ በመፈጸም ቤተ መቅደሴን በማርከሳችሁ ምክንያት እኔም ያለ ምሕረት እንድትዋረዱ አደርጋለሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ስለዚህ በሕያውነቴ እምላለሁ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ መቅደሴን በረከሱ ምስሎችሽና በጸያፍ ተግባርሽ ሁሉ ስላጐደፍሽ፣ ፊቴን ከአንቺ እመልሳለሁ፤ በርኅራኄ አልመለከትሽም፤ አልምርሽም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ስለዚህ እኔ ሕያው ነኝና ይላል ጌታ እግዚአብሔር በእድፍሽ ሁሉና በርኩሰትሽም ሁሉ መቅደሴን ስላረከስሽ፥ እኔም አሳንስሻለሁ፥ ዓይኔም አይራራም እኔም አላዝንም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ስለ​ዚህ እኔ ሕያው ነኝና በእ​ድ​ፍ​ሽና በር​ኵ​ሰ​ትሽ መቅ​ደ​ሴን ስላ​ረ​ከ​ስሽ፥ ስለ​ዚህ በእ​ው​ነት እኔ አሳ​ን​ስ​ሻ​ለሁ፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ዐይ​ኔም አይ​ራ​ራም፤ እኔም ይቅር አል​ልም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ስለዚህ፥ እኔ ሕያው ነኝና በእድፍሽና በርኵሰትሽ መቅደሴን ስላረከስሽ፥ ስለዚህ በእውነት እኔ አሳንስሻለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፥ ዓይኔም አይራራም እኔም አላዝንም።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 5:11
48 交叉引用  

እግዚአብሔር እንዲመለክበት ባዘዘው ስፍራ ማለትም በቤተ መቅደስ ውስጥ አረማዊ መሠዊያዎችን አቆመ።


በቤተ መቅደሱም ውስጥ የአሼራን ምስል አኖረ፤ ይህም ቤተ መቅደስ እግዚአብሔር ለዳዊትና ለልጁ ለሰሎሞን “ይህ በኢየሩሳሌም የሚገኘው ቤተ መቅደስ እኔ ለዘለዓለም እመለክበት ዘንድ ከዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች ግዛት ሁሉ የመረጥኩት ስፍራ ነው፤


ንጉሥ አካዝ ባሠራቸው መኖሪያ ክፍሎች ጣራ ላይ በሚገኘው ቤተ መንግሥት የይሁዳ ነገሥታት አሠርተዋቸው የነበሩትን መሠዊያዎችና በቤተ መቅደሱ ሁለት አደባባዮች ንጉሥ ምናሴ አሠርቶአቸው የነበሩትን መሠዊያዎች ሁሉ ኢዮስያስ ደመሰሳቸው፤ መሠዊያዎቹንም አንከታክቶ ወደ ቄድሮን ሸለቆ ወስዶ ጣላቸው።


እግዚአብሔር ለዘለዓለም ስሙ ይጠራበታል ባለው ስፍራ፥ ማለትም በኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ ውስጥ አረማዊ መሠዊያዎችን ተከለ፤


በቤተ መቅደስም ውስጥ የጣዖት ምስልን አቆመ፤ ይህም ቤተ መቅደስ እግዚአብሔር ለዳዊትና ለልጁ ለሰሎሞን “ይህ በኢየሩሳሌም የሚገኘው ቤተ መቅደስ ስሜ እንዲጠራበት ከዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች ግዛት ሁሉ የመረጥኩት የተቀደሰ ስፍራ ነው፤


በተጨማሪም የካህናት መሪዎችና ሕዝቡ ጣዖቶችን በማምለክ በዙሪያቸው የሚገኙትን ሕዝቦች መጥፎ ምሳሌነት ተከተሉ፤ እግዚአብሔር ራሱ የቀደሰውን ቤተ መቅደስም አረከሱ፤


ሸሽቶ ለማምለጥ ቢሞክርም ነፋሱ ያለ ርኅራኄ በእርሱ ላይ ያይልበታል፤


በጭቈና፥ በችግርና በሐዘን ተሸንፈው በተዋረዱ ጊዜ ግን፥


ተቈጥቼም ‘ዕረፍት ወደምታገኙባት ምድር ከቶ አትገቡም’ ብዬ ማልኩ።”


እግዚአብሔር ሆይ፥ አንተ ትክክለኛ ፈራጅ እንደ መሆንህ ገሥጸን፤ ነገር ግን ፈጽመን እንዳንጠፋ በምትቈጣበት ጊዜ አይሁን።


እንደ በድን ሕይወት በሌላቸው ጣዖቶች ርስቴን ስላረከሱና በሐሰተኞች አማልክታቸው ስለ ሞሉአት ስለ ኃጢአታቸውና ስለ ክፋታቸው በእጥፍ እቀጣቸዋለሁ።”


ይልቁንም የስሜ መጠሪያ እንዲሆን በተሠራው መቅደሴ አጸያፊ የሆኑ ጣዖቶቻቸውን በማቆም አርክሰውታል።


እኔ የምጠላቸውን እነዚህን አጸያፊ ነገሮች እንዳታደርጉ ያስጠነቅቋችሁ ዘንድ አገልጋዮቼን ነቢያትን ወደ እናንተ ደጋግሜ ልኬ ነበር።


እግዚአብሔር ያሰበውን ፈጸመ፤ ቀድሞ የተናገረውን ቃል ተግባራዊ አደረገ፤ ከረጅም ጊዜ በፊት በወሰነው መሠረት ያለ ርኅራኄ አፈራረሰ፤ ጠላት በእናንተ ላይ ደስ እንዲሰኝ አደረገ፤ የጠላቶቻችሁንም ኀይል አበረታ።


ወጣቶችና ሽማግሌዎች በተመሳሳይ ሁኔታ ሞተው በየመንገዱ ዳር ወደቁ፤ ወጣቶች ወንዶችና ሴቶች በጠላት ሰይፍ ተጨፈጨፉ፤ በቊጣህ ቀን ያለ ምሕረት እንዲታረዱ አደረግህ።


በሚመለሱበት ጊዜ የሚያገኙአቸውን አጸያፊና ርኩስ የሆኑ ጣዖቶችን ወዲያ ያስወግዳሉ።


ልባቸው ርኩስና አጸያፊ የሆኑ ጣዖቶችን የሚከተሉትን ግን እንደ ሥራቸው እከፍላቸዋለሁ፤” ይህን የተናገረ ልዑል እግዚአብሔር ነው።


ልዑል እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፦ “በጥላቻ ለምትጸየፊያቸው ሕዝቦች አሳልፌ እሰጥሻለሁ፤


እነርሱ የፈጸሙት በደል ይህ ብቻ አይደለም፤ ቤተ መቅደሴንም በዚያን ጊዜ አርክሰዋል፤ ሰንበቴንም ሽረዋል።


ለጣዖቶች መሥዋዕት አድርገው ለማቅረብ ልጆቼን በገደሉበት ዕለት ወደ ቤተ መቅደሴ መጥተው አረከሱት፤ እነሆ በቤቴ ያደረጉት ይህ ነው።


እኔ ልዑል እግዚአብሔር ‘አንድ ነገር የማደርግበት ጊዜ ቀርቦአል፤ አልገታም፤ አልምርም፤ ሐሳቤን አለውጥም፤ እንደ አካሄድሽና እንደ ሥራሽ እፈርድብሻለሁ’ ” ብዬ ተናግሬአለሁ።


እንዲያውም ከሁሉ የደከመ መንግሥት ስለሚሆን ዳግመኛ ሌሎች መንግሥታትን የመግዛት ዕድል አይኖረውም፤ ከሁሉ ያነሰ ስለማደርገው ሌላ መንግሥት ማስገበር አይችልም።


እኔ ልዑል እግዚአብሔር ሕያው እንደ መሆኔ ኃጢአተኛ ሰው፥ ኃጢአት መሥራቱን ትቶ በሕይወት እንዲኖር እንጂ በኃጢአቱ እንዲሞት አልፈቅድም፤ ስለዚህ እስራኤል ሆይ! ክፉ ሥራችሁን ተዉ፤ መሞትን ለምን ትፈልጋላችሁ? ብለህ ንገራቸው።


ነገሥታቱ የቤተ መንግሥታቸውን መድረኮችና መቃኖች ወደ ቤተ መቅደሴ መድረኮችና መቃኖች አስጠግተው ስለ ሠሩ፥ የእኔን ቤትና የእነርሱን ቤት የሚለይ አንድ ግንብ ብቻ ሆኖአል፤ በፈጸሙትም አጸያፊ ድርጊት ሁሉ ቅዱስ ስሜን አሰድበዋል፤ ከዚህም የተነሣ በቊጣዬ አጠፋኋቸው።


ስብንና ደምን ለእኔ የምግብ ቊርባን አድርጋችሁ በምታቀርቡበት ጊዜ ሊታዘዙኝ ፈቃደኞች ያልሆኑትን ያልተገረዙ ባዕዳን ወደ ተቀደሰው ስፍራዬ በማስገባት ቤተ መቅደሴን አርክሳችኋል፥ በረከሰውም ተግባራችሁ ሁሉ ቃል ኪዳኔን አፍርሳችኋል።


ስለዚህ ልዑል እግዚአብሔር የሚለው እንዲህ ነው፦ “እናንተ የኢየሩሳሌም ኗሪዎች! በዙሪያችሁ ካሉት ሕዝቦች ይበልጥ ሥርዓተ አልበኞች ሆናችኋል፤ ሕጎቼንና ሥርዓቴን አላከበራችሁም፤ በአካባቢአችሁ ባሉት ሕዝቦች ሥርዓት እንኳ አልተመራችሁም።


መመኪያቸው ከሆኑት ውብ ጌጦቻቸው አስጠሊና አጸያፊ ጣዖቶቻቸውን ሠሩባቸው፤ ስለዚህ እነዚህን ጌጦቻቸውን በእነርሱ ዘንድ አረክሳቸዋለሁ።


ከቶ አልራራላችሁም፤ ምሕረትም አላደርግላችሁም። በርኲሰት ላይ እስካላችሁ ድረስ እንደ አካሄዳችሁ እቀጣችኋለሁ፤ በዚያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ።”


ከቶ አልራራላችሁም፤ ምሕረትም አላደርግላችሁም፤ በርኲሰት ላይ እስካላችሁ ድረስ እንደ አካሄዳችሁ እቀጣችኋለሁ፤ በዚያን ጊዜ የምቀጣችሁ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ።”


እርሱም “የሰው ልጅ ሆይ! ይህን ታያለህን? ገና ከዚህ የባሰ አጸያፊ ነገር ታያለህ” አለኝ።


ስለዚህ በውስጥ በኩል ወዳለው ወደ ቤተ መቅደሱ አደባባይ ወሰደኝ፤ እዚያም ወደ መቅደሱ መግቢያ አጠገብ በመሠዊያውና በመተላለፊያው መካከል ኻያ አምስት ያኽል ሰዎች ነበሩ፤ እነርሱም ጀርባቸውን ወደ መቅደሱ አድርገው የምትወጣዋን ፀሐይ በማምለክ ወደ ምሥራቅ ተንበርክከው ይሰግዱ ነበር።


ስለዚህ ቊጣዬን አወርድባቸዋለሁ፤ ራርቼም አልተዋቸውም፤ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ወደ እኔ ቢጮኹም አላደምጣቸውም።”


ስለዚህ አልራራላቸውም፤ ምሕረትም አላደርግላቸውም፤ እነርሱ በሌሎች ላይ ያደረጉትን ሁሉ በእነርሱ ላይ መልሼ አደርግባቸዋለሁ።”


እንደገናም እግዚአብሔር ሌሎቹን ሰዎች እንዲህ ሲላቸው ሰማሁ፦ “በሉ እናንተም እርሱን ተከትላችሁ በከተማይቱ ውስጥ በመዘዋወር ሁሉን ግደሉ፤ ለማንም በመራራት ምሕረት አታድርጉ።


“በመካከላቸው ያለውን ማደሪያዬን በማርከስ እንዳይሞቱ እስራኤላውያንን ከርኲሰት ጠብቃቸው።”


ለያዕቆብና ለዘሮቹ መመኪያ የሆነው እግዚአብሔር እንዲህ ሲል በራሱ ማለ፦ “እነርሱ የሠሩትን ሥራ ሁሉ አልረሳም።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እኔም ከእንግዲህ ወዲህ በምድር ላይ ለሚኖር ለማንም ሰው ርኅራኄ አላደርግም፤ እኔ ራሴ እያንዳንዱን ሰው ለጐረቤቱና ለንጉሡ አሳልፌ እሰጣለሁ፤ እነርሱ ምድሪቱን ያጠፋሉ፤ እኔም ከእነርሱ እጅ አልታደጋቸውም።”


የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “እነርሱ የእኔ ይሆናሉ፤ እኔ በምሠራበት ቀን እነርሱ የእኔ የግሌ ይሆናሉ፤ ወላጆች ለሚያገለግሉአቸው ልጆች ምሕረት እንደሚያደርጉላቸው እኔም ለእነርሱ ምሕረት አደርግላቸዋለሁ።


የአይሁድ በደል ለዓለም ብዙ በረከት አስገኝቶአል፤ የእነርሱም ውድቀት ለአሕዛብ በረከት ሆኖአል፤ አይሁድ ቢድኑማ ኖሮ በረከቱ ምን ያኽል ብዙ በሆነ ነበር!


እግዚአብሔር በተፈጥሮ ቅርንጫፎች ለሆኑት አይሁድ ካልራራላቸው ለእናንተም አይራራላችሁም።


እግዚአብሔር ለአንድ ልጁ ሳይራራ ስለ እኛ አሳልፎ ከሰጠው እንዴት ከልጁ ጋር ሁሉን ነገር በነጻ አይሰጠንም?


እግዚአብሔር ለእንደዚህ ያለው ሰው ይቅርታ አያደርግም፤ ይልቁንም የእግዚአብሔር ቊጣና ቅናት በእርሱ ላይ እንደ እሳት ይነዳል፤ እግዚአብሔርም እንደዚህ ያለውን ሰው ፈጽሞ እስኪደመስሰው ድረስ በዚህ መጽሐፍ የተጻፉት መቅሠፍቶች ሁሉ ይወርዱበታል።


እግዚአብሔር ለአብርሃም ተስፋ በሰጠው ጊዜ የሚምልበት ከእርሱ የበለጠ ሌላ ማንም ስለሌለ እንዲህ ሲል በራሱ ማለ፤


跟着我们:

广告


广告