Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 5:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ “የሰው ልጅ ሆይ! የተሳለ ሰይፍ ወስደህ ጢምህንና የራስ ጠጒርህን በሙሉ ተላጭ፤ ጠጒርህንም በሚዛን መዝነህ በሦስት ቦታ ክፈለው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 “አንተም፤ የሰው ልጅ ሆይ፤ የተሳለ ሰይፍ ወስደህ እንደ ጢም መላጫ ጠጕርህንና ጢምህን ተላጭበት፤ ጠጕሩንም በሚዛን ከፋፍል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 አንተም፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ የተሳለ ሰይፍ ውሰድ፥ እንደ ጢም መላጫ ለራስህ ትወስደዋለህ፥ በራስህና በጢምህም አሳልፈው፥ ሚዛንንም ውሰድ ጠጉሩንም ትከፋፍለዋለህ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 “አን​ተም የሰው ልጅ ሆይ! ራስን ከሚ​ላጭ ምላጭ ይልቅ የተ​ሳለ ጐራ​ዴን ውሰድ፤ ወስ​ደ​ህም በእ​ር​ስዋ ራስ​ህ​ንና ጢም​ህን ተላጭ፤ ሚዛ​ን​ንም ውሰድ፤ ጠጕ​ሩ​ንም ትከ​ፋ​ፍ​ለ​ዋ​ለህ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 አንተም፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ የተሳለን ጐራዴ ውሰድ፥ እንደ ጢም መላጫ ወደ አንተ ትወስደዋለህ፥ ራስህንና ጢምህንም ትላጭበታለህ፥ ሚዛንንም ውሰድ ጠጕሩንም ትከፋፍላለህ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 5:1
6 交叉引用  

“ያም ዘመን በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከኤፍራጥስ ወንዝ ማዶ በተከራየው ምላጭ በአሦር ንጉሠ ነገሥት የራሳችሁን የጢማችሁንና የሰውነታችሁን ሁሉ ጠጒር ይላጫል።


እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ “ሄደህ ከሸክላ ሠሪው ገንቦ ግዛ፤ ከሕዝቡና ከካህናቱ መካከል ታላላቆቹን መርጠህ ከአንተ ጋር አብረው እንዲሄዱ አድርግ።


እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ “አንተ የሰው ልጅ ሆይ! አንድ ጡብ ወስደህ በፊትህ አኑር፤ በላዩም ላይ የኢየሩሳሌምን ከተማ የሚያመለክት ካርታ ንደፍበት።


“ካህናቱ ራሳቸውን መላጨትም ሆነ ጠጒራቸውን ማሳደግ አይገባቸውም፤ ነገር ግን ፀጒራቸውን በሚገባ ሁኔታ ያስተካክሉ።


ቴቄል ‘በሚዛን ተመዝነህ፥ ቀለህ ተገኘህ’ ማለት ነው፤


“ካህናት፥ ለሙታን በማዘን የራስ ጠጒራቸውን አይላጩ፤ ጢማቸውን አሳጥረው አይቊረጡ፤ ፊታቸውንም አይንጩ።


跟着我们:

广告


广告