Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 48:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 እንደዚሁም የሌዋውያኑና የከተማው ይዞታ በምሥራቅና በምዕራብ የመሪው ይዞታ ከሆኑት ቦታዎች መካከል ናቸው ማለት ነው፤ እንዲሁም በሰሜን ከይሁዳ ዕጣ፥ በደቡብም ከብንያም ዕጣ ጋር ይዋሰናል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ስለዚህ የሌዋውያኑ ይዞታና የከተማዪቱ ይዞታ ለገዢው በተሰጠው ቦታ መካከል ይሆናል፤ የገዢው ቦታም በይሁዳ ድንበርና በብንያም ድንበር መካከል ይሆናል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 የሌዋውያንም ርስት የከተማይቱም ይዞታ ለአለቃው በሆነው መካከል ይሆናል፤ በይሁዳ ድንበርና በብንያም ድንበር መካከል የአለቃ ዕጣ ክፍል ይሆናል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 የሌ​ዋ​ው​ያን ርስት፥ የከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ይዞታ ለአ​ለ​ቃው በሆ​ነው መካ​ከል ይሆ​ናል፤ በይ​ሁዳ ድን​በ​ርና በብ​ን​ያም ድን​በር መካ​ከል የአ​ለ​ቃው ዕጣ ክፍል ይሆ​ናል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 የሌዋውያንም ርስት የከተማይቱም ይዞታ ለአለቃው በሆነው መካከል ይሆናል፥ በይሁዳ ድንበርና በብንያም ድንበር መካከል የአለቃ ዕጣ ክፍል ይሆናል።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 48:22
3 交叉引用  

በተቀደሰው ቦታና በከተማውም ይዞታ በሁለቱም በኩል የተረፈው ክፍል የመስፍኑ ድርሻ ነው። ይኸውም በምሥራቅ በኩል የተቀደሰውን ቦታ ከሚያዋስነው ኻያ አምስት ሺህ ክንድ ተነሥቶ እስከ ምድሪቱ ወሰን ድረስ ነው። በምዕራብም በኩል የተቀደሰውን ቦታ ከሚያዋስነው ከኻያ አምስት ሺህ ክንድ ተነሥቶ እስከ ምድሪቱ ወሰን ድረስ ነው። የመሪውም ድርሻ ርዝመቱ ከሌሎቹ ነገዶች ድርሻ እኩል ነው። በዚህ ዐይነት የተቀደሰው ቦታና ቤተ መቅደሱ በመካከል ይሆናሉ ማለት ነው።


ስለቀሩትም ነገዶች የምድሪቱ አከፋፈል እንደሚከተለው ነው፤ ብንያም ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ የሚደርስ አንድ ድርሻ ይኖረዋል፤


“እስራኤላውያን ድርሻቸው ከሆነ ርስት ለሌዋውያን የሚኖሩባቸውን ከተሞችንና በከተሞቹም ዙሪያ የግጦሽ መሬት እንዲሰጡአቸው ንገር።


跟着我们:

广告


广告