ሕዝቅኤል 48:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም18 ከተቀደሰው ክልል በምሥራቅ ዐሥር ሺህ ክንድ በምዕራብ ዐሥር ሺህ ክንድ ተነሥቶለት ከተማይቱ ከተሠራች በኋላ የሚቀረው ትርፍ ቦታ በከተማይቱ ለሚኖሩት ሕዝብ የእርሻ መሬት ይሆናል። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም18 ከዚህ የሚቀረው፣ የተቀደሰውን ክፍል የሚያዋስነውና በተጓዳኝ ያለው ቦታ በምሥራቅ ዐሥር ሺሕ ክንድ፣ በምዕራብ ዐሥር ሺሕ ክንድ ይሆናል። ምርቱም ለከተማዪቱ ሠራተኞች ምግብ ይሆናል። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)18 በተቀደሰው መባ አጠገብ የተረፈው ርዝመቱ ወደ ምሥራቅ ዐሥር ሺህ ወደ ምዕራብም ዐሥር ሺህ ክንድ ይሆናል። ይህም በተቀደሰው መባ አጠገብ ይሆናል። ምርቷም ከተማይቱን ለሚያገለግሉ ለመብል ይሆናል። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)18 “በተቀደሰው መባ አንጻር የተረፈው ርዝመቱ ወደ ምሥራቅ ዐሥር ሺህ፥ ወደ ምዕራብም ዐሥር ሺህ ክንድ ይሆናል። በተቀደሰው መባ አንጻር ይሆናል። ፍሬውም ከተማዪቱን ለሚያገለግሉ መብል ይሆናል። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)18 በተቀደሰው መባ አንጻር የተረፈው ርዝመቱ ወደ ምሥራቅ አሥር ሺህ ወደ ምዕራብም አሥር ሺህ ክንድ ይሆናል። በተቀደሰው መባ አንጻር ይሆናል። ፍሬውም ከተማይቱን ለሚያገለግሉ ለመብል ይሆናል። 参见章节 |