ሕዝቅኤል 48:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም17 ከተማዋ በአራቱም ማእዘን የመሰማሪያ ቦታ ይኖራታል፤ በየማእዘኑ ያለው የመሰማሪያ ቦታ ስፋት ሁለት መቶ ኀምሳ ክንድ ነው። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም17 የከተማዪቱ ከብት ማሰማሪያ ቦታ፣ በሰሜን ሁለት መቶ ዐምሳ ክንድ፣ በደቡብ ሁለት መቶ ዐምሳ ክንድ፣ በምሥራቅ ሁለት መቶ ዐምሳ ክንድ፣ በምዕራብም ሁለት መቶ ዐምሳ ክንድ ይሆናል። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)17 ከተማይቱ ማሰማርያ ይኖራታል፤ በሰሜን በኩል ሁለት መቶ አምሳ፥ በደቡብ በኩል ሁለት መቶ አምሳ፥ በምሥራቅ በኩል ሁለት መቶ አምሳ፥ በምዕራብም በኩል ሁለት መቶ አምሳ ክንድ ይሆናል። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)17 ለከተማዪቱም ማሰማርያ ይኖራታል፤ በሰሜን በኩል ሁለት መቶ አምሳ፥ በደቡብም በኩል ሁለት መቶ አምሳ፥ በምሥራቅም በኩል ሁለት መቶ አምሳ፥ በምዕራብም በኩል ሁለት መቶ አምሳ ክንድ ይሆናል። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)17 ለከተማይቱም ማሰማርያ ይኖራታል፥ በሰሜን በኩል ሁለት መቶ አምሳ፥ በደቡብም በኩል ሁለት መቶ አምሳ፥ በምሥራቅም በኩል ሁለት መቶ አምሳ፥ በምዕራብም በኩል ሁለት መቶ አምሳ ክንድ ይሆናል። 参见章节 |