Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 48:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ከተቀደሰው ቦታ ይህ የእነርሱ ድርሻ ነው፤ እርሱም በጣም የተቀደሰ ሲሆን ከሌዋውያን ድንበር ጋር የተያያዘ ነው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 የሌዋውያንን ምድር ከሚያዋስነው፣ ከምድሪቱ ቅዱስ ድርሻ እጅግ የተቀደሰው ድርሻ ለእነርሱ ልዩ ስጦታ ይሆናል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ከምድሪቱ መባ የተቀደሰው መባ ለእነርሱ ይሆናል፥ እጅግ የተቀደሰ ይሆናል፤ በሌዋውያን ድንበር አጠገብ ይሆናል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ከም​ድ​ርም መባ የተ​ለየ ሌላ መባ ይሆ​ን​ላ​ቸ​ዋል፤ ከተ​ቀ​ደ​ሱ​ትም ይልቅ የተ​ቀ​ደሰ ይሆ​ናል፤ በሌ​ዋ​ው​ያን ድን​በር አጠ​ገብ ይሆ​ናል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ከምድርም መባ የተለየ መባ ይሆንላቸዋል፥ ከሁሉም ይልቅ የተቀደሰ ይሆናል፥ በሌዋውያን ድንበር አጠገብ ይሆናል።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 48:12
4 交叉引用  

ይህ ከጠቅላላው መሬት የተቀደሰ ክፍል ሆኖ ወደ እግዚአብሔር ቀርበው በቤተ መቅደሱ ውስጥ ለሚያገለግሉት ካህናት የተደለደለ ነው፤ ቦታውም ለካህናቱ መኖሪያና ለቤተ መቅደሱ መሥሪያ ይሆናል።


ይህም ቦታ የሳዶቅ ተወላጆች ለሆኑት የተቀደሱ ካህናት የተለየ ይሆናል። እስራኤላውያን ሁሉና ሌሎቹ ሌዋውያን እኔን ትተው በባዘኑ ጊዜ የሳዶቅ ልጆች ከትእዛዞቼ ፈቀቅ ሳይሉ ጠብቀው የኖሩ ናቸው።


ከካህናቱ ቦታ ጐን ኻያ አምስት ሺህ ክንድ ርዝመትና ዐሥር ሺህ ክንድ ወርድ የሆነ የሌዋውያን ድርሻ አለ፤ ጠቅላላውም ከካህናቱ ድርሻ ጋር ኻያ አምስት ሺህ ክንድ ርዝመትና ኻያ ሺህ ክንድ ወርድ ነው።


ይህ ለቀድሞ ባለቤቱ ለመመለስ የማይችለው መሬትም በተከታዩ በኢዮቤልዩ ዓመት ለእግዚአብሔር የተለየ ቀዋሚ ንብረት እንደ ሆነ ይቀራል፤ እርሱም የካህኑ ድርሻ ይሆናል።


跟着我们:

广告


广告