Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 47:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 እዚያም እንደ ደረስኩ በወንዙ ግራና ቀኝ ስመለከት ብዙ ዛፎችን አየሁ፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 እዚያም በደረስሁ ጊዜ፣ በወንዙ ግራና ቀኝ ብዙ ዛፍ አየሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 በተመለስሁም ጊዜ፥ እነሆ በወንዙ ዳር በዚህና በዚያ እጅግ ብዙ ዛፎች ነበሩ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 በተ​መ​ለ​ስ​ሁም ጊዜ፥ እነሆ በወ​ንዙ ዳር በዚ​ህና በዚያ እጅግ ብዙ ዛፎች ነበሩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 በተመለስሁም ጊዜ፥ እነሆ፥ በወንዙ ዳር በዚህና በዚያ እጅግ ብዙ ዛፎች ነበሩ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 47:7
9 交叉引用  

እንዲሁም ንጉሥ ሰሎሞን በኤዶም ምድር በቀይ ባሕር ዳርቻ በምትገኘው በኤላት አጠገብ ባለችው በዔጽዮንጋብር መርከቦችን ሠራ።


ከኤልያስም የወደቀውን ካባ ከመሬት አነሣ፤ ከዚያም ሄዶ በዮርዳኖስ ወንዝ ዳርቻ ቆመ።


ሙሴም በብርቱ ጩኸት ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤ እግዚአብሔርም አንድ እንጨት አሳየው፤ እርሱንም ወስዶ በውሃው ላይ በጣለው ጊዜ፥ ውሃው ወደጣፋጭነት ተለወጠ። በዚያ ስፍራ እግዚአብሔር የሚተዳደሩበት ደንብና ሥርዓት ሰጣቸው፤ በዚያም ፈተናቸው።


ቤተ መቅደሴ ያረፈበትን ቦታ ለማስዋብ የሊባኖስ ግርማ የሆኑት ዝግባ አስታና ጥድ ወደ አንቺ እንዲመጡ ይደረጋሉ፤ እኔም የእግሬ ማረፊያ የሆነውን አከብረዋለሁ።


ሕዝብሽ ጻድቃን ይሆናሉ፤ ምድሪቱን ለዘለዓለም ይወርሳሉ፤ እኔ እመሰገን ዘንድ እነርሱን የፈጠርኳቸውና የተካኋቸው እኔ ነኝ።


በጽዮን ለሚያለቅሱት ሰዎች በዐመድ ፈንታ የአበባ ጒንጒንን፥ በእንባቸው ምትክ የወይራ ዘይትን በኀዘን ፈንታ የደስታ ዘይትን፥ በዛለ መንፈሳቸው ፈንታ የምስጋና መጐናጸፊያን ለማስገኘት ላከኝ። እነርሱም ክብሩን እንዲገልጡ እግዚአብሔር የተከላቸው “የጽድቅ ዋርካዎች” ተብለው ይጠራሉ።


በፈሳሹ ውሃ ዳርና ዳር ለምግብ የሚሆኑ ተክሎች በየዐይነቱ ይገኛሉ፤ እነርሱም ቅጠሎቻቸው አይደርቁም፤ ፍሬ ማፍራትንም አያቋርጡም፤ ከቤተ መቅደሱ ሥር የሚፈሰውን ወንዝ ውሃ ስለሚያገኙ በየወሩ አዲስ ፍሬ ያፈራሉ፤ ዛፎቹ ፍሬአቸው ለምግብ፥ ቅጠላቸው ለፈውስ የሚጠቅም ነው።”


ይህ ወንዝ በከተማይቱ ዋና መንገድ መካከል ሰንጥቆ ያልፋል፤ በወንዙ ግራና ቀኝ በየወሩ እያፈራ በዓመት ዐሥራ ሁለት ጊዜ ፍሬ የሚሰጥ የሕይወት ዛፍ ነበረ፤ የዛፉም ቅጠሎች ሕዝቦችን ለመፈወስ ያገለግላሉ።


跟着我们:

广告


广告