Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 47:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ሰውየውም “የሰው ልጅ ሆይ! ይህን ሁሉ በጥንቃቄ አስታውስ” አለኝ። ከዚያን በኋላ ያ ሰው ወደ ውሃው ዳርቻ መለሰኝ፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 እርሱም፣ “የሰው ልጅ ሆይ፤ ይህን ታየዋለህን?” ሲል ጠየቀኝ። ከዚያም መልሶ ወደ ወንዙ ዳር መራኝ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 እንዲህም አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ አይተሃልን? መራኝ፥ ወደ ወንዙም ዳር መለሰኝ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 እር​ሱም፥ “የሰው ልጅ ሆይ! አይ​ተ​ሃ​ልን?” አለኝ። አመ​ጣ​ኝም፤ ወደ ወን​ዙም ዳር መለ​ሰኝ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 እርሱም፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ አይተሃልን? አለኝ። አመጣኝም፥ ወደ ወንዙም ዳር መለሰኝ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 47:6
8 交叉引用  

ሰውየውም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ! እዚህ ድረስ እንድትመጣ የተደረገበት ምክንያት እኔ የማሳይህን ሁሉ እንድትረዳ ስለ ሆነ ልብ ብለህ ተመልከት፤ በጥንቃቄም ስማ፤ የምታየውንም ሁሉ ለእስራኤል ሕዝብ ንገራቸው።”


እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ! የምትሰማውንና የምታየውን ነገር ሁሉ ልብ ብለህ አስተውለው፤ እነሆ እኔ ስለ ቤተ መቅደሱ ሕግና ሥርዓት ሁሉ እነግርሃለሁ፤ በቤተ መቅደሱ ውስጥ መግባትና መውጣት የሚፈቀድላቸው ምን ዐይነት ሰዎች እንደ ሆኑ አስተውል።


ቀጥሎም እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ! ይህን ታያለህን? እነዚህ የይሁዳ ሕዝቦች በዚህ ስፍራ ያየኸውን አጸያፊ ነገር ሁሉ በመሥራትና በአገሪቱም ላይ ዐመፅ ማስፋፋቱ አልበቃ ብሎአቸው ወደዚህ ወደ ቤተ መቅደስ እንኳ ሳይቀር በቀጥታ መጥተው ይህን ሁሉ በማድረግ እኔን እንደገና ማስቈጣት ይፈልጋሉ፤ እንዴት እንደሚሰድቡኝና እኔን ለማስቈጣት የተቻላቸውን ሁሉ እንደሚያደርጉ ተመልከት!


እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ! የሆነውን ነገር ሁሉ ታያለህን? የእስራኤል ሕዝብ በዚህ ስፍራ የሚፈጽሙትን አጸያፊ ነገር ተመልከት፤ በዚህ አድራጎታቸው ከተቀደሰው ስፍራዬ እንድርቅ አድርገውኛል፤ ከዚህም የበለጠ እጅግ አስነዋሪ የሆነ ነገር ገና ታያለህ።”


“ይህ የምታየው ምንድን ነው?” ብሎም ጠየቀኝ። እኔም እንዲህ ብዬ መለስኩለት፦ “ሰባት መብራቶች ያሉበት አንድ የወርቅ መቅረዝ አያለሁ፤ በአናቱም ላይ የዘይት ማሰሮ አለ፤ ሰባቱም መብራቶች የክር ማስተላለፊያ ቧንቧ አላቸው።


መልአኩም “ምን ታያለህ?” ብሎ ጠየቀኝ፤ እኔም “ርዝመቱ ዐሥር ሜትር፤ ስፋቱም አምስት ሜትር የሆነ፥ አንድ የተጠቀለለ የብራና መጽሐፍ በአየር ላይ ሲበር አያለሁ” አልኩት።


ደግሞም ኢየሱስ፦ “ይህን ሁሉ አስተዋላችሁን?” አላቸው። እነርሱም “አዎን ጌታ ሆይ!” አሉ።


跟着我们:

广告


广告