Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 47:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ያም ሰው በሰሜኑ ቅጽር በር በኩል ከቤተ መቅደሱ አውጥቶ ወሰደኝ፤ ወደ ምሥራቅ አቅጣጫ በሚመለከተውም ቅጽር በር አዞረኝ፤ ከቅጽር በሩም በስተ ደቡብ ውሃው ወደ ምሥራቅ ይፈስ ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ከዚያም በሰሜኑ በር በማውጣት በውጭ አዙሮ በምሥራቅ አቅጣጫ ወዳለው የውጭ በር መራኝ፤ ውሃውም በደቡብ በኩል ይፈስስ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 በሰሜኑ በር በኩል አወጣኝ፤ በውጭ ባለው መንገድ፥ ወደ ምሥራቅ ወደሚመለከት በውጭ ወዳለው በር አመጣኝ፤ እነሆ ውኃው በደቡብ በኩል ይፈስስ ነበር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 በሰ​ሜ​ኑም በር በኩል አወ​ጣኝ፤ በስተ ውጭ በአ​ለው መን​ገድ፥ ወደ ምሥ​ራቅ ወደ​ሚ​መ​ለ​ከት በስተ ውጭ ወዳ​ለው በር አዞ​ረኝ፤ እነ​ሆም ውኃው በቀኝ በኩል ይፈ​ስስ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 በሰሜኑም በር በኩል አወጣኝ፥ በስተ ውጭ ባለው መንገድ፥ ወደ ምሥራቅ ወደሚመለከት በስተ ውጭ ወዳለው በር አዞረኝ፥ እነሆም፥ ውኃው በቀኙ ወገን ይፈስስ ነበር።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 47:2
5 交叉引用  

ያ ሰው ወደ ሰሜኑ ቅጽር በር ወሰደኝ፤ በለካውም ጊዜ ስፋቱ በሌሎቹ ልክ ሆኖ ተገኘ።


እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፦ “ይህ በር እንደ ተዘጋ ይኖራል እንጂ ከቶ አይከፈትም፤ የእስራኤል አምላክ እኔ እግዚአብሔር የገባሁበት ስለ ሆነ፥ ማንም በዚህ በር መጠቀም አይችልም፤ ስለዚህም እንደ ተዘጋ ይኖራል።


ከዚያም በኋላ ያ ሰው በሰሜኑ ቅጽር በር በኩል አድርጎ ወደ ቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት ወሰደኝ፤ በዚያም ሆኜ ስመለከት የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ በክብሩ ተሞልቶ አየሁ፤ እኔም በግንባሬ ተደፋሁ፤


ከዚያም በኋላ ወደ ቤተ መቅደሱ መግቢያ መለሰኝ፤ እዚያም ከቤተ መቅደሱ መድረክ ሥር ውሃ ወደ ምሥራቅ ይፈስ ነበር፤ (ይህም የቤተ መቅደሱ በር ወደ ምሥራቅ ዞሮ ስለ ነበረ ነው) ውሃውም የሚፈሰው ከቤተ መቅደሱ በስተደቡብ በኩል ባለው መድረክ ሥር ከመሠዊያው በስተደቡብ ነበር።


ያም ሰው በያዘው የመለኪያ ገመድ ወደ ምሥራቅ የሚፈሰውን ውሃ በመከተል አንድ ሺህ ክንድ ለካ፤ በዚያም ውሃ እየተራመድኩ እንድሻገር አደረገኝ፤ ውሃውም እስከ ቊርጭምጭሚቴ ደረሰ።


跟着我们:

广告


广告