Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 47:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ከዔንገዲ ጀምሮ እስከ ዔንዔግላይም ድረስ ዓሣ አጥማጆች ይቆማሉ፤ ያም ቦታ መረቦች የሚዘረጉበት ቦታ ይሆናል፤ በሜዲትራኒያን ባሕር እንደሚገኘው ዐይነት በዚህም ልዩ ልዩ ዓሣ ይገኛል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ዓሣ አጥማጆች በወንዙ ዳር ይቆማሉ፤ ከዓይንጋዲ እስከ ዓይንኤግላይም ድረስ ያለው ቦታ መረብ መዘርጊያ ይሆናል፤ ዓሣውም እንደ ታላቁ ባሕር ዓሣ፣ የተለያየ ዐይነት ይሆናል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ከዔንጌዲ ጀምሮ እስከ ዔንዔግላይም ድረስ አጥማጆች በዚያ ይቆማሉ፤ የመረቦች መዘርጊያ ይሆናል፤ ዓሣዎችም እንደ ታላቁ ባሕር ዓሣ በየወገናቸው እጅግ ይበዛሉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ዓሣ አጥ​ማ​ጆ​ችም ከዓ​ይ​ን​ጋዲ ጀምሮ እስከ ዓይ​ን​ኤ​ግ​ላ​ይም ድረስ በዚያ ይቆ​ማሉ። ያም መረብ መዘ​ር​ጊያ ይሆ​ናል፤ ዓሣ​ዎ​ችም እንደ ታላቁ ባሕር ዓሣ​ዎች በየ​ወ​ገ​ና​ቸው እጅግ ይበ​ዛሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 አጥማጆችም በዚያ ይቆማሉ፥ ከዓይንጋዲ ጀምሮ እስከ ዓይንኤግላይም ድረስ መረብ መዘርጊያ ይሆናል፥ ዓሣዎችም እንደ ታላቁ ባሕር ዓሣዎች በየወገናቸው እጅግ ይበዛሉ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 47:10
21 交叉引用  

ከዚያም ተመልሰው ወደ ቃዴስ መጡ፤ በዚያን ጊዜ የዚህ ቦታ ስም ዔይንሚሽፖጥ ይባል ነበር። የዐማሌቃውያንንም ምድር ሁሉ ያዙ፤ በሐጸጾን ታማር ይኖሩ የነበሩትን አሞራውያንንም አሸነፉ።


ሰዎች መጥተው ለንጉሥ ኢዮሣፍጥ “በአንተ ላይ አደጋ ለመጣል እጅግ ብዙ የሆነ ሠራዊት ከሙት ባሕር ባሻገር ካለው ከኤዶም ምድር መጥቶብሃል፤ እነሆ ሐጸጾንታማርን ቀደም ሲል በድል አድራጊነት ይዘዋል” ሲሉ ነገሩት፤ (ሐጸጾንታማር የዔንገዲ ሌላ መጠሪያ ስሙ ነው፤)


ከቊጥር በላይ በሆኑ ታላላቅና ታናናሽ ሕያዋን ፍጥረቶች የተሞላው ትልቁና ሰፊው ባሕር እነሆ፥


መንጠቆአቸውን ወደ አባይ ወንዝ የሚጥሉ ዓሣ አጥማጆች ያዝናሉ፤ ያለቅሳሉም፤ መረቦቻቸውንም በውሃ ላይ የሚዘረጉ ተስፋ ይቈርጣሉ፤


ሕዝቦቼ ከሩቅ አገሮች ይመጣሉ፤ ከሰሜንና ከምዕራብ እንዲሁም ከሲኒም።”


በስደት የተወለዱ ልጆችሽ ‘ይህ ቦታ ለእኛ በጣም ጠባብ ስለ ሆነ የምንኖርበት ሰፊ ቦታ ስጪን’ ይሉሻል።


ዓሣ አጥማጆች መረባቸውን የሚያሰጡበት አለት ብቻ አግጥጦ ይቀራል፤ ከተማይቱ ዳግመኛ አትታደስም፤ ይህም የሚሆነው እኔ ልዑል እግዚአብሔር ስለ ተናገርኩ ነው።”


እዚያው በባሕር መካከል አጥማጆች መረባቸውን ለማድረቅ የሚያሰጡበት ስፍራ አደርጋታለሁ፤ እኔ ልዑል እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ፤ ሕዝቦች ጢሮስን ይመዘብራሉ።


“የመሬቱ ድንበር እንደሚከተለው ነው፦ የሰሜኑ ድንበር ከሜዲቴራኒያን ባሕር ተነሥቶ ወደ በሔትሎን በኩል ወደ ሐማት መተላለፊያ፥ ወደ ጼዳድም፥


“የደቡቡም ድንበር ከታማር ተነሥቶ እስከ መሪባ ቃዴስ ድረስ፥ ከዚያም ከግብጽ ሸለቆ እስከ ሜዲቴራኒያን ባሕር ይደርሳል፤ ይህም የደቡብ ድንበር ነው።


የጋድ ደቡባዊ ድንበር ከታማር ከተማ ደቡብ ተነሥቶ በመሪባ ቃዴስ እስከምትገኘው የውሃ ምንጭ ይዘልቃል፤ ከዚያም የግብጽ ወሰን የሆነውን ወንዝ ተከትሎ እስከ ሜዲቴራኒያን ባሕር ይደርሳል።


“የምዕራቡ ወሰን የሜድትራኒያን ባሕር ጠረፍ ይሆናል።


ኢየሱስም “ኑ ተከተሉኝ፤ ዓሣን እንደምታጠምዱ ሁሉ ሰዎችን እንድትሰበስቡልኝ አደርጋችኋለሁ” አላቸው።


ኢየሱስም፦ “ኑ ተከተሉኝ፤ ዓሣን እንደምታጠምዱ ሁሉ ሰዎችንም እንድትሰበስቡልኝ አደርጋችኋለሁ፤” አላቸው።


ኒብሻን፥ የጨው ከተማና ዔንገዲ ተብለው የሚጠሩ በድምሩ ስድስት ከተሞች ሲሆኑ በዙሪያቸው የሚገኙትን መንደሮች ያጠቃልላሉ።


እኔም ገና ድል ያልተመቱትና ድል የመታኋቸው ሕዝቦች ይዞታ የነበረውና በምሥራቅ በኩል ከዮርዳኖስ ወንዝ በመዋሰን በስተምዕራብ እስከ ሜዲቴራኒያን ባሕር የሚደርሰውን ሁሉ ለነገዶቻችሁ ርስት አድርጌ ሰጥቼአለሁ፤


ዳዊትም ከዚያ በመነሣት ተሸሽጎ ወደቈየበት ዔንገዲ ተብሎ ወደሚጠራው ስፍራ ሄደ።


ሳኦል ፍልስጥኤማውያንን ወግቶ ከተመለሰ በኋላ ዳዊት በዔንገዲ አጠገብ በሚገኘው ምድረ በዳ የሚገኝ መሆኑን ሰማ፤


跟着我们:

广告


广告