Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 46:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 “በማናቸውም የበዓል ቀን ሕዝቡ ለእግዚአብሔር ለመስገድ በሚመጡበት ጊዜ በሰሜን ቅጽር በር የገቡት በደቡብ ቅጽር በር ይውጡ፤ በደቡብ ቅጽር በር የገቡትም በሰሜን ቅጽር በር ይውጡ፤ ማንም ሰው በገባበት በር አይውጣ፤ ነገር ግን በአንጻሩ ባለው በሌላ በር መውጣት አለበት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 “ ‘በተወሰኑት በዓላት የምድሪቱ ሕዝብ በእግዚአብሔር ፊት በሚቀርብበት ጊዜ፣ ይሰግድ ዘንድ በሰሜን በር የገባ ሁሉ በደቡብ በር ይውጣ፤ በደቡብ በር የገባም በሰሜኑ በር ይውጣ፤ በፊት ለፊቱ ባለው በር ይመለስ እንጂ ማንም በገባበት በር አይውጣ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 የምድሪቱ ሕዝብ ግን በየክብረ በዓሉ ቀን ወደ ጌታ ፊት በመጡ ጊዜ በሰሜን በር በኩል ሊሰግድ የገባው በደቡብ በር በኩል ይውጣ፥ በደቡብ በር የገባው በሰሜን በር በኩል ይውጣ፤ በፊት ለፊት ባለው ይውጣ እንጂ በገባበት በር አይመለስ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 “የሀ​ገሩ ሕዝብ ግን በየ​ክ​ብረ በዓሉ ቀን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በመጡ ጊዜ በሰ​ሜን በር በኩል ሊሰ​ግድ የሚ​ገ​ባው በደ​ቡብ በር በኩል ይውጣ፤ በደ​ቡ​ብም በር የሚ​ገ​ባው በሰ​ሜን በር በኩል ይውጣ፤ በፊት ለፊት ይውጣ እንጂ በገ​ባ​በት በር አይ​መ​ለስ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 የአገሩ ሕዝብ ግን በየክብረ በዓሉ ቀን ወደ እግዚአብሔር ፊት በመጡ ጊዜ በሰሜን በር በኩል ሊሰግድ የሚገባው በደቡብ በር በኩል ይውጣ፥ በደቡብም በር የሚገባው በሰሜን በር በኩል ይውጣ፥ በፊት ለፊት ይውጣ እንጂ በገባበቱ በር አይመለስ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 46:9
15 交叉引用  

በመጓዝ ላይ ሳሉ ብዙ ብርታትን ያገኛሉ፤ የአማልክትንም አምላክ በጽዮን ያዩታል።


“በዓመት ሦስት ጊዜ ወንዶች ሁሉ ለእኔ ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ይሰግዱ ዘንድ ይምጡ።


እያንዳንዱ ፍጥረት በአራት አቅጣጫ ለመመልከት ይችል ስለ ነበር ሁሉም በአንድነት ወዲያና ወዲህ ሳይሉ መንፈስ ወደሚሄድበት አቅጣጫ ሁሉ ይበሩ ነበር።


እነርሱም ከአራቱ አቅጣጫዎች ወደፈለጉት አቅጣጫ ወደ ሌላ ሳይዞሩ ቀጥ ብለው ይሄዳሉ።


ቀድሞ ኢየሩሳሌም በበዓል ቀን ለመሥዋዕት በሚቀርቡ በጎች ትሞላ እንደ ነበረች የፈራረሱት ከተሞች በሕዝብ የተሞሉ ይሆናሉ፤ በዚያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንኩ ያውቃሉ።”


ከዚያም በኋላ ወደ ደቡብ ወሰደኝ፤ እዚያም በደቡብ በኩል የሚያስወጣ አንድ በር ነበር፤ ሰውየውም የበሩን የግድግዳ ዐምዶችና በስተመጨረሻ ያለውን ክፍል ለካ፤ ስፋታቸውም ከሌሎቹ ጋር እኩል ነበር።


ሕግን በሚመለከት አከራካሪ ነገር በሚነሣበት ጊዜ፥ ደንቡ በሚያዝዘው መሠረት ካህናቱ ይወስኑላቸው፤ በሕጌና ሥርዓቴ መሠረት በዓሎቼን፥ እንዲሁም ዕለተ ሰንበትን በመቀደስ ይጠብቁ።


ስለዚህ በስተሰሜን በኩል ወዳለው ወደ ቤተ መቅደሱ ቅጽር በር ወሰደኝ፤ ተሙዝ ለተባለው ጣዖታቸው ሴቶች ሲያለቅሱለት አሳየኝ።


ለኀያሉ አምላክ ለእግዚአብሔር ለመስገድ በምመጣበት ጊዜ ምን ይዤ ልቅረብ? ለእርሱ የሚቃጠል መሥዋዕት ይሆኑ ዘንድ የአንድ ዓመት ጥጆችን ይዤ ልምጣን?


“የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ይመሩበት ዘንድ በሲና ተራራ ላይ ለአገልጋዬ ለሙሴ የሰጠሁትን ሕግና ትእዛዝ አስታውሱ።


“በዓመት ሦስት ጊዜ ወንዶች ሁሉ የፋሲካን፥ የመከርንና የዳስ በዓልን ለማክበር እግዚአብሔር አምላክህ በሚመርጠው ቦታ ይሰብሰቡ፤ በዓሉን ለማክበር በሚወጡበት ጊዜ ባዶ እጃቸውን አይምጡ፤


የእኔ የሆነ ጻድቁ ሰው ግን በእምነት ሕይወትን ያገኛል፤ ወደ ኋላው ቢያፈገፍግ ግን እኔ በእርሱ አልደሰትም።”


跟着我们:

广告


广告