Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 46:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ከእያንዳንዱም የበግ አውራ ጋር አንድ የኢፍ መስፈሪያ እህል ያምጣ፤ እንዲሁም ከእያንዳንዱ ጠቦት ጋር ለማቅረብ የፈለገውን ያኽል ያቅርብ፤ ከእያንዳንዱም ኢፍ መሥዋዕት ጋር አብሮ የሚቀርብ ሦስት ሊትር ዘይት ያምጣ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ከአውራ በጉ ጋራ የሚቀርበው የእህል ቍርባን አንድ የኢፍ መስፈሪያ ይሁን፤ ከበግ ጠቦቶቹ ጋራ የሚቀርበውም የእህል ቍርባን ሰውየው የወደደውን ያህል ይሁን፤ እያንዳንዱም የኢፍ መስፈሪያ አንድ የሂን መስፈሪያ ዘይት ይኑረው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ለአውራ በጉ አንድ የኢፍ መስፈሪያ የእህል ቁርባን ይሁን፥ ለእያንዳንዱም ጠቦት እጁ የሰጠችውን ያህል የእህል ቁርባን ይሁን፥ ለአንዱም የኢፍ መስፈሪያ አንድ የኢን መስፈሪያ ዘይት ያቅርብ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 የእ​ህ​ሉም ቍር​ባን ለአ​ውራ በጉ አንድ የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ ይሁን፤ ለጠ​ቦ​ቶ​ቹም የእ​ህል ቍር​ባን እጁ እንደ ቻለ ያህል ይሁን፥ ለአ​ን​ዱም የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ አንድ የኢን መስ​ፈ​ሪያ ዘይት ያቅ​ርብ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 የእህሉም ቍርባን ለአውራ በጉ አንድ የኢፍ መስፈሪያ ይሁን፥ ለጠቦቶቹም የእህል ቍርባን እንደሚቻል ያህል ይሁን፥ ለአንዱም የኢፍ መስፈሪያ አንድ የኢን መስፈሪያ ዘይት ያቅርብ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 46:5
7 交叉引用  

እያንዳንዱ ኰርማና እያንዳንዱ የበግ አውራ በሚሠዋበት ጊዜ አንድ አንድ የኤፋ መስፈሪያ እህልና ሦስት ሦስት ሊትር የወይራ ዘይት አብሮ ይቀርባል።


ከእያንዳንዱ ኰርማና ከእያንዳንዱ የበግ አውራ ጋር አንድ አንድ ኢፍ የእህል መባ ይሁን፤ እንዲሁም ከእያንዳንዱ የበግ ጠቦት ጋር የሚቀርበው መባ መስፍኑ ለመስጠት የፈቀደውን ያኽል ይሁን፤ ከእያንዳንዱም ኢፍ ጋር ሦስት ሊትር የወይራ ዘይት አብሮ ይቅረብ።


“ሰውየው ይህን ሁሉ ለማምጣት የማይችል ድኻ ከሆነ፥ በመወዝወዝ ለኃጢአት ማስተስረያ ይሆንለት ዘንድ ለበደል መሥዋዕት የሚሆን አንድ ጠቦት ያምጣ፤ ከዚሁም ጋር በወይራ ዘይት የተለወሰ አንድ ኪሎ የላመ ዱቄት ለእህል መባ ያምጣ፤ እንዲሁም የሊትር ሲሶ የሆነ የወይራ ዘይት ያቅርብ፤


ለእህልም ቊርባን በወይራ ዘይት የተለወሰ ምርጥ ዱቄት አቅርቡ፤ ይኸውም ከእያንዳንዱ ኰርማ ጋር ሦስት ኪሎ ዱቄት፥ ከአውራው በግ ጋር ሁለት ኪሎ ዱቄት፥


“እንግዲህ እነዚህ ስለ ናዝራውያን የተሰጡ የሕግ መመሪያዎች ናቸው፤ ነገር ግን አንድ ናዝራዊ በስእለቱ መሠረት ሊያቀርብ ከሚገባው በላይ ለመስጠት ቃል ቢገባ በገባው ቃል መሠረት ስእለቱን መፈጸም አለበት።”


እያንዳንዱም የሚያመጣው ስጦታ እግዚአብሔር በሰጠው በረከት መጠን ይሁን።


跟着我们:

广告


广告