Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 46:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 መስፍኑ በመግቢያው ክፍል በኩል ከውጪ አደባባይ ወደ ውስጥ ገብቶ በቅጽሩ በር መቃን አጠገብ ይቆማል፤ ካህናቱ ደግሞ እርሱ ያዘጋጀውን የሚቃጠልና የደኅንነት መሥዋዕት ያቀርባሉ፤ መስፍኑም በመድረኩ ላይ እንዳለ ይሰግዳል፤ ከዚያ በኋላ እርሱ ይወጣል፤ የቅጽሩ በር ግን እስከ ምሽት ድረስ አይዘጋም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ገዥው ከውጭ በኩል በመግቢያው መተላለፊያ በረንዳ በመግባት በበሩ መቃን አጠገብ ይቁም፤ ካህናቱም የርሱን የሚቃጠል መሥዋዕትና የኅብረት መሥዋዕት ያቅርቡለት፤ በበሩ መግቢያ ደፍ ላይ ሆኖ ይስገድ፤ ከዚያም ይውጣ፤ በሩ ግን እስከ ምሽት ድረስ አይዘጋ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 መስፍኑ ከውጭ በኩል ባለው በር በመተላለፊያ መንገድ ገብቶ በበሩ መቃን አጠገብ ይቁም፥ ካህናቱም የእርሱን የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የሰላሙን መሥዋዕት ያቅርቡ፥ እርሱም በበሩ መድረክ ላይ ይስገድ፤ ከዚያም በኋላ ይውጣ፥ በሩ ግን እስከ ማታ ድረስ አይዘጋ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 አለ​ቃው በስተ ውጭ ባለው በር በደጀ ሰላሙ መን​ገድ ገብቶ በበሩ መቃን አጠ​ገብ ይቁም፤ ካህ​ና​ቱም የእ​ር​ሱን የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የደ​ኅ​ን​ነ​ቱን መሥ​ዋ​ዕት ያቅ​ርቡ፥ እር​ሱም በበሩ መድ​ረክ ላይ ይስ​ገድ፤ ከዚ​ያም በኋላ ይውጣ፤ በሩ ግን እስከ ማታ ድረስ አይ​ዘጋ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 አለቃውም በስተ ውጭ ባለው በር በደጀ ሰላሙ መንገድ ገብቶ በበሩ መቃን አጠገብ ይቁም፥ ካህናቱም የእርሱን የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የደኅንነቱን መሥዋዕት ያቅርቡ፥ እርሱም በበሩ መድረክ ላይ ይስገድ፥ ከዚያም በኋላ ይውጣ፥ በሩ ግን እስከ ማታ ድረስ አይዘጋ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 46:2
18 交叉引用  

ከዚህ በኋላ ንጉሥ ዳዊት እግዚአብሔር ወደሚመለክበት ድንኳን ሄደ፤ ተቀምጦም እንዲህ ሲል ጸለየ፤ “እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፥ እኔ ይህን ሁሉ ነገር ታደርግልኝ ዘንድ እኔ ማነኝ? ቤተሰቤስ ምንድን ነው?


እስከዚያን ጊዜ ድረስ በምሥራቅ በኩል በንጉሥ ቅጽር በር መግቢያ ተመድበው ነበር፤ እነርሱም ቀደም ሲል ወደ ሌዋውያን ሰፈር በሚያስገቡት ቅጽር በሮች ዘብ ይጠብቁ ነበር።


እዚያም እንደ ደረሰች አዲሱ ንጉሥ በተለመደው ባህል መሠረት ለነገሥታት በተመደበው በቤተ መቅደሱ መግቢያ በሚገኘው ዐምድ አጠገብ በጦር መኰንኖችና በእምቢልታ ነፊዎች ተከቦ ታጅቦ እንደ ቆመ አየች፤ ሕዝቡም ሁሉ በደስታ ተሞልተው እልል ይሉ ነበር፤ እምቢልታ ነፊዎችም መለከት ይነፉ ነበር፤ የቤተ መቅደስ መዘምራንም በሙዚቃ መሣሪያዎች ታጅበው የበዓሉን ሥነ ሥርዓት ይመሩ ነበር፤ ዐታልያም በድንጋጤ ልብስዋን በመቅደድ “ይህ ሤራ ነው! ይህ ሤራ ነው!” ስትል ጮኸች።


መሥዋዕቱን የማቅረብ ሥራ በተፈጸመ ጊዜ ንጉሥ ሕዝቅያስና በዚያ የነበሩ ሰዎች ሁሉ ተንበርክከው ለእግዚአብሔር ሰገዱ።


ንጉሡ በዐምዱ አጠገብ ቆሞ በሙሉ ልቡና ሐሳቡ እግዚአብሔርን ለመከተልና ትእዛዞቹን፥ ደንቦቹንና ድንጋጌዎቹን ለመጠበቅ በእርሱ ፊት ቃል ኪዳኑን አደሰ፤ ስለዚህም በዚህ መጽሐፍ የተጻፈውን ቃል ኪዳን አረጋገጠ።


ወደ ውስጠኛው አደባባይ የሚያደርስ ከፍ ብሎ የተሠራ የቅጽር በር ነበር፤ ያም ሰው በሁለቱ የቅጽር በሮች ከመካከል ያለውን ርቀት ለካ፤ እርሱም መቶ ክንድ ሆነ።


በመግቢያው ክፍል በኩል በግራና በቀኝ ትይዩ ሁለት ሁለት ጠረጴዛዎች ነበሩ፤ በእነዚያም ጠረጴዛዎች ላይ ለሚቃጠል መሥዋዕት፥ ለኃጢአት መሥዋዕትና ለበደል መሥዋዕት የሚቀርቡ እንስሶች ይታረድባቸው ነበር።


የሆነ ሆኖ የሕዝቡ መሪ የተቀደሰውን የመሥዋዕት ኅብስት ለመብላት በዚያ መቀመጥ ይችላል፤ በመግቢያውም ክፍል ውስጠኛ ጫፍ በሚገኘው መተላለፊያ በኩል መግባትና መውጣት ይፈቀድለታል።”


ካህኑ ከዚህ የኃጢአት ስርየት መሥዋዕት ጥቂት ደም ወስዶ የቤተ መቅደሱን መቃኖች፥ የመሠዊያውን እርከን አራት ማእዘኖችና ወደ ውስጠኛው አደባባይ የሚያስገቡትን የቅጽር በሮች መቃኖች ይቀባል፤


“በሥልጣን ላይ ያለው መስፍን በሙሉ የሚቃጠልም ሆነ ወይም የደኅንነት መሥዋዕት በበጎ ፈቃደኛነት በግሉ ለእግዚአብሔር ማቅረብ ቢፈልግ ወደ ውስጠኛው አደባባይ የሚያስገባው የምሥራቁ በር ይከፈትለት፤ የመባውንም አቀራረብ በሰንበት ቀን በሚያደርገው ዐይነት ይፈጽም፤ እርሱም ወጥቶ ከሄደ በኋላ በሩ ይዘጋ።”


መስፍኑም ሲገባ በበሩ መተላለፊያ በኩል ገብቶ ሲወጣም በዚያው በኩል ይውጣ።


ከእነርሱ ጥቂት ራቅ ብሎ ሄደና፥ በመሬት ላይ በግንባሩ ተደፍቶ፥ እንዲህ ሲል ጸለየ፤ “አባት ሆይ! የሚቻል ከሆነ ይህ የመከራ ጽዋ ከእኔ ወዲያ ይለፍ! ነገር ግን የአንተ ፈቃድ ይሁን እንጂ የእኔ ፈቃድ አይሁን።”


እያንዳንዱ ሰው በክርስቶስ ብቁ ሰው እንዲሆን አድርገን ለማቅረብ ለሰው ሁሉ ጥበብን ሁሉ በማስተማርና በመምከር ስለ ክርስቶስ እንሰብካለን።


跟着我们:

广告


广告