Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 46:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “በሥልጣን ላይ ያለው መስፍን ከርስቱ ላይ ቀንሶ ከልጆቹ ለአንዱ ቢሰጥ ያ ርስት ለርሱና ለራሱ ቤተሰብ ጸንቶ ይቈያል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 “ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ገዥው ከርስቱ ላይ ከወንድ ልጆቹ ለአንዱ ስጦታ ቢያደርግ፣ ያ ስጦታ ለዘሩ የሚተላለፍ ነው፤ በውርስም ንብረታቸው ይሆናል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ መስፍኑ ከልጆቹ ለአንዱ ከርስቱ ስጦታ ቢሰጥ ለልጆቹ ይሁን፤ በውርስም ይዞታቸው ይሆናል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “አለ​ቃው ከል​ጆቹ ለአ​ንዱ ከር​ስቱ ስጦታ ቢሰጥ ለል​ጆቹ ይሁን፤ የር​ስት ይዞታ ይሆ​ን​ላ​ቸ​ዋል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ አለቃው ከልጆቹ ለአንዱ ከርስቱ ስጦታ ቢሰጥ ለልጆቹ ይሁን፥ የርስት ይዞታ ይሆንላቸዋል።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 46:16
10 交叉引用  

አባታቸው ብዙ ወርቅና ብር እንዲሁም ከፍ ያለ ዋጋ ያለው ሌላም ልዩ ልዩ ንብረት ሰጣቸው፤ በተመሸጉት የይሁዳ ከተሞች እያንዳንዱን በአንዳንድ ከተማ ላይ ሾመ፤ ኢዮራም የበኲር ልጁ ስለ ሆነ አባቱ ኢዮሣፍጥ በእርሱ እግር ተተክቶ እንዲነግሥ አደረገ፤


እግዚአብሔር ታዛዦቹን በየቀኑ ይጠብቃቸዋል፤ የሰጣቸውም ስጦታ ለዘለዓለም ከእነርሱ ጋር ይኖራል።


የሀገሪቱም መሪ ድርሻ ከተቀደሰው ቦታና ከከተማው ክልል ቀጥሎ በሁለቱም በኩል ማለትም በስተምዕራብ እስከ ሀገሪቱ ድንበር ሲደርስ በስተ ምሥራቅም እስከ ሀገሪቱ ድንበር የሚደርስ ይከለላል፤ ርዝመቱም ለአንድ ነገድ የሚደርሰውን ድርሻ ያኽላል።


በዚያን ጊዜ ንጉሡ በቀኙ በኩል ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል፦ ‘እናንተ አባቴ የባረካችሁ! ኑ! ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ!


ነገር ግን ተፈላጊው አንድ ነገር ብቻ ነው፤ ማርያም የሚሻለውን ነገር መርጣለች፤ እርሱንም ከእርስዋ የሚወስድባት ማንም የለም።”


ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲህ ልጅ ነህ እንጂ ባሪያ አይደለህም፤ ልጅ ከሆንክም የእግዚአብሔር ወራሽ ነህ።


跟着我们:

广告


广告