Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 46:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 “በሥልጣን ላይ ያለው መስፍን በሙሉ የሚቃጠልም ሆነ ወይም የደኅንነት መሥዋዕት በበጎ ፈቃደኛነት በግሉ ለእግዚአብሔር ማቅረብ ቢፈልግ ወደ ውስጠኛው አደባባይ የሚያስገባው የምሥራቁ በር ይከፈትለት፤ የመባውንም አቀራረብ በሰንበት ቀን በሚያደርገው ዐይነት ይፈጽም፤ እርሱም ወጥቶ ከሄደ በኋላ በሩ ይዘጋ።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 “ ‘ገዥው የበጎ ፈቃድ ስጦታ፣ የሚቃጠል መሥዋዕትም ሆነ የኅብረት መሥዋዕት ለእግዚአብሔር በሚያቀርብበት ጊዜ፣ በምሥራቅ ትይዩ የሆነው በር ይከፈትለት፤ በሰንበት ቀን እንደሚያደርገው ሁሉ የሚቃጠል መሥዋዕቱንም ሆነ የኅብረት መሥዋዕቱን ያቅርብ፤ ከዚያ በኋላ ይወጣል፤ በሩም ይዘጋል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 መስፍኑ በፈቃዱ የሚያቀርበውን መሥዋዕት፥ የሚቃጠለውን መሥዋዕት፥ ወይም የሰላሙን መሥዋዕት፥ በፈቃዱ ለጌታ የሚያቀርበውን መሥዋዕት ባቀረበ ጊዜ፥ ወደ ምሥራቅ የሚመለከተው በር ይከፈትለት፥ በሰንበትም ቀን እንደሚያደርግ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የሰላሙን መሥዋዕት ያቅርብ፤ ከዚያ በኋላ ይውጣ፥ ከወጣም በኋላ በሩ ይዘጋ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 አለ​ቃ​ውም በፈ​ቃዱ የሚ​ያ​ቀ​ር​በ​ውን መሥ​ዋ​ዕት፥ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት፥ ወይም በፈ​ቃዱ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ያ​ቀ​ር​በ​ውን የደ​ኅ​ን​ነ​ቱን መሥ​ዋ​ዕት በአ​ቀ​ረበ ጊዜ፥ ወደ ምሥ​ራቅ የሚ​መ​ለ​ከ​ተው በር ይከ​ፈ​ት​ለት፤ በሰ​ን​በ​ትም ቀን እን​ደ​ሚ​ያ​ደ​ርግ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የደ​ኅ​ን​ነ​ቱን መሥ​ዋ​ዕት ያቅ​ርብ፤ ከዚ​ያም በኋላ ይውጣ፤ ከወ​ጣም በኋላ በሩ ይዘጋ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 አለቃውም በፈቃዱ የሚያቀርበውን መሥዋዕት፥ የሚቃጠለውን መሥዋዕት፥ ወይም በፈቃዱ ለእግዚአብሔር የሚያቀርበውን የደኅንነቱን መሥዋዕት፥ ባቀረበ ጊዜ፥ ወደ ምሥራቅ የሚመለከተው በር ይከፈትለት፥ በሰንበትም ቀን እንደሚያደርግ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የደኅንነቱን መሥዋዕት ያቅርብ፥ ከዚያም በኋላ ይውጣ፥ ከወጣም በኋላ በሩ ይዘጋ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 46:12
19 交叉引用  

ታላቅ መሠዊያ የሚገኘው በገባዖን ስለ ነበር አንድ ቀን ሰሎሞን መሥዋዕት ለማቅረብ ወደዚያ ሄደ፤ ከዚህም በፊት በዚያ መሠዊያ ላይ አንድ ሺህ የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ አቅርቦአል፤


በማግስቱ ብዙ እንስሶችን ዐርደው ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አቀረቡ፤ ከዚያም በኋላ ሕዝቡ እንዲመገቡ ሰጡአቸው፤ በተጨማሪም አንድ ሺህ ኰርማዎችን፥ አንድ ሺህ የበግ አውራዎችንና አንድ ሺህ የበግ ጥቦቶችን መሥዋዕት አድርገው በማረድ ሙሉ በሙሉ በመሠዊያው ላይ አቃጠሉአቸው፤ የወይን ጠጅ መባም አቀረቡ፤


ንጉሥ ሕዝቅያስም ሕዝቡን “አሁን ራሳችሁን ለእግዚአብሔር የለያችሁ ስለ ሆነ ለእግዚአብሔር ምስጋና ለማቅረብ መሥዋዕታችሁን ሁሉ ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አምጡ!” አላቸው፤ እነርሱም ንጉሡ እንዳዘዛቸው አደረጉ፤ አንዳዶቹም በገዛ ፈቃዳቸው ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚቀርቡ እንስሶችን አመጡ፤


ንጉሥ ሰሎሞንና ሕዝቡ ሁሉ በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት ለፊት ተሰበሰቡ፤ ከዚህም በኋላ ከብዛታቸው የተነሣ ሊቈጠሩ የማይችሉ እጅግ ብዙ በጎችንና የቀንድ ከብቶችን መሥዋዕት አድርገው አቀረቡ።


እነዚህ ከሞት የተረፉት ሰዎች በሚመለሱበት ጊዜ በአካባቢአቸው የሚኖሩ ሰዎች ብርና ወርቅ፥ ዕቃና የጭነት ከብቶች ይርዱአቸው፤ ይህም በኢየሩሳሌም ለሚገኘው ቤተ መቅደስ በፈቃዳቸው ከሚሰጡት መባ ሌላ ነው።”


በተጨማሪም ዘወትር በሙሉ የሚቃጠለውን መሥዋዕት፥ በወር መባቻ በዓልና በሌሎችም የተቀደሱ የእግዚአብሔር በዓላት የሚቀርብ መሥዋዕትን በበጎ ፈቃድ ለእግዚአብሔር ከሚቀርበው ከሌላው መሥዋዕት ሁሉ ጋር አቀረቡ።


እነርሱም ሁሉ ለበዓሉ የሚሆኑትን አንድ መቶ ወይፈኖችን፥ ሁለት መቶ በጎችንና አራት መቶ ጠቦቶችን ለመሥዋዕት አቀረቡ፤ ለኃጢአት ስርየት መሥዋዕት የሚሆኑም ዐሥራ ሁለት ፍየሎችን በእያንዳንዱ ነገድ ስም አቀረቡ።


ያም ሰው በስተ ምሥራቅ በኩል ወደሚገኘው ወደ ቤተ መቅደሱ ውጪ በር ወሰደኝ፤ በሩም ተዘግቶ ነበር፤


የሆነ ሆኖ የሕዝቡ መሪ የተቀደሰውን የመሥዋዕት ኅብስት ለመብላት በዚያ መቀመጥ ይችላል፤ በመግቢያውም ክፍል ውስጠኛ ጫፍ በሚገኘው መተላለፊያ በኩል መግባትና መውጣት ይፈቀድለታል።”


ለሚቃጠለው መሥዋዕት፥ ለእህል ቊርባንና ለመጠጥ ቊርባን በወር መባቻ፥ በሰንበቶች፥ በተወሰኑትም የእስራኤል ሕዝብ በዓላት እንዲቀርቡ የሚያስፈልጉትን ማዘጋጀት የመሪው ግዴታ ነው፤ ለእስራኤላውያን የኃጢአት ማስተስረያ ይሆን ዘንድ ስለ ኃጢአት የሚቀርበውን መሥዋዕት፥ የእህሉን ቊርባን የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የደኅንነትን ቊርባን ማዘጋጀት አለበት።”


መስፍኑም ሲገባ በበሩ መተላለፊያ በኩል ገብቶ ሲወጣም በዚያው በኩል ይውጣ።


ይኸውም ከቀንድ ከብቱ መካከል አንዱን ለሚቃጠል መሥዋዕት ማቅረብ ቢፈልግ ምንም ነውር የሌለበትን ኰርማ መርጦ ያምጣ፤ እርሱም በእግዚአብሔር ፊት የሰመረ መሥዋዕት ይሆንለት ዘንድ በመገናኛው ድንኳን መግቢያ በር በኩል ያቅርበው።


እነዚህም በዓላት ከእግዚአብሔር ሰንበቶች ጋር ተጨማሪ ሆነው የሚከበሩ ናቸው፤ ለእግዚአብሔር ከምትሰጡት ስጦታ ስእለት ሲፈጸምላችሁ ከምትሰጡት ስጦታና በፈቃዳችሁ ከምታቀርቡት ሁሉ ጋር ተደምረው የሚቀርቡ ናቸው።


“አንድ ሰው የሚያቀርበው የአንድነት መሥዋዕት ስእለት ስለ ተፈጸመለት ወይም የበጎ ፈቃድ ስጦታ ቢሆን ሁሉም በዚያው በቀረበበት ዕለት ይበላ፤ ከዚያም የተረፈ ቢኖር በማግስቱ ይበላ።


“በተወሰኑላችሁ በዓሎች እነዚህን ለጌታ ታቀርባላችሁ፤ ይህም ከስእለት ቊርባናችሁ፥ በፈቃዳችሁ ከምታቀርቡት መባ ሌላ የሚቃጠል መሥዋዕታችሁን፥ የእህል ቊርባናችሁን፥ የመጠጥ ቊርባናችሁንና የአንድነት ቊርባናችሁን ታቀርባላችሁ።”


እንግዲህ ወንድሞቼ ሆይ! እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ፥ ሕያውና የተቀደሰ መሥዋዕት አድርጋችሁ ሁለንተናችሁን እንድታቀርቡ በመሐሪው በእግዚአብሔር ስም እለምናችኋለሁ፤ ይህም ማቅረብ የሚገባችሁ ቅንነት ያለው እውነተኛ የእግዚአብሔር አገልግሎት ነው።


ክርስቶስ እንደ ወደደንና እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ መልካም መዓዛ ያለው መባና መሥዋዕት አድርጎ ሕይወቱን ስለ እኛ አሳልፎ እንደ ሰጠ እናንተም በፍቅር ኑሩ።


跟着我们:

广告


广告