Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 46:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 በታላላቅና በታናናሽ በዓላት ቀኖች ከእያንዳንዱ ኰርማና ከእያንዳንዱ የበግ አውራ ጋር የሚቀርበው የኽህል መባ አንድ የኢፍ መስፈሪያ ይሁን፤ ለእግዚአብሔር የሚሰግደው ሰው ከእያንዳንዱ የበግ ጠቦት ጋር የፈቀደውን ያኽል ያቅርብ። ከእያንዳንዱም የኢፍ መስፈሪያ መባ ጋር ሦስት ሊትር የወይራ ዘይት አብሮ ይቅረብ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 በበዓላትና በተወሰኑት በዓላት፣ ከወይፈኑ ጋራ አንድ የኢፍ መስፈሪያ፣ ከአውራ በጉም ጋራ አንድ የኢፍ መስፈሪያ የእህል ቍርባን ያቅርብ፤ ከበግ ጠቦቶቹ ጋራ የሚያቀርበው የእህል ቍርባን ግን ሰውየው የወደደውን ያህል ይሁን፤ እያንዳንዱም የኢፍ መስፈሪያ አንድ የሂን መስፈሪያ ዘይት ይኑረው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 በበዓላትና በክብረ በዓል ቀኖች የእህሉ ቁርባን ለወይፈኑ አንድ የኢፍ መስፈሪያ፥ ለአውራ በጉ አንድ የኢፍ መስፈሪያ፥ ለጠቦቶቹም እጁ የሰጠችውን ያህል፥ ለኢፍ መስፈሪያም አንድ የኢን መስፈሪያ ዘይት ይሆናል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 በበ​ዓ​ላ​ትና በክ​ብረ በዓል ቀኖች የእ​ህሉ ቍር​ባን ለወ​ይ​ፈኑ አንድ የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ፥ ለአ​ውራ በጉ አንድ የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ፥ ለጠ​ቦ​ቶ​ቹም እጁ እን​ደ​ሚ​ች​ለው ያህል፥ ለአ​ንድ የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ ዱቄት አንድ የኢን መስ​ፈ​ሪያ ዘይት ይሆ​ናል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 በበዓላትና በክብረ በዓል ቀኖች የእህሉ ቍርባን ለወይፈኑ አንድ የኢፍ መስፈሪያ፥ ለአውራ በጉ አንድ የኢፍ መስፈሪያ፥ ለጠቦቶቹም እንደሚቻለው ያህል፥ ለኢፍ መስፈሪያም አንድ የኢን መስፈሪያ ዘይት ይሆናል።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 46:11
8 交叉引用  

ለሚቃጠለው መሥዋዕት፥ ለእህል ቊርባንና ለመጠጥ ቊርባን በወር መባቻ፥ በሰንበቶች፥ በተወሰኑትም የእስራኤል ሕዝብ በዓላት እንዲቀርቡ የሚያስፈልጉትን ማዘጋጀት የመሪው ግዴታ ነው፤ ለእስራኤላውያን የኃጢአት ማስተስረያ ይሆን ዘንድ ስለ ኃጢአት የሚቀርበውን መሥዋዕት፥ የእህሉን ቊርባን የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የደኅንነትን ቊርባን ማዘጋጀት አለበት።”


እያንዳንዱ ኰርማና እያንዳንዱ የበግ አውራ በሚሠዋበት ጊዜ አንድ አንድ የኤፋ መስፈሪያ እህልና ሦስት ሦስት ሊትር የወይራ ዘይት አብሮ ይቀርባል።


ከእያንዳንዱም የበግ አውራ ጋር አንድ የኢፍ መስፈሪያ እህል ያምጣ፤ እንዲሁም ከእያንዳንዱ ጠቦት ጋር ለማቅረብ የፈለገውን ያኽል ያቅርብ፤ ከእያንዳንዱም ኢፍ መሥዋዕት ጋር አብሮ የሚቀርብ ሦስት ሊትር ዘይት ያምጣ።


ከእያንዳንዱ ኰርማና ከእያንዳንዱ የበግ አውራ ጋር አንድ አንድ ኢፍ የእህል መባ ይሁን፤ እንዲሁም ከእያንዳንዱ የበግ ጠቦት ጋር የሚቀርበው መባ መስፍኑ ለመስጠት የፈቀደውን ያኽል ይሁን፤ ከእያንዳንዱም ኢፍ ጋር ሦስት ሊትር የወይራ ዘይት አብሮ ይቅረብ።


跟着我们:

广告


广告