Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 45:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 በዓሉ በሚከበርባቸው ሰባት ዕለቶች በእያንዳንዱ ቀን ምንም ነውር የሌለባቸውን ሰባት ኰርማዎችና ሰባት የበግ አውራዎች በሙሉ ለሚቃጠል መሥዋዕት ለእግዚአብሔር የሚቀርቡትን ያዘጋጃል፤ ከዚህም ጋር በእያንዳንዱ ዕለት ለኃጢአት ስርየት መሥዋዕት የሚሆን አንድ የፍየል አውራ ያዘጋጃል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 በዓሉ በሚከበርበት በሰባቱ ቀን ገዥው በየዕለቱ እንከን የሌለባቸውን ሰባት ወይፈኖችና ሰባት አውራ በጎች የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር ያቅርብ፤ በየዕለቱም ለኀጢአት መሥዋዕት አውራ ፍየል ያቅርብ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 በበዓሉም በሰባቱ ቀኖች የሚቃጠለውን መሥዋዕት በየዕለቱ ነውር የሌለባቸውን ሰባት ወይፈንና ሰባት አውራ በጎች በሰባቱም ቀኖች ለጌታ ያቅርብ፤ ለኃጢአትም መሥዋዕት በየዕለቱ አንድ አውራ ፍየል ያቅርብ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 በበ​ዓ​ሉም በሰ​ባቱ ቀኖች የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያቅ​ርብ፤ ሰባ​ቱን ቀኖች በየ​ዕ​ለቱ ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸ​ውን ሰባት ወይ​ፈ​ንና ሰባት አውራ በጎች ያቅ​ርብ፤ ለኀ​ጢ​አ​ትም መሥ​ዋ​ዕት በየ​ዕ​ለቱ ከፍ​የ​ሎች አንድ አውራ ፍየል ያቅ​ርብ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 በበዓሉም በሰባቱ ቀኖች የሚቃጠለውን መሥዋዕት ለእግዚአብሔር ያቅርብ፥ ሰባቱን ቀኖች በየዕለቱ ነውር የሌለባቸውን ሰባት ወይፈንና ሰባት አውራ በጎች ያቅርብ፥ ለኃጢአትም መሥዋዕት በየዕለቱ አንድ አውራ ፍየል ያቅርብ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 45:23
7 交叉引用  

ስለዚህ አሁን ሰባት ኰርማዎችንና ሰባት አውራ በጎችን ይዛችሁ ወደ አገልጋዬ ወደ ኢዮብ ሂዱ፤ እዚያም ስለ ራሳችሁ ኃጢአት የሚቃጠል መሥዋዕት አቅርቡ፤ አገልጋዬ ኢዮብ ይጸልይላችኋል፤ እኔም ጸሎቱን ሰምቼ በበደላችሁ መጠን አልቀጣችሁም፤ እናንተ እንደ ኢዮብ ስለ እኔ ትክክል የሆነውን ነገር አልተናገራችሁም።”


እስከ ሰባት ቀን ድረስ የሚቃጠል መሥዋዕት ለእግዚአብሔር አቅርቡ፤ የዕለት ተግባራችሁን ማከናወን ትታችሁ በሰባተኛው ቀን ለአምልኮ ትሰበሰባላችሁ።”


ስለ ኃጢአት ስርየትም የሚሆን አንድ ተባዕት ፍየል ታቀርባላችሁ፤ በዚህም ዐይነት ለሕዝቡ የማስተስረይ ሥርዓት ትፈጽማላችሁ።


跟着我们:

广告


广告