Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 45:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ካህኑ ከዚህ የኃጢአት ስርየት መሥዋዕት ጥቂት ደም ወስዶ የቤተ መቅደሱን መቃኖች፥ የመሠዊያውን እርከን አራት ማእዘኖችና ወደ ውስጠኛው አደባባይ የሚያስገቡትን የቅጽር በሮች መቃኖች ይቀባል፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ካህኑም ከኀጢአቱ መሥዋዕት ደም በመውሰድ በቤተ መቅደሱ በር መቃኖች፣ በመሠዊያው ላይኛው ዕርከን አራት ማእዘንና በውስጠኛው አደባባይ በር መቃኖች ላይ ይርጨው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ካህኑም ከኃጢአቱ መሥዋዕት ደም ወስዶ የቤቱን መቃኖችና የመሠዊያው ጠርዝ በአራቱ ማዕዘን፥ የውስጠኛውም አደባባይ የበሩን መቃኖች ይቀባ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ካህ​ኑም ከኀ​ጢ​አቱ መሥ​ዋ​ዕት ደም ወስዶ በመ​ቅ​ደሱ መቃ​ኖ​ችና በመ​ሠ​ዊ​ያው እር​ከን በአ​ራቱ ማዕ​ዘን፥ በው​ስ​ጠ​ኛ​ውም አደ​ባ​ባይ በበሩ መቃ​ኖች ላይ ይር​ጨው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ካህኑም ከኃጢአቱ መሥዋዕት ደም ወስዶ በመቅደሱ መቃኖችና በመሠዊያው እርከን በአራቱ ማዕዘን በውስጠኛውም አደባባይ በበሩ መቃኖች ላይ ይርጨው።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 45:19
8 交叉引用  

መሬት ላይ ካረፈው መሠረት ተነሥቶ እስከ ታችኛው እርከን ድረስ ከፍታው ሁለት ክንድ፥ ወርዱ አንድ ክንድ ነበር። ከትንሹ እርከን እስከ ትልቁ እርከን ድረስ ከፍታው አራት ክንድ፥ ወርዱ አንድ ክንድ ነበር።


የላይኛው እርከን እንደ ሌሎቹ እኩል አራት ማእዘን ነበረው፤ እነርሱም ዐሥራ አራት ክንድ ርዝመትና ዐሥራ አራት ክንድ ወርድ ሲሆኑ የጠርዙ ዙሪያ ግማሽ ክንድ ስፋት ነበረው፤ የማረፊያውም ዙሪያ አንድ ክንድ ስፋት ነበረው፤ መወጣጫዎቹም በስተምሥራቅ በኩል ነበሩ።


በፊቴ ቆመው እኔን ለሚያገልገሉ የሌዊ ነገድ ከሆነው ከሳዶቅ ዘር ለተወለዱ የኃጢአት ሥርየት መሥዋዕት አድርገው ያቀርቡ ዘንድ ለእነርሱ አንድ ወይፈን ትሰጣቸዋለህ፤’ ይላል ልዑል እግዚአብሔር።


አንተም ከደሙ ትንሽ ወስደህ በመሠዊያው ጫፍ በአራቱ ማእዘን ያሉትን የመሠዊያውን ቀንዶች በመሠዊያው እርከን ላይ ያሉትን አራት ማእዘኖችና የመሠዊያውን ጠርዝ ሁሉ ትቀባቸዋለህ፤ በዚህም ሁኔታ መሠዊያውን ታነጻውና ትቀድሰዋለህ።


ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ወደ ውስጠኛው አደባባይ የሚያስገባው ወደ ምሥራቅ አቅጣጫ የሚያመለክተው በር በስድስቱ የሥራ ቀኖች ዝግ መሆን አለበት፤ ነገር ግን በሰንበት ቀንና በየወሩ መባቻ ቀን ይከፈታል።


መስፍኑ በመግቢያው ክፍል በኩል ከውጪ አደባባይ ወደ ውስጥ ገብቶ በቅጽሩ በር መቃን አጠገብ ይቆማል፤ ካህናቱ ደግሞ እርሱ ያዘጋጀውን የሚቃጠልና የደኅንነት መሥዋዕት ያቀርባሉ፤ መስፍኑም በመድረኩ ላይ እንዳለ ይሰግዳል፤ ከዚያ በኋላ እርሱ ይወጣል፤ የቅጽሩ በር ግን እስከ ምሽት ድረስ አይዘጋም።


በዚህም ዐይነት ቅድስተ ቅዱሳኑን ከእስራኤል ሕዝብ ርኲሰትና ከኃጢአታቸውም ሁሉ ለማጥራት የማንጻትን ሥርዓት ይፈጽማል፤ ንጹሕ ባልሆነ ሰፈር መካከል ስለሚገኝ ድንኳኑንም ለማንጻት እንዲሁ ያደርጋል።


跟着我们:

广告


广告