Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 45:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ምድሪቱ ለእያንዳንዱ ነገድ በርስትነት በምትከፋፈልበት ጊዜ አንድ ዕጣ ለእግዚአብሔር የተለየ ይሆናል፤ እርሱም ርዝመቱ ኻያ አምስት ሺህ ክንድ፥ ወርዱም ኻያ ሺህ ክንድ ይሆናል፤ ጠቅላላውም ክልል የተቀደሰ ይሆናል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 “ ‘ምድሪቱን ርስት አድርጋችሁ በዕጣ በምትከፋፈሉበት ጊዜ፣ ርዝመቱ ሃያ ዐምስት ሺሕ ክንድ፣ ወርዱ ሃያ ሺሕ ክንድ የሆነውን አንዱን ክፍል፣ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ስፍራ አድርጋችሁ ስጡ፤ ስፍራውም በሙሉ ቅዱስ ይሆናል፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ርስት አድርጋችሁ ምድሪቱን በዕጣ በምታካፍሉበት ጊዜ ከምድሪቱ የተቀደሰውን ክፍል መባ አድርጋችሁ ወደ ጌታ ታቀርባላችሁ። ርዝመቱ ሀያ አምስት ሺህ ክንድ ወርዱም ሀያ ሺህ ክንድ ይሆናል፤ በዳርቻው ዙሪያ ሁሉ የተቀደሰ ይሆናል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 “ርስ​ትም አድ​ር​ጋ​ችሁ ምድ​ርን በዕጣ በም​ታ​ካ​ፍ​ሉ​በት ጊዜ ከም​ድር የተ​ቀ​ደ​ሰ​ውን የዕጣ ክፍል መባ አድ​ር​ጋ​ችሁ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ። ርዝ​መቱ ሃያ አም​ስት ሺህ ክንድ፥ ወር​ዱም ሃያ ሺህ ክንድ ይሆ​ናል፤ በዳ​ር​ቻው ሁሉ ዙሪ​ያው የተ​ቀ​ደሰ ይሆ​ናል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ርስትም አድርጋችሁ ምድርን በዕጣ በምታካፍሉበት ጊዜ ከምድር የተቀደሰውን የዕጣ ክፍል መባ አድርጋችሁ ወደ እግዚአብሔር ታቀርባላችሁ። ርዝመቱ ሀያ አምስት ሺህ ክንድ ወርዱም ሀያ ሺህ ክንድ ይሆናል፥ በዳርቻው ሁሉ ዙሪያውን የተቀደሰ ይሆናል።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 45:1
15 交叉引用  

ከሀብትህና ምድርህ ከሚያፈራው መልካም ነገር ሁሉ የመጀመሪያውን መባ አድርገህ በመስጠት እግዚአብሔርን አክብር።


የመለኪያውንም ዘንግ ወስዶ የምሥራቁን አቅጣጫ ሲለካ አምስት መቶ ክንድ ነው።


ልዑል እግዚአብሔር “በዚህ ዐይነት ለእስራኤል ነገዶች ሁሉ በርስትነት የምታከፋፍሉአቸው ምድር ይህች ናት” ሲል ተናገረ።


“ምድሪቱ ለዘለቄታ መሸጥ አይገባትም፤ እርስዋ የእኔ እንጂ የእናንተ አይደለችም፤ እናንተ እንደ መጻተኛ ሆናችሁ እንድትጠቀሙባት ብቻ ፈቅጃለሁ።


ሙሴ እስራኤላውያንን እንዲህ ብሎ አዘዛቸው፦ “ለዘጠኝ ተኩል ነገዶች እንዲሰጥ እግዚአብሔር ያዘዘው በዕጣ የምትካፈሉት ርስት ይህ ነው።


ከሊባኖስ እስከ ሚስረፎትማይም ድረስ በተራራማው አገር የሚኖሩ ነዋሪዎች፥ ማለት ሲዶናውያንን ሁሉ፥ እኔ ራሴ ከእስራኤላውያን ፊት አባርራቸዋለሁ፤ አንተ ግን እኔ እንዳዘዝኩህ ምድሪቱን ለእስራኤላውያን ርስት አድርገህ አከፋፍል።


ይህንንም ምድር ርስት አድርገህ የምታካፍለው ለዘጠኙ ነገዶችና ለምናሴ ነገድ እኩሌታ ነው።”


ካህኑ አልዓዛር፥ የነዌ ልጅ ኢያሱና የእስራኤል ነገድ የቤተሰብ አለቆች በከነዓን ምድር ለእስራኤላውያን አከፋፍለዋቸው የተቀበሉት ርስት ይህ ነው።


እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተምዕራብ ያለው ግዛት በሙሉ ለዘጠኙ ነገድ ተኩል በዕጣ ተከፈለ።


ሙሴ ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ ያለውን ምድር ለሁለት ተኩል ነገዶች ርስት አድርጎ ሰጥቶአቸው ነበር፤ ለሌዋውያን ግን በእነርሱ መካከል ርስት አልሰጣቸውም።


跟着我们:

广告


广告