Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 44:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 የተቀደሰ ቊርባኔንም በኀላፊነት አልጠበቃችሁም፤ እንዲያውም በተሰጣችሁ የኀላፊነት ቦታ ላይ ባዕዳንን መደባችሁበት።’ ”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 እናንተ ራሳችሁ ማድረግ የሚገባችሁን ቅዱሳት ሥርዐቶቼን በመፈጸም ፈንታ ባዕዳንን በኀላፊነት በመቅደሴ አስቀመጣችሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 በመቅደሴ ውስጥ ሥርዓቴን ጠባቂዎች ለራሳችሁ አስቀመጣችሁ እንጂ የተቀደሰውን ነገሬን ሥርዓት አልጠበቃችሁም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 የመ​ቅ​ደ​ሴን ሥር​ዐት አል​ጠ​በ​ቃ​ች​ሁም፤ ነገር ግን የመ​ቅ​ደ​ሴን ሥር​ዐት የሚ​ጠ​ብቁ ሌሎ​ችን ለራ​ሳ​ችሁ ሾማ​ችሁ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 በመቅደሴ ውስጥ ለራሳችሁ ሥርዓቴን ጠባቂዎች አደረጋችሁ እንጂ የተቀደሰውን ነገሬን ሥርዓት አልጠበቃችሁም።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 44:8
12 交叉引用  

እንዲሁም እግዚአብሔር የሚመለክበትን ድንኳንና ቤተ መቅደሱን የመንከባከብ ኀላፊነት የእነርሱ ነበር፤ በተጨማሪም በቤተ መቅደሱ ውስጥ በሚፈጸመው የአምልኮ ሥነ ሥርዓት ዘመዶቻቸውን የአሮን ዘሮች የሆኑ ካህናትን ይረዱ ነበር።


ስለዚህ በክህነት ሳይሆን በቤተ መቅደሱ ውስጥ ያለውን ሌላውን ተግባር ሁሉ እንዲያከናውኑ እመድባቸዋለሁ።”


እኔን ለማገልገል ወደ ተቀደሰው ቦታዬ የሚገቡና ወደ ገበታዬ የሚቀርቡ እነርሱ ናቸው። እነርሱም ትእዛዜን ይጠብቃሉ።


ነገር ግን መሠዊያውንና ከመጋረጃው በስተውስጥ በኩል ያለውን ቅድስተ ቅዱሳኑን የሚመለከተውን የክህነት አገልግሎት የምትፈጽሙ አንተና ልጆችህ ብቻ ናችሁ፤ የክህነትን አገልግሎት ዕድል ፈንታ አድርጌ ስለ ሰጠኋችሁ ይህ ሁሉ ኀላፊነት የእናንተ ነው፤ ካህን ያልሆነ ማንኛውም ሰው ወደዚያ ቢቀርብ ይሞታል።”


ከዚያ በኋላ ወንድሞቻቸው ሌዋውያን በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ለሚፈጽሙት አገልግሎት እንደ ረዳት ሆነው ይሠራሉ፤ እነርሱ ራሳቸው ብቻቸውን ግን ምንም ዐይነት ሥራ አይሥሩ፤ እንግዲህ የሌዋውያንን አገልግሎት ሥርዓት የምታስይዘው በዚህ ዐይነት ነው።”


እናንተ በመላእክት አማካይነት ሕግን ተቀብላችሁ ነበር፤ ነገር ግን አልጠበቃችሁትም።”


ለሁሉ ነገር ሕይወት በሚሰጠው በእግዚአብሔርና በጴንጤናዊው ጲላጦስ ፊት በመልካም መታመን በመሰከረው በኢየሱስ ክርስቶስ ፊት አዝሃለሁ።


በእግዚአብሔርና እንዲሁም መንግሥቱን በሚያቋቁምበት ጊዜ፥ በሕያዋንና በሙታን ላይ በሚፈርደው በኢየሱስ ክርስቶስ ፊት ዐደራ እልሃለሁ፤


跟着我们:

广告


广告