Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 44:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ስብንና ደምን ለእኔ የምግብ ቊርባን አድርጋችሁ በምታቀርቡበት ጊዜ ሊታዘዙኝ ፈቃደኞች ያልሆኑትን ያልተገረዙ ባዕዳን ወደ ተቀደሰው ስፍራዬ በማስገባት ቤተ መቅደሴን አርክሳችኋል፥ በረከሰውም ተግባራችሁ ሁሉ ቃል ኪዳኔን አፍርሳችኋል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ከአስጸያፊ ሥራችሁም ሌላ ምግብ፣ ሥብና ደም ስታቀርቡ ልባቸውንና ሥጋቸውን ያልተገረዙትን እንግዶች ወደ መቅደሴ በማስገባት ቤተ መቅደሴን አረከሳችሁ፤ ቃል ኪዳኔንም አፈረሳችሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ምግቤን፥ ስብንና ደምን፥ በምታቀርቡበት ጊዜ ቤቴን እንዲያረክሱ በመቅደሴ ውስጥ እንዲሆኑ ያልተገረዘ ልብ፥ ያልተገረዘ ሥጋ ያላቸውን ባዕዳንን አግብታችኋል፥ በርኩሰታችሁም ሁሉ ቃል ኪዳኔን አፍርሰዋል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 እን​ጀ​ራ​ዬን፥ ስብ​ንና ደምን በም​ታ​ቀ​ር​ቡ​በት ጊዜ በመ​ቅ​ደሴ ውስጥ ይሆኑ ዘንድ ቤቴ​ንም ያረ​ክሱ ዘንድ፥ በል​ባ​ቸ​ውና በሥ​ጋ​ቸው ያል​ተ​ገ​ረ​ዙ​ትን እን​ግ​ዶ​ችን ሰዎች አግ​ብ​ታ​ች​ኋ​ልና፥ በር​ኵ​ሰ​ታ​ች​ሁም ሁሉ ቃል ኪዳ​ኔን አፍ​ር​ሳ​ች​ኋ​ልና።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 እንጀራዬን፥ ስብንና ደምን፥ በምታቀርቡበት ጊዜ በመቅደሴ ውስጥ ይሆኑ ዘንድ ቤቴንም ያረክሱ ዘንድ በልባቸውና በሥጋቸው ያልተገረዙትን እንግዶችን ሰዎች አግብታችኋልና፥ እነርሱም በርኵሰታችሁ ሁሉ ላይ ይጨመሩ ዘንድ ቃል ኪዳኔን አፍርሰዋልና ርኵሰታችሁ ሁሉ ይብቃችሁ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 44:7
38 交叉引用  

በሥጋው ያልተገረዘ ወንድ ሁሉ ቃል ኪዳኔን ስላላከበረ ከሕዝቡ ይወገዳል።”


እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፤ “የፋሲካ በዓል አከባበር ሥርዓት ይህ ነው፤ ማንኛውም የባዕድ አገር ሰው የፋሲካን ራት አይብላ፤


ነገር ግን ያልተገረዘ ማንም ሰው አይብላ፤ የውጪ አገር ሰው በመካከላችሁ ቢኖርና የእግዚአብሔርን የፋሲካ በዓል ማክበር ቢፈልግ፥ አስቀድማችሁ በቤተሰቡ ያሉትን ወንዶች ሁሉ ግረዙ፤ ከዚያም በኋላ የሀገር ተወላጅ እስራኤላዊ እንደ ሆነ ተቈጥሮ የፋሲካን በዓል ለማክበር ከእናንተ ጋር ይተባበር።


ሰዎች ሕጎችን በመጣስ፥ ደንብን በመተላለፍና ዘለዓለማዊውን ቃል ኪዳን በማፍረስ ምድርን አርክሰዋል።


እኔ ያዘዝኳቸውን ለመፈጸም እምቢ ይሉ እንደ ነበሩት እንደ ቀድሞ አባቶቻቸው ኃጢአት ይሠራሉ፤ ባዕዳን አማልክትን ያመልካሉ፤ እስራኤልና ይሁዳ በአንድነት ከቀድሞ አባቶቻቸው ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን አፍርሰዋል።


ይህም ቃል ኪዳን እነርሱን ከግብጽ ለማውጣት እጃቸውን በያዝኩ ጊዜ እንደ ገባሁት ቃል ኪዳን ያለ አይደለም፤ እኔ አምላካቸው ብሆንም እንኳ እነርሱ ቃል ኪዳኔን አልጠበቁም፤ እኔም ችላ አልኳቸው፤


እናንተ የይሁዳ ሕዝብና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ሆይ! የልባችሁን ክፋት ገርዛችሁ አእምሮአችሁን በማንጻት ሁለንተናችሁን ለእግዚአብሔር አስገዙ፤ ይህን ባታደርጉ ግን በክፉ ሥራችሁ ምክንያት ቊጣዬ እንደ እሳት ይነዳል፤ ቊጣዬም ከነደደ ማንም ሊያጠፋው አይችልም።”


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ለስም ብቻ የተገረዙትን ሁሉ የምቀጣበት ጊዜ ይመጣል፤


የግብጽ፥ የይሁዳ፥ የኤዶም፥ የአሞን፥ የሞአብና በበረሓ ጠረፍ የሚኖሩ የግንባራቸውን ግራና ቀኝ ጠጒር የተላጩ ሕዝቦች እንዲሁም የእስራኤል ሕዝብ ከልባቸው ያልተገረዙ ስለ ሆኑ ሁሉንም በአንድ ዐይነት እቀጣለሁ።”


ካህናቱ ሕጌን ይጥሳሉ፤ ቅዱስ ለሆነ ነገርም አክብሮት የላቸውም፤ ቅዱሱን ከርኩሱ አይለዩም፤ ንጹሕ በሆነና ባልሆነ ነገር መካከል ያለውን አያስተምሩም፤ ሰንበትንም ያቃልላሉ፤ ከዚህ የተነሣ የእስራኤል ሕዝብ እኔን አያከብሩኝም።


ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ “ሌሎቹ የእስራኤል ሕዝብ እኔን ከድተው ከፊቴ ሲርቁ፥ በቤተ መቅደስ በታማኝነት ጸንተው እኔን ሲያገለግሉ የኖሩና ነገዳቸው ከሌዊ ወገን ሆኖ ከሳዶቅ የተወለዱ ካህናት አሉ፤ ስለዚህም ስብና የመሥዋዕት ደም በማቅረብ በፊቴ ቆመው ሊያገለግሉኝ የሚገባቸው እነርሱ ናቸው፤


ስለዚህ ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሊታዘዙኝ ፈቃደኞች ያልሆኑት ያልተገረዙ ባዕዳን ሁሉ፥ በእስራኤል ሕዝብ መካከል የሚኖሩት እንኳ ቢሆኑ ወደተቀደሰው ስፍራዬ እንዲገቡ አይፈቀድላቸውም።”


መመኪያቸው ከሆኑት ውብ ጌጦቻቸው አስጠሊና አጸያፊ ጣዖቶቻቸውን ሠሩባቸው፤ ስለዚህ እነዚህን ጌጦቻቸውን በእነርሱ ዘንድ አረክሳቸዋለሁ።


የማንኛውም ሕያው ፍጥረት ሕይወት የሚገኘው በደሙ ውስጥ ነው፤ ደሙ በመሠዊያው ላይ ለእናንተ ኃጢአት ማስተስረያ እንዲሆን ሰጥቻችኋለሁ፤ ደምም ሕይወት ስለ ሆነ የኃጢአት ማስተስረያ ነው።


“ለአሮን እንዲህ ብለህ ንገረው፤ ‘ከዘርህ የአካል ጒድለት ያለበት ማንም ሰው የእኔን የአምላኩን የምግብ መባ ማቅረብ የለበትም፤ ይህም ሥርዓት በሚመጡት ዘመናት ሁሉ ተጠብቆ ይኖራል፤


በአጠቃላይ ከካህኑ አሮን ዘሮች መካከል የአካል ጒድለት ያለበት ማንም ሰው የሚቃጠል መሥዋዕት ወይም የምግብ ቊርባን ለአምላኩ ማቅረብ አይችልም።


የሚቃጠል መሥዋዕትና የምግብ መባ ለእኔ ለአምላካቸው የሚያቀርቡ ካህናት ለእኔ የተለዩና ስሜንም የማያረክሱ መሆን አለባቸው፤ ስለዚህ የተቀደሱ ይሆናሉ።


ሕዝቡም ካህኑን ቅዱስ እንደ ሆነ ይቊጠረው፤ እርሱ ለእኔ ለአምላካችሁ የምግብ መባ ያቀርባል፤ እኔ የምቀድሳችሁ እኔ እግዚአብሔር ቅዱስ ነኝ፤


“ከባዕድ ሰው የተገኘውን እንስሳ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አድርገህ አታቅርብ፤ እነዚህን የመሳሰሉ እንስሶች ነውር እንዳለባቸው ስለሚቈጠሩ ተቀባይነት የላቸውም።”


ትእዛዞቼን ባትጠብቁ፥ ሕግጋቴን ብትንቁ፥ ቃል ኪዳኔን ብታፈርሱና ሥርዓቶቼን ብትጸየፉ፥


እነርሱን ተቃውሜ ወደ ጠላቶቻቸው አገር እንዲሰደዱ አደረግሁ፤ ሆኖም እልኸኛ ልባቸው በትሕትና ተሰብሮ ከኃጢአታቸው ቢታረሙ፥


የረከሰ ምግብ በመሠዊያዬ ላይ እያኖራችሁ ‘መሠዊያህን ያረከስነው እንዴት ነው?’ ብላችሁ ትጠይቃላችሁ፤ ያረከሳችሁትማ ገበታዬ በዚህ በእናንተ ነገር ይናቃል ብላችሁ ስላሰባችሁ ነው።


ከሌዊና ከተወላጆቹ ጋር ያለኝ ቃል ኪዳን ጸንቶ ይኖር ዘንድ ይህን ትእዛዝ እኔ የላክሁላችሁ መሆኑን ታውቃላችሁ።


እናንተ ግን ከመንገድ ወጥታችሁ በትምህርታችሁ ብዙዎችን አሰናክላችኋል፤ ከሌዊ ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን አፍርሳችኋል።


“የእስራኤል ሰዎች ሆይ! እርዱን! ሕዝባችንንና ሕጋችንን፥ ይህንንም ስፍራ እየተሳደበ በየአገሩ ያለውን ሕዝብ ሁሉ የሚያስተምር ይህ ሰው ነው፤ ይህም አልበቃ ብሎት አሕዛብን ወደ ቤተ መቅደስ በማስገባት ይህን የተቀደሰ ስፍራ አርክሶአል!” እያሉ ጮኹ።


“እናንተ እልኸኞች ልባችሁ የተደፈነ! ጆሮአችሁም የማይሰማ! እናንተም ልክ እንዳባቶቻችሁ ሁልጊዜ መንፈስ ቅዱስን ትቃወማላችሁ።


ስለዚህም ከአሁን በኋላ ልበ ደንዳናነትንና እልኸኛነትን አስወግዳችሁ ለእግዚአብሔር ታዛዦች ሁኑ፤


አምላክህ እግዚአብሔር ለአንተና ለልጆችህ ታዛዥ ልብ ይሰጣል፤ ስለዚህም እርሱን በፍጹም ልብህ ትወደዋለህ፤ በዚያችም ምድር በሕይወት ትኖራለህ።


እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፦ “አንተ በቅርብ ጊዜ እንደ ቀድሞ አባቶችህ ትሞታለህ፤ ከዚያ በኋላ ይህ ሕዝብ ከእርሱ ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን ያፈርሳል። እኔንም በመተው በሚወርሰው ምድር የሚገኙትን ጣዖቶች ያመልካል።


ለቀድሞ አባቶቻቸው በመሐላ ቃል ኪዳን በገባሁላቸው መሠረት በማርና በወተት ወደ በለጸገችው ምድር አስገባቸዋለሁ፤ በዚያም በልተው በጠገቡና በወፈሩ ጊዜ እኔን ይተዋሉ፤ ቃል ኪዳኔንም አፍርሰው ሌሎች አማልክትን ያመልካሉ።


ይህም ቃል ኪዳን እጃቸውን ይዤ ከግብጽ ምድር ባወጣኋቸው ጊዜ ከአባቶቻቸው ጋር እንደ ገባሁት ቃል ኪዳን ያለ አይደለም፤ እነርሱ በቃል ኪዳኔ ስላልጸኑ እኔም ችላ አልኳቸው ይላል ጌታ።


跟着我们:

广告


广告