Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 44:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ! የምትሰማውንና የምታየውን ነገር ሁሉ ልብ ብለህ አስተውለው፤ እነሆ እኔ ስለ ቤተ መቅደሱ ሕግና ሥርዓት ሁሉ እነግርሃለሁ፤ በቤተ መቅደሱ ውስጥ መግባትና መውጣት የሚፈቀድላቸው ምን ዐይነት ሰዎች እንደ ሆኑ አስተውል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፤ “የሰው ልጅ ሆይ፤ ስለ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ሥርዐት የምነግርህን ሁሉ በጥንቃቄ አስተውል፤ በሚገባ አድምጥ፤ ልብም በለው። የቤተ መቅደሱን መግቢያና የመቅደሱን መውጫዎች ሁሉ አስተውል፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ጌታም እንዲህ አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ ስለ ጌታ ቤት ሥርዓት ሁሉ እና ሕጉን ሁሉ የምናገርህን ሁሉ ልብ አድርግ በዓይንህ ተመልከት በጆሮህም ስማ፤ የቤቱን መግቢያ የመቅደሱንም መውጫ ሁሉ ልብ አድርግ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ አለኝ፥ “የሰው ልጅ ሆይ! ልብ አድ​ርግ፤ ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት ሥር​ዐ​ትና ሕግ ሁሉ የም​ነ​ግ​ር​ህን ሁሉ በዐ​ይ​ንህ ተመ​ል​ከት፤ በጆ​ሮ​ህም ስማ፤ የቤ​ቱ​ንም መግ​ቢያ፥ የመ​ቅ​ደ​ሱ​ንም መውጫ ሁሉ ልብ አድ​ርግ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ ልብ አድርግ ስለ እግዚአብሔርም ቤት ሥርዓትና ሕግ ሁሉ የምናገርህን ሁሉ በዓይንህ ተመልከት በጆሮህም ስማ፥ የቤቱንም መግቢያ የመቅደሱንም መውጫ ሁሉ ልብ አድርግ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 44:5
17 交叉引用  

እንግዲህ አምላካችሁን እግዚአብሔርን በፍጹም ልባችሁና በፍጹም ነፍሳችሁ አገልግሉ፤ የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦትና እግዚአብሔርን ለማምለክ መገልገያ የሆኑትን ንዋያተ ቅድሳት ሁሉ አምጥታችሁ በውስጡ ማኖር ትችሉ ዘንድ ቤተ መቅደሱን ለክብሩ መሥራት ጀምሩ።”


ከዚህም የተነሣ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔርን በቅን መንፈስ ለማምለክ የፈለጉ ከመላው የእስራኤል ነገዶች የተውጣጡ ብዙ ሰዎች ለቀድሞ አባቶቻቸው አምላክ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ለማቅረብ ሌዋውያኑን ተከትለው ወደ ኢየሩሳሌም መጡ።


እግዚአብሔር ሆይ! አንተ ሕጎችህን ሰጥተኸናል፤ በታማኝነት እንድንታዘዛቸውም ነግረኸናል፤


ወደ እግዚአብሔር ተራራ ማን ይወጣል፤ በተቀደሰ ስፍራውስ ማን ይቆማል።


የቀሩት ግን እግዚአብሔር የተናገረውን ቃል ችላ በማለት አገልጋዮቻቸውንና እንስሶቻቸውን በሜዳ ተዉ።


ይህን በተመለከትኩ ጊዜ ስለ እርሱ አስባለሁ፤ ከተመለከትኩትም ነገር ትምህርትን ገበየሁ።


ሰውየውም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ! እዚህ ድረስ እንድትመጣ የተደረገበት ምክንያት እኔ የማሳይህን ሁሉ እንድትረዳ ስለ ሆነ ልብ ብለህ ተመልከት፤ በጥንቃቄም ስማ፤ የምታየውንም ሁሉ ለእስራኤል ሕዝብ ንገራቸው።”


የታችኛዎቹ ክፍሎች በምሥራቅ በኩል ከወደ ውጪው አደባባይ መግቢያ ነበራቸው።


ከዚያ በኋላ ያ ሰው በበሩ ጥግ መግቢያ በኩል በሰሜን ወዳለው የተቀደሱ የካህናት መደዳ ክፍሎች ወደ ሆኑት አመጣኝ፤ ከክፍሎቹም በስተ ምዕራብ መጨረሻ አንድ ቦታ አየሁ።


ሰውየውም “የሰው ልጅ ሆይ! ይህን ሁሉ በጥንቃቄ አስታውስ” አለኝ። ከዚያን በኋላ ያ ሰው ወደ ውሃው ዳርቻ መለሰኝ፤


ደግሞም እንዲህ አለኝ፦ “ዳንኤል ሆይ! አትፍራ! ማስተዋልን ለማግኘት ራስህን በእግዚአብሔር ፊት ለማዋረድ ከወሰንክበት ከመጀመሪያው ቀን አንሥቶ ጸሎትህ ተሰምቶአል፤ እኔም ተልኬ ወደ አንተ የመጣሁት ጸሎትህ መልስ ከማግኘቱ የተነሣ ነው።


ያዘዝኳችሁንም ሁሉ እንዲፈጽሙ አስተምሩአቸው! እነሆ፥ እኔም እስከ ዓለም መጨረሻ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።”


ሲሄዱም ውሃ ወዳለበት ቦታ ደረሱ፤ ጃንደረባውም “እነሆ፥ እዚህ ውሃ አለ፤ እንዳልጠመቅ የሚከለክለኝ ነገር ምንድን ነው?” አለ። [


“እንግዲህ እኔ ያዘዝኩህን ሁሉ አድርግ፤ በእርሱ ላይ ምንም ነገር አትጨምር፤ ከእርሱም አንዳች ነገር አታጒድል።


እርሱም እንዲህ አለ፦ “የዚህን ሕግ ቃላት በጥንቃቄ መጠበቅ ይችሉ ዘንድ ልጆቻችሁን እንድታዙ እኔ ዛሬ በእናንተ ላይ ምስክር እንዲሆን የምሰጣችሁን ቃላት ሁሉ አስተውሉ።


跟着我们:

广告


广告