ሕዝቅኤል 44:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም3 የሆነ ሆኖ የሕዝቡ መሪ የተቀደሰውን የመሥዋዕት ኅብስት ለመብላት በዚያ መቀመጥ ይችላል፤ በመግቢያውም ክፍል ውስጠኛ ጫፍ በሚገኘው መተላለፊያ በኩል መግባትና መውጣት ይፈቀድለታል።” 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም3 በእግዚአብሔር ፊት ይበላ ዘንድ በመግቢያው በር ገብቶ ውስጥ ሊቀመጥ የሚችለው ገዥው ራሱ ብቻ ነው፤ በመግቢያው መተላለፊያ በረንዳ እንደ ገባ መውጣትም የሚችለው በዚያው ነው።” 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)3 መስፍኑ ብቻ በጌታ ፊት ምግብ ለመብላት ይቀመጥበታል፤ በበሩ መተላለፊያ መንገድ ይገባል በዚያም መንገድ ይወጣል። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)3 አለቃው ግን እርሱ በእግዚአብሔር ፊት እንጀራ ይበላ ዘንድ ይቀመጥባታል፤ በበሩ ይገባል፤ በዚያም መንገድ ይወጣል።” 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)3 አለቃው ግን እርሱ በእግዚአብሔር ፊት እንጀራ ይበላ ዘንድ ይቀመጥበታል፥ በበሩ ደጀ ሰላም መንገድ ይገባል በዚያም መንገድ ይወጣል። 参见章节 |