Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 44:29 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 የእህሉ መሥዋዕት፥ የኃጢአትና የበደል ስርየት መሥዋዕት ለእነርሱ ምግብ ይሁንላቸው፤ በእስራኤል ምድር ለእኔ ተለይቶ የተቀደሰውን ማናቸውንም መባ ሁሉ ይቀበሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 የእህሉን ቍርባን፣ የኀጢአቱንና የበደሉን መሥዋዕት ይበላሉ፤ በእስራኤል ለእግዚአብሔር የተሰጠው ሁሉ የእነርሱ ይሆናል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 የእህሉን ቁርባን፥ የኃጢአትን መሥዋዕትና የበደልን መሥዋዕት ይበላሉ፤ በእስራኤልም እርም የሆነው ነገር ሁሉ ለእነርሱ ይሆናል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 የእ​ህ​ሉን ቍር​ባ​ንና የኀ​ጢ​አ​ትን መሥ​ዋ​ዕት የን​ስ​ሓ​ንም መሥ​ዋ​ዕት ይበ​ላሉ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ዘንድ እርም የሆ​ነው ነገር ሁሉ ለእ​ነ​ርሱ ይሆ​ናል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 የእህሉን ቍርባንና የኃጢአትን መሥዋዕት የበደልንም መሥዋዕት ይበላሉ፥ በእስራኤልም ዘንድ እርም የሆነው ነገር ሁሉ ለእነርሱ ይሆናል።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 44:29
14 交叉引用  

እርሱም እንዲህ አለኝ፦ “ይህ ቦታ ካህናቱ ለኃጢአትና ለበደል ማስተስረያ መሥዋዕት ሆኖ የቀረበውን ሥጋ የሚቀቅሉበትና የእህል መሥዋዕት የሚጋግሩበት ክፍል ነው፤ በዚህም ዐይነት በሕዝቡ ላይ ጒዳት እንዳይደርስ ከተቀደሰው መሥዋዕት ሁሉ ወደ ውጪው አደባባይ አይወጣም።”


ቀሪው መባ ግን ለካህናቱ ይሰጥ፤ እርሱም ለእግዚአብሔር ከቀረበው መባ ተከፍሎ የተወሰደ በመሆኑ እጅግ የተቀደሰ ነው።


ከእህል መባውም የተረፈው ዱቄት የአሮን ዘር ለሆኑት ካህናት ይሰጥ፤ እርሱም ለእግዚአብሔር ከቀረበው መባ የሚቃጠል ቊርባን በመሆኑ እጅግ የተቀደሰ ነው።


ይህ ለቀድሞ ባለቤቱ ለመመለስ የማይችለው መሬትም በተከታዩ በኢዮቤልዩ ዓመት ለእግዚአብሔር የተለየ ቀዋሚ ንብረት እንደ ሆነ ይቀራል፤ እርሱም የካህኑ ድርሻ ይሆናል።


“አንድ ሰው የራሱን ሰውም ሆነ እንስሳን ወይም መሬትን ሙሉ በሙሉ ለእግዚአብሔር አገልግሎት የተለየ እንዲሆን ካደረገው በኋላ ፈጽሞ ሊሸጠውም ሆነ መልሶ ሊዋጀው አይገባውም።


እንስሳውን የሚሠዋውም ካህን በመገናኛው ድንኳን አደባባይ ባለው የተቀደሰ ስፍራ ይብላው፤


ከካህናቱ ቤተሰብ ወንድ የሆነ ሁሉ ይህን መሥዋዕት ይመገብ፤ እርሱ እጅግ የተቀደሰ መሥዋዕት ነው።


ከካህናት ወገን የሆነ ወንድ ሁሉ የመሥዋዕቱን ሥጋ ይብላ፤ ነገር ግን ያ መሥዋዕት እጅግ የተቀደሰ ስለ ሆነ በተቀደሰ ስፍራ ይብላው።


“በእስራኤል ውስጥ ሙሉ በሙሉ ለእኔ የተለየ ነገር ሁሉ ለእናንተ ይሆናል።


እኛ መሠዊያ አለን፤ ሆኖም በድንኳኒቱ ውስጥ የሚያገለግሉ ካህናት በዚህ መሠዊያ ላይ ካለው ምግብ ወስደው መብላት አይፈቀድላቸውም።


ሙሴ ለሌዊ ነገድ የርስት ድርሻ አልሰጠም፤ እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር በመሠዊያ ላይ የሚቃጠል መሥዋዕት ሆኖ ከሚቀርበው መባ የሚያገኙት ድርሻ እንደ ርስት ሆኖ ተመድቦላቸዋል።


跟着我们:

广告


广告