Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 44:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 “ካህናቱ ለሕዝቤ ቅዱስ የሆነውንና ያልሆነውን ንጹሕ የሆነውንና ርኩስ የሚባለውን ነገር እንዲለዩ ያስተምሩአቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 በተቀደሰውና ባልተቀደሰው መካከል ያለውን ልዩነት ለሕዝቤ ያስተምሩ፤ የረከሰውንና ያልረከሰውን እንዴት እንደሚለዩም ያሳዩአቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 ሕዝቤን ቅዱስ በሆነውና በረከሰው መካከል እንዲለዩ ያስተምሩ፥ ንጹሕ በሆነውና ንጹሕ ባልሆነው መካከል እንዲለዩ ያሳዩአቸው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 በተ​ቀ​ደ​ሰ​ውና ባል​ተ​ቀ​ደ​ሰው መካ​ከል ይለዩ ዘንድ ሕዝ​ቤን ያስ​ተ​ምሩ፤ ንጹ​ሕና ንጹሕ ባል​ሆ​ነው መካ​ከል ይለዩ ዘንድ ያሳ​ዩ​አ​ቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 በተቀደሰውና ባልተቀደሰው መካከል ይለዩ ዘንድ ሕዝቤን ያስተምሩ፥ ንጹሕና ንጹሕ ባልሆነው መካከል ይለዩ ዘንድ ያሳዩአቸው።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 44:23
15 交叉引用  

እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል መለሰልኝ፦ “ወደ እኔ በንስሓ ብትመለስ፥ እቀበልሃለሁ፤ እንደገናም አገልጋይ ትሆነኛለህ፤ ከንቱ ቃል መናገርህን ትተህ ቁም ነገር ያለውን መልእክት ብታስተላልፍ፥ እንደገና የእኔ ነቢይ ትሆናለህ፤ ሕዝቡ ወደ አንተ ይመጣሉ እንጂ አንተ ወደ እነርሱ አትሄድም።


ካህናቱ ሕጌን ይጥሳሉ፤ ቅዱስ ለሆነ ነገርም አክብሮት የላቸውም፤ ቅዱሱን ከርኩሱ አይለዩም፤ ንጹሕ በሆነና ባልሆነ ነገር መካከል ያለውን አያስተምሩም፤ ሰንበትንም ያቃልላሉ፤ ከዚህ የተነሣ የእስራኤል ሕዝብ እኔን አያከብሩኝም።


በተቀደሰውና በተራው ቦታ መካከል ለመለየት ቤተ መቅደሱን የሚከልለው ግንብ ርዝመቱ አምስት መቶ ክንድ፥ ወርዱ አምስት መቶ ክንድ ሆነ።


ሕዝቤ እኔን በሚገባ ካለማወቁ የተነሣ ጠፍቶአል፤ እናንተ እኔን ለማወቅ ስላልፈለጋችሁ እኔም ካህናት ሆናችሁ እንድታገለግሉኝ አልፈልጋችሁም፤ ሕጌንም ስላቃለላችሁና ስለ ረሳችሁ ልጆቻችሁ በእኔ ዘንድ የተረሱ ይሆናሉ።


ንጹሕ በሆነውና ንጹሕ ባልሆነው መካከል ያለውን ልዩነት ለማወቅ፥ ይኸውም በሚበሉትና በማይበሉት እንስሶች መካከል ያለውን ልዩነት ለመረዳት ብርቱ ጥንቃቄ አድርጉ።”


ካህኑም ይመርምረውና እነዚህ ሁሉ የልብስ ዐይነቶች እስከ ሰባት ቀን ድረስ በአንድ ክፍል ተዘግቶባቸው ይቈዩ።


እነዚህ ሥርዓቶች አንድን ነገር ንጹሕ መሆኑን ወይም አለመሆኑን የሚወስኑ ናቸው።”


ነቢያትዋ በትዕቢት የተወጠሩና በተንኰል የተሞሉ ናቸው፤ ካህናትዋ የተቀደሰውን ያረክሳሉ፤ በሕግም ላይ ያምፃሉ።


ሥርዓትህን ለያዕቆብ፥ ሕግህንም ለእስራኤል ያስተምራሉ፤ በፊትህ ዕጣን ያጥናሉ፤ የሚቃጠል መሥዋዕትም በመሠዊያህ ላይ ያቀርባሉ።


跟着我们:

广告


广告