ሕዝቅኤል 44:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም17 በቤተ መቅደሱ ወደ ውስጠኛው አደባባይ የሚያደርሰውን ቅጽር በር በሚገቡበት ጊዜ ከበፍታ የተሠራ ልብስ መልበስ ይኖርባቸዋል፤ በውስጠኛው አደባባይም ሆነ በቤተ መቅደስ በሚያገለግሉበት ጊዜ ማናቸውንም ከበግ ጠጒር የተሠራ ነገር መልበስ የለባቸውም። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም17 “ ‘ወደ ውስጠኛው አደባባይ በሮች ሲገቡ፣ የበፍታ ፈትል ይልበሱ፤ በውስጠኛው አደባባይ በሮችም ሆነ በቤተ መቅደሱ ውስጥ ሲያገለግሉ፣ ከበግ ጠጕር የተሠራ ልብስ አይልበሱ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)17 ወደ ውስጠኛው አደባባይ በር በገቡ ጊዜ የተልባ እግር ልብስ ይልበሱ፤ በውስጠኛው አደባባይ በርና በቤቱ ውስጥ ባገለገሉ ጊዜ አንዳች የበግ ጠጉር በላያቸው አይሁን። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)17 ወደ ውስጠኛውም አደባባይ በር በገቡ ጊዜ የተልባ እግር ልብስ ይልበሱ፤ በውስጠኛውም አደባባይ በርና በቤቱ ውስጥ በአገለገሉ ጊዜ ከበግ ጠጕር አንዳች ነገር በላያቸው አይሁን። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)17 ወደ ውስጠኛውም አደባባይ በር በገቡ ጊዜ የተልባ እግር ልብስ ይልበሱ፥ በውስጠኛውም አደባባይ በርና በቤቱ ውስጥ ባገለገሉ ጊዜ ከበግ ጠጕር አንዳች ነገር በላያቸው አይሁን። 参见章节 |