Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 44:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 “በክህነት ለማገልገል ወደ እኔ አይቀርቡም፤ በጣም ወደ ተቀደሰው ቅዱስ ቊርባኔም አይቀርቡም፤ እነርሱም ለፈጸሙት አጸያፊ ተግባራቸው አሳፋሪ ውጤት ተጠያቂዎች ይሆናሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 እንደ ካህናት ያገለግሉኝ ዘንድ ወደ እኔ አይቀርቡም፤ ወይም ቅዱስ ወደ ሆነው ነገሬ ሁሉ፣ ወይም እጅግ ወደ ተቀደሱ መሥዋዕቶቼ አይቀርቡም፤ የአስጸያፊ ድርጊታቸውን ኀፍረት ይሸከማሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 በክህነት ሊያገለግሉኝ ወደ እኔ አይቀርቡም፥ ወደተቀደሰው ነገሬና ወደ ቅድስተ ቅዱሳን አይቀርቡም፤ ስድባቸውንና የሠሩትን ርኩሰታቸውን ይሸከማሉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 እኔ​ንም በክ​ህ​ነት ለማ​ገ​ል​ገል ወደ እኔ አይ​ቀ​ር​ቡም፤ ወደ ተቀ​ደ​ሰ​ውም ነገ​ሬና ወደ ቅድ​ስተ ቅዱ​ሳን ነገር አይ​ቀ​ር​ቡም፤ እፍ​ረ​ታ​ቸ​ው​ንና የሠ​ሩ​ት​ንም ርኵ​ሰ​ታ​ቸ​ውን ይሸ​ከ​ማሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ካህናትም ይሆኑኝ ዘንድ ወደ እኔ አይቀርቡም፥ ወደ ተቀደሰውም ነገሬና ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ነገር አይቀርቡም፥ እፍረታቸውንና የሠሩትንም ርኵሰታቸውን ይሸከማሉ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 44:13
8 交叉引用  

እነዚያም ካህናት በቤተ መቅደስ ከማገልገል ታገዱ፤ ይሁን እንጂ ለጓደኞቻቸው ካህናት ይሰጥ የነበረውን እርሾ ያልነካው ኅብስት እንዲመገቡ ተፈቅዶላቸው ነበር።


እኛና የቀድሞ አባቶቻችን በመደጋገም ኃጢአት በመሥራት እግዚአብሔር አምላካችንን አሳዝነናል፤ ትእዛዞቹንም አልፈጸምንም፤ ስለዚህ በዕፍረት ልንወድቅና ውርደትም እንደ ልብስ ሊሸፍነን ይገባል።”


ታላቅና ታናሽ እኅቶችሽን ወስጄ ለአንቺ እንደ ልጆችሽ አድርጌ በምሰጥበት ጊዜ የቀድሞውን አካሄድሽን አስታውሰሽ ታፍሪአለሽ። ይህ የሚሆነው ግን ከአንቺ ጋር በገባሁት ቃል ኪዳን መሠረት አይደለም።


ይህንንም የማደርገው፥ ለፈጸምሽው በደል ሁሉ ይቅርታ ሳደርግልሽ ሥራሽን በማስታወስ በድንጋጤ ዐፍረሽ ጸጥ እንድትዪ ነው፤” ይህን የተናገረ ልዑል እግዚአብሔር ነው።


“በግብጽ ምድር ላይ ሰይፍ ስለ ተዘጋጀ ብዛት ያለው የግብጽ ሕዝብ በሰይፍ ከተገደሉት ሰዎች መካከል ይወድቃሉ።


በእናንተ ዙሪያ የሚገኙ የጐረቤት አገሮች ሁሉ እንደሚዋረዱ፥ እኔ ልዑል እግዚአብሔር በፍጹም እምላለሁ።


የሚያስፈራቸው ነገር ሳይኖር በገዛ ምድራቸው በሰላም ይኖሩ በነበረ ጊዜ የፈጸሙትን አሳፋሪ ተግባርና ለእኔ አለመታመናቸውን ሁሉ ይረሳሉ።


እነርሱም እናንተን የመርዳት ተግባራቸውን እያከናወኑ ድንኳኑንም የመንከባከብ ኀላፊነት ይወስዳሉ፤ ይሁን እንጂ በተቀደሰው ስፍራና በመሠዊያው ላይ ያሉትን ንዋያተ ቅድሳት መንካት አይኖርባቸውም፤ ነክተው ቢገኙ ግን እነርሱም እናንተም በአንድነት ትሞታላችሁ።


跟着我们:

广告


广告