ሕዝቅኤል 43:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም20 አንተም ከደሙ ትንሽ ወስደህ በመሠዊያው ጫፍ በአራቱ ማእዘን ያሉትን የመሠዊያውን ቀንዶች በመሠዊያው እርከን ላይ ያሉትን አራት ማእዘኖችና የመሠዊያውን ጠርዝ ሁሉ ትቀባቸዋለህ፤ በዚህም ሁኔታ መሠዊያውን ታነጻውና ትቀድሰዋለህ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም20 ከደሙም ጥቂት ወስደህ፣ በመሠዊያው አራት ቀንዶች፣ በላይኛው ዕርከን አራት ጐኖች ላይ እንዲሁም በጠርዙ ዙሪያ ሁሉ ታደርጋለህ፤ በዚህ ሁኔታ መሠዊያውን ታነጻለህ፤ ታስተሰርይለታለህም። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)20 ከደሙ ትወስዳለህ፥ በአራቱ ቀንዶቹ፥ በእርከኑ፥ በአራቱ ማዕዘን ላይ፥ በዙሪያውም ባለው ጠርዝ ላይ ታደርጋለህ፤ እንዲሁ ታነጻዋለህ ታጠራዋለህም። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)20 ከደሙም ትወስዳለህ፤ በአራቱ የመሠዊያ ቀንዶቹም፥ በእርከኑም በአራቱ ማዕዘን ላይ፥ በዙሪያውም በአለው ክፈፍ ላይ ትረጨዋለህ፤ እንዲሁ ታነጻዋለህ፤ ታስተሰርይለትማለህ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)20 ከደሙም ትወስዳለህ፥ በአራቱ ቀንዶቹም በእርከኑም በአራቱ ማዕዘን ላይ በዙሪያውም ባለው ክፈፍ ላይ ትረጨዋለህ፥ እንዲሁ ታነጻዋለህ ታስተሰርይለትማለህ። 参见章节 |