Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 42:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 በተቀደሰውና በተራው ቦታ መካከል ለመለየት ቤተ መቅደሱን የሚከልለው ግንብ ርዝመቱ አምስት መቶ ክንድ፥ ወርዱ አምስት መቶ ክንድ ሆነ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ስለዚህ በአራቱም ማእዘን ለካው፤ የተቀደሰውን ስፍራ ከሌላው የሚለይ በዙሪያው ግንብ ነበረ፤ የግንቡም ርዝመት ዐምስት መቶ ክንድ ሲሆን፣ ወርዱ ዐምስት መቶ ክንድ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 በአራቱ አቅጣጫ ለካ፤ የተቀደሰውንና ያልተቀደሰውን ለመለየት ርዝመቱ አምስት መቶ ክንድ ወርዱም አምስት መቶ ክንድ የሆነ ቅጥር በዙሪያው ነበረ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 በአ​ራ​ቱም ወገን ለካ፤ የተ​ቀ​ደ​ሰ​ው​ንና ያል​ተ​ቀ​ደ​ሰ​ውን ይለይ ዘንድ ርዝ​መቱ አም​ስት መቶ ክንድ፥ ወር​ዱም አም​ስት መቶ ክንድ የሆነ ቅጥር በዙ​ሪ​ያው ነበረ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 በአራቱ ወገን ለካው። የተቀደሰውንና ያልተቀደሰውን ይለይ ዘንድ ርዝመቱ አምስት መቶ ክንድ ወርዱም አምስት መቶ ክንድ የሆነ ቅጥር በዙሪያው ነበረ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 42:20
18 交叉引用  

ውዴ፥ ዋልያ ወይም የአጋዘን ግልገል ይመስላል፤ እነሆም ከቤታችን ቅጽር አጠገብ ቆሞአል፤ በመስኮትም ወደ ውስጥ ይመለከታል፤ በዐይነ ርግቡ ቀዳዳ በኩል አሾልኮ ይቃኛል።


አምላክ ሆይ! አንተ አምላኬ ነህ፤ ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ፤ ስምህንም አመሰግናለሁ፤ አንተ እጅግ አስደናቂ የሆኑ ነገሮችን አድርገሃል፤ ከጥንት ጀምሮ ያቀድከውን ሁሉ፥ ፍጹምነት ባለው አስተማማኝ ሁኔታ አከናውነሃል።


በዚያን ጊዜ በይሁዳ ምድር የሚከተለው መዝሙር ይዘመራል፦ ጠንካራ ከተማ አለን፤ እንደ ቅጥርና እንደ ምሽግ የጸና መዳኛም አድርጎላታል።


ከእንግዲህ ወዲህ በምድርሽ የዐመፅ ድምፅ በድንበሮችሽም ጥፋት ወይም ውድመት አይሰማም፤ ነገር ግን ቅጥሮችሽን መዳን የቅጥር በሮችሽን ምስጋና ብለሽ ትጠሪአቸዋለሽ።


ካህናቱ ሕጌን ይጥሳሉ፤ ቅዱስ ለሆነ ነገርም አክብሮት የላቸውም፤ ቅዱሱን ከርኩሱ አይለዩም፤ ንጹሕ በሆነና ባልሆነ ነገር መካከል ያለውን አያስተምሩም፤ ሰንበትንም ያቃልላሉ፤ ከዚህ የተነሣ የእስራኤል ሕዝብ እኔን አያከብሩኝም።


በቤተ መቅደሱ ዙሪያ ቅጥር ነበረ፤ በሰውዬው እጅ ያለው መለኪያ ዘንግ በእርሱ ረጃጅም ክንዶች ስድስት ይሆናል፤ የቅጽሩ ስፋት ሲለካ አንድ ዘንግ፥ ከፍታው ሲለካ አንድ ዘንግ ሆነ። የእርሱ ክንድ ግን በሌሎች ሰዎች ክንድ ሲለካ አንድ ክንድ ከጋት ይሆናል።


በምዕራቡ በኩል ሲለካ አምስት መቶ ክንድ ሆነ።


የቤተ መቅደሱም ሕግ ይህ ነው፤ በተራራው ጫፍ ላይ በቤተ መቅደሱ ዙሪያ ያለው ክልል በሙሉ እጅግ የተቀደሰ ይሆናል።”


“ካህናቱ ለሕዝቤ ቅዱስ የሆነውንና ያልሆነውን ንጹሕ የሆነውንና ርኩስ የሚባለውን ነገር እንዲለዩ ያስተምሩአቸው።


ከዚህም ክልል ውስጥ የእያንዳንዱ ማእዘን ርዝመት አምስት መቶ ክንድ ሆኖ አራት ማእዘን ያለው አንድ ቦታ ለቤተ መቅደሱ ይመደባል፤ በዚህም ክልል ዙሪያ ስፋቱ ኀምሳ ክንድ የሆነ ክፍት ቦታ ይኖራል።


ልዩ ከሆነው ክልል ተከፍሎ የሚቀረው ስፍራ ኻያ አምስት ሺህ ክንድ ርዝመት አምስት ሺህ ክንድ ወርድ ነው፤ እርሱም በአጠቃላይ ለሕዝቡ የጋራ መጠቀሚያ ይሆናል፤ ለቤት ሥራና ለከብት ማሰማሪያም ይሆናል፤ ከተማይቱም በመካከሉ ትሆናለች።


ስለዚህም በምድሪቱ መኻል የተለየው ቅዱስ ድርሻ በጠቅላላው የእያንዳንዱ ማእዘን ርዝመት ኻያ አምስት ሺህ ክንድ ሲሆን እርሱም ከተማይቱ የተሠራችበትን ቦታ ያጠቃልላል።


እናንተ በተቀደሰውና ባልተቀደሰው፥ በንጹሕና ርኩስ በሆነው መካከል ያለውን ልዩነት ማወቅ አለባችሁ፤


እናንተ የኢየሩሳሌም ሕዝብ ሆይ! የከተማይቱ ቅጽሮች የሚሠሩበት ጊዜ ይመጣል፤ በዚያን ጊዜ ግዛታችሁ ይሰፋል።


እግዚአብሔር ራሱ በዙሪያዋ እንደ እሳት ቅጽር ሆኖ ከተማይቱን እንደሚጠብቅና በክብሩም በዚያ እንደሚኖር ተስፋ ሰጥቶአል።”


ከዚህም ሁሉ በላይ በእኛና በእናንተ መካከል ትልቅ ገደል አለ፤ ስለዚህ ከእኛ ወደ እናንተ፥ ከእናንተም ወደ እኛ መሻገር የሚችል ማንም የለም።’


ደግሞም ጌታ እንዲህ ብሎአል፦ “ከእነርሱ መካከል ተለይታችሁ ውጡ፤ ርኩስ የሆነውንም ነገር አትንኩ፤ እኔም እቀበላችኋለሁ፤


跟着我们:

广告


广告